ዘፀአት 29:38 - Compare All Versions

ዘፀአት 29:38 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

“በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ የም​ታ​ቀ​ር​በው ይህ ነው፤ በቀን በቀን ዘወ​ትር በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ሁለት ንጹ​ሓን የዓ​መት ጠቦ​ቶች ታቀ​ር​ባ​ለህ።

ዘፀአት 29:38 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

“በየዕለቱ ያለ ማቋረጥ በመሠዊያው ላይ የምታቀርበው ይህ ነው፤ ዓመት የሞላቸው ሁለት የበግ ጠቦቶች፤

ዘፀአት 29:38 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

በመሠዊያውም ላይ የምታቀርበው ይህ ነው፤ በቀን በቀን ዘወትር ሁለት የዓመት ጠቦቶች ታቀርባለህ።

ዘፀአት 29:38 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

“በሚመጡት ዘመናት ሁሉ በየዕለቱ አንድ ዓመት የሆናቸው ሁለት ጠቦቶች መሥዋዕት አድርገህ በመሠዊያው ላይ ታቀርባለህ፤

ዘፀአት 29:38 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

“በመሠዊያው ላይ የምታቀርበው ይህ ነው፤ በየቀኑ ዘወትር ሁለት የአንድ ዓመት ጠቦቶች ታቀርባለህ።