ዘፀአት 21:23-25
ዘፀአት 21:23-25 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ነገር ግን ሴትዮዋ ራስዋ ብርቱ ጒዳት የደረሰባት ከሆነች ቅጣቱ ‘በሕይወት ምትክ ሕይወት፥ በዐይን ምትክ ዐይን፥ በጥርስ ምትክ ጥርስ፥ በእጅ ምትክ እጅ፥ በእግር ምትክ እግር፥ በቃጠሎ ምትክ ቃጠሎ፥ በቊስል ምትክ ቊስል፥ በመፈንከት ምትክ መፈንከት’ በሚለው ሕግ መሠረት ይወሰን።
ያጋሩ
ዘፀአት 21 ያንብቡዘፀአት 21:23-25 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ተሥዕሎተ መልክእ የተፈጸመለት ፅንስ ቢያስወርዳት ግን ሕይወት በሕይወት፥ ዐይን በዐይን፥ ጥርስ በጥርስ፥ እጅ በእጅ፥ እግር በእግር፥ መቃጠል በመቃጠል፥ ቍስል በቍስል፥ ግርፋት በግርፋት ይክፈል።
ያጋሩ
ዘፀአት 21 ያንብቡዘፀአት 21:23-25 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ነገር ግን የከፋ ጕዳት ቢደርስ ሕይወት በሕይወት፣ ዐይን በዐይን፣ ጥርስ በጥርስ፣ እጅ በእጅ፣ እግር በእግር፣ ቃጠሎ በቃጠሎ፣ ቍስል በቍስል፣ ግርፋት በግርፋት ታስከፍላለህ።
ያጋሩ
ዘፀአት 21 ያንብቡዘፀአት 21:23-25 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ጕዳት ግን ቢያገኛት ሕይወት በሕይወት፥ ዓይን በዓይን፥ ጥርስ በጥርስ፥ እጅ በእጅ፥ እግር በእግር፥ መቃጠል በመቃጠል፥ ቍስል በቍስል፥ ግርፋት በግርፋት ይከፈል።
ያጋሩ
ዘፀአት 21 ያንብቡ