ዘፀአት 36:2-3 - Compare All Versions

ዘፀአት 36:2-3 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ከዚያም ሙሴ ባስልኤልንና ኤልያብን እንዲሁም እግዚአብሔር ችሎታ የሰጣቸውን፣ መጥተው ሥራውን ለመሥራት ፈቃደኛ የሆኑትን ጥበብ ያላቸውን ሰዎች ሁሉ አስጠራ። የመቅደሱን የግንባታ ሥራ ለማከናወን እስራኤላውያን ያመጡትን ስጦታ ሁሉ ከሙሴ ተቀበሉ፤ ሕዝቡ የበጎ ፈቃድ ስጦታዎችን በየማለዳው ማምጣታቸውን ቀጠሉ።

ዘፀአት 36:2-3 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ሙሴም ባጽልኤልንና ኦሆሊአብን፥ እንዲሁም እግዚአብሔር ልዩ ችሎታ የሰጣቸውንና ለመርዳት ፈቃደኞች የነበሩትን ሌሎችን ጥበበኞች ሁሉ ጠርቶ ሥራውን እንዲጀምሩ ነገራቸው። እነርሱም እስራኤላውያን ለተቀደሰው ድንኳን መሥሪያ እንዲውል ያመጡትን ስጦታ ከሙሴ እጅ ተቀበሉ፤ የእስራኤል ሕዝብ ግን በየማለዳው ስጦታቸውን ለሙሴ ከማምጣት አልተቈጠቡም።

ዘፀአት 36:2-3 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ሙሴም ባስ​ል​ኤ​ል​ንና ኤል​ያ​ብን፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዕው​ቀ​ት​ንና ጥበ​ብን በል​ቡ​ና​ቸው ያሳ​ደ​ረ​ባ​ቸ​ው​ንና ጥበብ ያላ​ቸ​ውን፥ ሥራ​ው​ንም ለመ​ሥ​ራት ይቀ​ርብ ዘንድ ልቡ ያስ​ነ​ሣ​ውን ሁሉ ሥራ​ውን ሠር​ተው ይፈ​ጽሙ ዘንድ ጠራ​ቸው። እነ​ር​ሱም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ለመ​ቅ​ደስ ማገ​ል​ገያ ሥራ ያመ​ጡ​ትን ስጦታ ሁሉ ይሠሩ ዘንድ ከሙሴ ተቀ​በሉ። እነ​ዚ​ያም እንደ ፈቃ​ዳ​ቸው ማለዳ ማለዳ ስጦ​ታ​ውን ገና ወደ እርሱ ያመጡ ነበር።

ዘፀአት 36:2-3 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ሙሴም ባስልኤልንና ኤልያብን፥ እግዚአብሔርም በልቡ ጥበብን ያደረገለትን በልብ ጥበበኛ ሰው ሁሉ፥ ሥራውንም ለመሥራት ይቀርብ ዘንድ ልቡ ያስነሣውን ሁሉ ጠራቸው። እነርሱም የእስራኤል ልጆች ለመቅደስ ማገልገያ ሥራ ያመጡትን ስጦታ ሁሉ ይሠሩ ዘንድ ከሙሴ ተቀበሉ። እነዚያም እንደ ፈቃዳቸው ማለዳ ማለዳ ስጦታውን ገና ወደ እርሱ ያመጡ ነበር።

ዘፀአት 36:2-3 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ሙሴም ባስልኤልን፥ ኤልያብንና ጌታ በልቡ ጥበብን ያሳደረበትን ጥበበኛ ሰው ሁሉ፥ ሥራውን ለመሥራት ልቡ ያነሣሣውን ሁሉ ጠራቸው። የመቅደሱን ሥራ ለመሥራት የእስራኤል ልጆች ያመጡትን ስጦታ ሁሉ ከሙሴ ወሰዱ። እነዚያም በፈቃዳቸው የሚያቀርቡትን ስጦታ አሁንም ማለዳ ማለዳ ወደ እርሱ ያመጡ ነበር።