ዘፀአት 2:3 - Compare All Versions

ዘፀአት 2:3 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ደግ​ሞም ሊሸ​ሽ​ጉት በአ​ል​ቻሉ ጊዜ እናቱ የደ​ን​ገል ሣጥን ለእ​ርሱ ወስዳ ዝፍ​ትና ቅጥ​ራን ለቀ​ለ​ቀ​ችው፤ ሕፃ​ኑ​ንም አኖ​ረ​ች​በት፤ በወ​ን​ዝም ዳር ባለ በቄ​ጠማ ውስጥ አስ​ቀ​መ​ጠ​ችው።

ዘፀአት 2:3 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ከዚያ በላይ ልትሸሽገው ባልቻለች ጊዜ ግን የደንገል ቅርጫት ወስዳ፣ በዝፍትና በቅጥራን ለቀለቀችው፤ ሕፃኑንም በውስጡ አስተኝታ ቅርጫቱን አባይ ወንዝ ዳር ቄጠማ መካከል አስቀመጠችው።

ዘፀአት 2:3 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ደግሞም ልትሸሽገው ባልቻለች ጊዜ፥ የደንገል ሣጥን ለእርሱ ወስዳ ዝፍትና ቅጥራን ለቀለቀችው፤ ሕፃኑንም አኖረችበት፤ በወንዝም ዳር ባለ በቄጠማ ውስጥ አስቀመጠችው።

ዘፀአት 2:3 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ሆኖም ከዚያ በላይ ልትሸሽገው አለመቻልዋን በተረዳች ጊዜ፥ በሣጥን መልክ ከደንገል የተሠራ ቅርጫት አዘጋጀች፤ ውሃም እንዳያስገባ በቅጥራን ለቀለቀችው፤ ሕፃኑንም አስገብታ ቅርጫቱን በወንዝ ዳር በሚገኝ ቀጤማ መካከል አስቀመጠችው።

ዘፀአት 2:3 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ደግሞም ልትሸሽገው ባልቻለች ጊዜ፥ የደንገል ሣጥን ለእርሱ ወስዳ ዝፍትና ቅጥራን ለቀለቀችው፤ ሕፃኑንም እዚያ ውስጥ አስገባችው፥ በወንዝም ዳር ባለ በቄጠማ ውስጥ አስቀመጠችው።