ዘፀአት 2:23 - Compare All Versions

ዘፀአት 2:23 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ከዚ​ያም ከብዙ ቀን በኋላ እን​ዲህ ሆነ፤ የግ​ብፅ ንጉሥ ሞተ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከባ​ር​ነት የተ​ነሣ አለ​ቀሱ፤ ጮኹም፤ ስለ ባር​ነ​ታ​ቸ​ውም ጩኸ​ታ​ቸው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወጣ።

ዘፀአት 2:23 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ከብዙ ዓመት በኋላ የግብጽ ንጉሥ ሞተ፤ እስራኤላውያንም በባርነት ከደረሰባቸው ግፍ የተነሣ ይጮኹ ነበር፤ ከባርነት ቀንበር ለመላቀቅ ያሰሙትም ጩኸት ወደ እግዚአብሔር ደረሰ።

ዘፀአት 2:23 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ከዚያም ከብዙ ቀን በኋላ እንዲህ ሆነ፤ የግብፅ ንጉሥ ሞተ፤ የእስራኤልም ልጆች ከባርነት የተነሣ አለቀሱ፤ ጮኹም፤ ስለባርነታቸውም ጩኸታቸው ወደ እግዚአብሔር ወጣ።

ዘፀአት 2:23 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ከብዙ ዓመቶች በኋላ የግብጽ ንጉሥ ሞተ፤ እስራኤላውያን ግን አሁንም በባርነት ቀንበር ሥር በመጨነቅ ርዳታ ለማግኘት በመጮኽ ላይ ነበሩ፤ ጩኸታቸውም ወደ እግዚአብሔር ደረሰ።

ዘፀአት 2:23 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ከብዙ ቀኖች በኋላ የግብጽ ንጉሥ ሞተ፤ የእስራኤልም ሕዝቦች ከባርነት የተነሣ አለቀሱ፥ ጮኹም፥ ስለባርነታቸውም የልመና ጩኸታቸው ወደ እግዚአብሔር ወጣ።