ዘፀአት 20:1-7

ዘፀአት 20:1-7 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይህን ቃል ሁሉ እን​ዲህ ብሎ ተና​ገረ፦ “ከግ​ብፅ ምድር ከባ​ር​ነት ቤት ያወ​ጣ​ሁህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ እኔ ነኝ፤ “ከእኔ በቀር ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት አታ​ም​ልክ። “በላይ በሰ​ማይ ከአ​ለው፥ በታ​ችም በም​ድር ከአ​ለው፥ ከም​ድ​ርም በታች በውኃ ከአ​ለው ነገር የማ​ና​ቸ​ው​ንም ምስል ለአ​ንተ አም​ላክ አታ​ድ​ርግ። አት​ስ​ገ​ድ​ላ​ቸው፤ አታ​ም​ል​ካ​ቸ​ውም፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ ቀና​ተኛ አም​ላክ ነኝና። በሚ​ጠ​ሉኝ እስከ ሦስ​ተ​ኛና አራ​ተኛ ትው​ልድ ድረስ የአ​ባ​ቶ​ችን ኀጢ​አት በል​ጆች ላይ የማ​መጣ፤ ለሚ​ወ​ድ​ዱኝ፥ ትእ​ዛ​ዜ​ንም ለሚ​ጠ​ብቁ እስከ ሺህ ትው​ልድ ድረስ ምሕ​ረ​ትን የማ​ደ​ርግ አም​ላክ ነኝና። “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የአ​ም​ላ​ክ​ህን ስም በከ​ንቱ አት​ጥራ፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስሙን በከ​ንቱ የሚ​ጠ​ራ​ውን ከበ​ደል አያ​ነ​ጻ​ው​ምና።