ዘፀአት 20:1-3 - Compare All Versions

ዘፀአት 20:1-3 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

እግዚአብሔር እነዚህን ቃሎች ሁሉ እንዲህ ብሎ ተናገረ፤ “ከግብጽ ከባርነት ምድር ያወጣሁህ አምላክህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ። “ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይኑሩህ።

ዘፀአት 20:1-3 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

እግዚአብሔር እነዚህን ትእዛዞች ሁሉ ለሕዝቡ ተናገረ፥ “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! በባርነት ከምትኖርባት ከግብጽ ምድር ያወጣሁህ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝ፤ “ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ አታምልክ፤

ዘፀአት 20:1-3 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይህን ቃል ሁሉ እን​ዲህ ብሎ ተና​ገረ፦ “ከግ​ብፅ ምድር ከባ​ር​ነት ቤት ያወ​ጣ​ሁህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ እኔ ነኝ፤ “ከእኔ በቀር ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት አታ​ም​ልክ።

ዘፀአት 20:1-3 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

እግዚአብሔርም ይህን ቃል ሁሉ እንዲህ ብሎ ተናገረ፦ ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ። ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ።

ዘፀአት 20:1-3 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

እግዚአብሔርም እነዚህን ቃሎች ሁሉ እንዲህ ሲል ተናገረ፦ “ከግብጽ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣሁህ ጌታ አምላክህ እኔ ነኝ። “ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይኑሩህ።