ዘፀአት 6:1 - Compare All Versions

ዘፀአት 6:1 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “በጸ​ናች እጅ ይለ​ቅ​ቃ​ቸ​ዋ​ልና፥ በተ​ዘ​ረ​ጋ​ችም ክንድ ከም​ድሩ አስ​ወ​ጥቶ ይሰ​ድ​ዳ​ቸ​ዋ​ልና አሁን በፈ​ር​ዖን የማ​ደ​ር​ገ​ውን ታያ​ለህ።”

ዘፀአት 6:1 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን፣ “አሁን በፈርዖን ላይ የማደርገውን ታያለህ፤ ከኀያሉ እጄ የተነሣ እንዲሄዱ ይለቅቃቸዋል፤ ከኀያሉም እጄ የተነሣ ከአገሩ ያስወጣቸዋል” አለው።

ዘፀአት 6:1 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ “በጸናች እጅ ይለቅቃቸዋልና፥ በጸናችም እጅ ከምድሩ አስወጥቶ ይሰድዳቸዋልና አሁን በፈርዖን የማደርገውን ታያለህ።”

ዘፀአት 6:1 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

እግዚአብሔርም ሙሴን “በንጉሡ በፈርዖን ላይ የማደርገውን አሁን ታያለህ፤ በኀይሌ ተገዶ ሕዝቤን ይለቃል፤ በኀያል ክንዴም ተሸንፎ ያባርራቸዋል።”

ዘፀአት 6:1 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ጌታም ሙሴን አለው፦ “አሁን ፈርዖንን ምን እንደማደርገው ታያለህ በጸናች እጅ ይለቅቃቸዋል፥ በጸናችም እጅ ከምድሩ አስወጥቶ ይሰድዳቸዋል።”