ዘፀአት 17:1-16

ዘፀአት 17:1-16 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘዘ ከሲን ምድረ በዳ ሊጓዙ ተነሡ፤ በራ​ፊ​ድም ሰፈሩ፤ በዚ​ያም ሕዝቡ የሚ​ጠ​ጡት ውኃ አል​ነ​በ​ረም። ሕዝ​ቡም ሙሴን ተጣ​ሉት፥ “የም​ን​ጠ​ጣ​ውን ውኃ ስጠን” አሉ። ሙሴም፥ “ለምን ትጣ​ሉ​ኛ​ላ​ችሁ? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንስ ለምን ትፈ​ታ​ተ​ና​ላ​ችሁ?” አላ​ቸው። ሕዝ​ቡም በዚያ ስፍራ ውኃ ተጠሙ፥ “እኛ​ንና ልጆ​ቻ​ች​ንን፥ ከብ​ቶ​ቻ​ች​ን​ንም በጥ​ማት ልት​ገ​ድል ለምን ከግ​ብፅ አወ​ጣ​ኸን?” ሲሉ በሙሴ ላይ አን​ጐ​ራ​ጐሩ። ሙሴም፦ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ለዚህ ሕዝብ ምን ላድ​ርግ? በድ​ን​ጋይ ሊወ​ግ​ሩኝ ጥቂት ቀር​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና።” እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “በሕ​ዝቡ ፊት እለፍ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችን ከአ​ንተ ጋር ውሰድ፤ ወን​ዙ​ንም የመ​ታ​ህ​ባ​ትን በትር በእ​ጅህ ይዘ​ሃት ሂድ። እነሆ፥ እኔ በዚያ በኮ​ሬብ በዓ​ለት ላይ በፊ​ትህ እቆ​ማ​ለሁ፤ ዓለ​ቱ​ንም ትመ​ታ​ለህ፤ ሕዝ​ቡም ይጠጣ ዘንድ ከእ​ርሱ ውኃ ይወ​ጣል” አለው። ሙሴም በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት እን​ዲሁ አደ​ረገ። ስለ እስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ክር​ክር፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ካ​ከ​ላ​ችን ነውን? ወይስ አይ​ደ​ለም?” ሲሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ ተፈ​ታ​ተ​ኑት የዚ​ያን ስፍራ ስም “መን​ሱት” ደግ​ሞም “ጋእዝ” ብሎ ጠራው። ዐማ​ሌ​ቅም መጥቶ ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋራ በራ​ፊድ ተዋጋ። ሙሴም ኢያ​ሱን፥ “ጐል​ማ​ሶ​ችን ለአ​ንተ ምረጥ፤ ሲነ​ጋም ወጥ​ተህ ከዐ​ማ​ሌቅ ጋር ተዋጋ፤ እኔም በተ​ራ​ራው ራስ ላይ እቆ​ማ​ለሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በትር በእጄ ናት” አለው። ኢያ​ሱም ሙሴ እንደ አለው አደ​ረገ፤ ወጥ​ቶም ከዐ​ማ​ሌቅ ጋር ተዋጋ፤ ሙሴና አሮን፥ ሖርም ወደ ኮረ​ብ​ታው ራስ ወጡ። እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ሙሴ እጁን በአ​ነሣ ጊዜ እስ​ራ​ኤል ድል ያደ​ርግ ነበር ፤ እጁ​ንም በአ​ወ​ረደ ጊዜ ዐማ​ሌቅ ድል ያደ​ርግ ነበር። የሙሴ እጆች ግን ከብ​ደው ነበር፤ ድን​ጋ​ይም ወሰዱ፤ በበ​ታ​ቹም አኖሩ፤ እር​ሱም ተቀ​መ​ጠ​በት፤ አሮ​ንና ሖርም አንዱ በዚህ አንዱ በዚያ ሆነው እጆ​ቹን ይደ​ግፉ ነበር፤ ፀሐ​ይም እስ​ክ​ት​ገባ ድረስ እጆቹ ተዘ​ር​ግ​ተው ነበር። ኢያ​ሱም ዐማ​ሌ​ቅ​ንና ሕዝ​ቡን በሰ​ይፍ ስለት አሸ​ነፈ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “የዐ​ማ​ሌ​ቅን ዝክር ከሰ​ማይ በታች ጨርሼ እደ​መ​ስ​ሳ​ለ​ሁና ይህን ለመ​ታ​ሰ​ቢያ በመ​ጽ​ሐፍ ጻፈው፤ በኢ​ያ​ሱም ጆሮ ተና​ገር” አለው። ሙሴም መሠ​ዊያ ሠራ፤ ስሙ​ንም “ምም​ሕ​ፃን” ብሎ ጠራው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በተ​ሰ​ወ​ረች እጅ ዐማ​ሌ​ቅን እስከ ልጅ ልጅ ይዋ​ጋ​ልና።

ዘፀአት 17:1-16 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

መላው የእስራኤል ማኅበር ከሲና ምድረ በዳ ተነሥቶ እግዚአብሔር እንዳዘዘው ከስፍራ ወደ ስፍራ ተጕዞ በራፊዲም ሰፈረ፤ ነገር ግን ሕዝቡ የሚጠጡት ውሃ አልነበረም። ስለዚህ፣ “የምንጠጣውን ውሃ ስጠን” በማለት ሙሴን ተጣሉት። ሙሴም፣ “እኔን ለምን ትጣሉኛላችሁ? እግዚአብሔርንስ ለምን ትፈታተኑታላችሁ?” አለ። ነገር ግን ሕዝቡ በዚያ ተጠምተው ስለ ነበር፣ በሙሴ ላይ አጕረመረሙ። እነርሱም፣ “እኛና ልጆቻችን እንዲሁም ከብቶቻችን በውሃ ጥም እንድናልቅ፣ ከግብጽ ለምን አወጣኸን?” አሉት። ከዚያም ሙሴ፤ “በዚህ ሕዝብ ምን ላድርግ? በድንጋይ ሊወግሩኝ ተዘጋጅተዋል” ብሎ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ። እግዚአብሔር ለሙሴ እንዲህ መለሰለት፤ “ከሕዝቡ ፊት ሂድ፤ ከእስራኤል አለቆች አንዳንዶቹን እንዲሁም አባይን የመታህባትን በትር ያዝና ሂድ። ኮሬብ አጠገብ ባለው ዐለት በዚያ እኔ በአንተ ፊት እቆማለሁ። ዐለቱን ምታው፤ ከርሱም ሕዝቡ የሚጠጡት ውሃ ይወጣል።” ስለዚህ ሙሴ በእስራኤል አለቆች ፊት ይህንኑ አደረገ። ስፍራውንም ማሳህና መሪባ ብሎ ጠራው፤ እስራኤላውያን ጠብ ፈጥረው፣ “እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ነው ወይስ አይደለም” በማለት እግዚአብሔርን ተፈታትነዋልና። አማሌቃውያን መጥተው እስራኤላውያንን ራፊዲም ላይ ወጉ፤ ሙሴም ኢያሱን፣ “ከሰዎቻችን አንዳንዶቹን ምረጥና አማሌቃውያንን ለመውጋት ውጣ፤ በነገው ዕለት የእግዚአብሔርን በትር በእጆቼ ይዤ በኰረብታው ጫፍ ላይ እቆማለሁ።” ስለዚህ ኢያሱ ሙሴ ባዘዘው መሠረት ከአማሌቃውያን ጋራ ተዋጋ፤ ሙሴ፣ አሮንና ሖርም ወደ ኰረብታው ጫፍ ወጡ። ሙሴ እጆቹን ወደ ላይ በሚያነሣበት ጊዜ ሁሉ እስራኤላውያን ድል ያደርጉ ነበር። እጆቹን ባወረደ ጊዜ ግን አማሌቃውያን ያሸንፉ ነበር። የሙሴ እጆች እየዛሉ በሄዱ ጊዜ ድንጋይ ወስደው ከበታቹ አደረጉ፤ እርሱም ተቀመጠበት፤ አሮንና ሖርም አንዱ በአንዱ በኩል ሌላውም በሌላ በኩል ሆነው እጆቹን ወደ ላይ ያዙ። ይኸውም እጆቹ ፀሓይ እስክትጠልቅ ድረስ ጸንተው እንዲቈዩ ነው። ስለዚህ ኢያሱ የአማሌቃውያንን ሰራዊት በሰይፍ ድል አደረገ። ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን፣ “ሲታወስ እንዲኖር ይህን በጥቅልል መጽሐፍ ላይ ጻፈው፤ ኢያሱም መስማቱን አረጋግጥ፤ ምክንያቱም የአማሌቃውያንን ዝክር ከሰማይ በታች ፈጽሜ እደመስሳለሁ” አለው። ሙሴም መሠዊያውን ሠርቶ፣ “እግዚአብሔር ዐርማዬ ነው” ብሎ ሰየመው። “እጆች ወደ እግዚአብሔር ዙፋን ተዘርግተዋልና፤ እግዚአብሔር አማሌቃውያንን ከትውልድ እስከ ትውልድ ይዋጋቸዋል” አለ።

ዘፀአት 17:1-16 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ እግዚአብሔር እንዳዘዘ ከሲን ምድረ በዳ ሊጓዙ ተነሡ፥ በራፊዲምም ሰፈሩ፤ ሕዝቡም ይጠጡ ዘንድ ውኃ አልነበረም። ሕዝቡም ሙሴን ተጣሉት፦ የምንጠጣውን ውኃ ስጠን አሉት። ሙሴም፦ ለምን ትጣሉኛላችሁ? እግዚአብሔርንስ ለምን ትፈታተናላችሁ? አላቸው። ሕዝቡም በዚያ ስፍራ ውኃ ተጠሙ፦ እኛንና ልጆቻችንን ከብቶቻችንንም በጥማት ልትገድል ለምን ከግብፅ አወጣኽን? ሲሉ በሙሴ ላይ አንጎራጎሩ። ሙሴም፦ ሊወግሩኝ ቀርበዋልና በዚህ ሕዝብ ምን ላድርግ? ብሎ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ። እግዚአሔርም ሙሴን፦ በሕዝቡ ፊት እለፍ፥ ከእስራኤልም ሽማግሌዎች ከአንተ ጋር ውሰድ፤ ወንዙንም የመታህባትን በትር በእጅህ ይዘሃት ሂድ። እነሆ እኔ በዚያ በኮሬብ በዓለት ላይ በፊትህ እቆማለሁ፤ ዓለቱንም ትመታለህ፥ ሕዝቡም ይጠጣ ዘንድ ከእርሱ ውኃ ይወጣል አለው። ሙሴም በእስራኤል ሽማግሌዎች ፊት እንዲሁ አደረገ። ስለ እስራኤልም ልጆች ክርክር፦ እግዚአብሔር በመካከላችን ነውን ወይስ አይደለም? ሲሉ እግዚአብሔርን ስለተፈታተኑት የዚያን ስፍራ ስም ማሳህ፥ ደግሞም መሪባ ብሎ ጠራው። አማሌቅም መጥቶ ከእስራኤል ጋር በራፊድም ተዋጋ። ሙሴም ኢያሱን፦ ጕልማሶችን ምረጥልን፥ ወጥተህም ከአማሌቅ ጋር ተዋጋ፤ እኔ ነገ የእግዚአብሔርን በትር በእጄ ይዤ በኮረብታው ራስ ላይ እቆማለሁ አለው። ኢያሱም ሙሴ እንዳለው አደረገ፥ ከአማሌቅም ጋር ተዋጋ፤ ሙሴና አሮንም ሖርም ወደ ኮረብታው ራስ ወጡ። እንዲህም ሆነ፤ ሙሴ እጁን ባነሣ ጊዜ እስራኤል ድል ያደርግ ነበር፤ እጁንም ባወረደ ጊዜ አማሌቅ ድል ያደርግ ነበር። የሙሴ እጆች ግን ከብደው ነበር፤ ድንጋይም ወሰዱ፥ በበታቹም አኖሩ፥ እርሱም ተቀመጠበት፤ አሮንና ሖርም አንዱ በዚህ አንዱ በዚያ ሆነው እጆቹን ይደግፉ ነበር፤ ፀሐይም እስክትገባ ድረስ እጆቹ ጠነከሩ። ኢያሱም አማሌቅንና ሕዝቡን በሰይፍ ስለት አሸነፈ። እግዚአብሔርም ሙሴን፦ የአማሌቅን ዝክር ከሰማይ በታች ጨርሼ እደመስሳለሁና ይህን ለመታሰቢያ በመጽሐፍ ጻፈው፥ በኢያሱም ጆሮ ተናገር አለው። ሙሴም መሠዊያ ሠራ፥ ስሙንም ይህዌህ ንሲ ብሎ ጠራው፤ እርሱም፦ እጁን በእግዚአብሔር ዙፋን ላይ ስለጫነ የእግዚአብሔር ሰልፍ በአማሌቅ ላይ ለልጅ ልጅ ይሁን አለ።

ዘፀአት 17:1-16 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

መላው የእስራኤል ሕዝብ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ከቦታ ወደ ቦታ በመዘዋወር “ሲን” ተብሎ የሚጠራውን ምድረ በዳ ትተው በረፊዲም ሰፈሩ፤ ነገር ግን በዚያ የሚጠጣ ውሃ አልነበረም። ስለዚህም “የምንጠጣው ውሃ ስጠን” ብለው በሙሴ ላይ አጒረመረሙ። ሙሴም “ስለምን ትወቅሱኛላችሁ? ስለምንስ እግዚአብሔርን ትፈታተናላችሁ?” አላቸው። ሕዝቡ ግን እጅግ ተጠምተው ስለ ነበር “ከግብጽ ምድር ያወጣኸን ለምንድን ነው? እኛንና ልጆቻችንን እንስሶቻችንንም ጭምር በውሃ ጥም ለመፍጀት ነውን?” እያሉ በሙሴ ላይ ማጒረምረማቸውን ቀጠሉ። ሙሴም “ከቶ ይህን ሕዝብ ምን ባደርገው ይሻላል? እነሆ፥ በድንጋይ ሊወግሩኝ ተዘጋጅተዋል” እያለ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ። እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ከእስራኤል ሕዝብ አለቆች፥ ጥቂቶቹን ውሰድ፤ ከሕዝቡም ቀድመህ ወደ ፊት ሂድ፤ የዐባይን ወንዝ የመታህበትንም በትር በእጅህ ያዝ፤ እነሆ፥ እኔ በሲና ተራራ በአለት ላይ በፊትህ እቆማለሁ፤ አንተም አለቱን ምታው፤ ሕዝቡም የሚጠጡት ውሃ ከውስጡ ይፈልቃል፤” ሙሴም በእስራኤል አለቆች ፊት እንደዚሁ አደረገ። እስራኤላውያን “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው ወይስ አይደለም?” በማለት በማጒረምረማቸውና እግዚአብሔርን በመፈታተናቸው ያ ስፍራ ማሳህና እና መሪባ ተብሎ ተጠራ። እስራኤላውያን በረፊዲም ሳሉ ዐማሌቃውያን መጥተው አደጋ ጣሉባቸው፤ ሙሴም ኢያሱን “ጥቂት ሰዎች ምረጥና በነገው ዕለት ዐማሌቃውያንን ውጋ፤ እኔም ተአምራት እንድፈጽምባት እግዚአብሔር የሰጠኝን በትር ይዤ በኮረብታው ጫፍ ላይ እቆማለሁ” አለው። ኢያሱም የሙሴን ትእዛዝ በመፈጸም ዐማሌቃውያንን ለመውጋት ወጣ፤ ሙሴ፥ አሮንና ሑር ወደ ኮረብታው ጫፍ ወጡ፤ ሙሴ እጆቹን ወደ ሰማይ በዘረጋ ጊዜ እስራኤላውያን ድል ያደርጉ ነበር፤ እጆቹን ባጠፈ ጊዜ ግን ዐማሌቃውያን እንደገና አንሰራርተው ያሸንፉ ነበር። የሙሴ እጆች ስለ ዛሉ አሮንና ሑር ድንጋይ አምጥተው ሙሴ እንዲቀመጥበት አደረጉ፤ በግራና በቀኝ ክንዶቹን ደግፈው በመቆም ፀሐይ እስከምትጠልቅበት ጊዜ ድረስ ቈዩ። በዚህ ሁኔታ ኢያሱ ዐማሌቃውያንን በሰይፍ ጠራርጎ አጠፋ። ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን “ዘወትር ሲታወስ እንዲኖር የዚህን ድል ታሪክ ጻፈው፤ ለኢያሱም ዐማሌቃውያንን ከምድር ጨርሼ የማጠፋቸው መሆኔን ንገረው” አለው። ሙሴም መሠዊያ ሠርቶ “እግዚአብሔር የድል ሰንደቅ ዓላማዬ ነው” ብሎ ሰየመው፤ እንዲህም አለ “የእግዚአብሔርን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ አድርጋችሁ ያዙ! እግዚአብሔር ዐማሌቃውያንን ለዘለዓለም ይዋጋቸዋል።”

ዘፀአት 17:1-16 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

የእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ ጌታ እንዳዘዘ ሊጓዙ ከሲን ምድረ በዳ ተነሡ፥ በረፊዲምም ሰፈሩ፤ ሕዝቡ የሚጠጡት ውኃ አልነበረም። ሕዝቡም ሙሴን ተጣሉት፦ “የምንጠጣውን ውኃ ስጠን” አሉት። ሙሴም፦ “ለምን ትጣሉኛላችሁ? ጌታንስ ለምን ትፈታተናላችሁ?” አላቸው። ሕዝቡም በዚያ ስፍራ ውኃ ተጠሙ፥ ሕዝቡም በሙሴ ላይ አጉረመረሙ “እኛንና ልጆቻችንን ከብቶቻችንንም በጥማት ልትገድል ለምን ከግብጽ አወጣኸን?” አሉ። ሙሴም፦ “ይህን ሕዝብ ምን ላድርገው? በድንጋይ ሊወግሩኝ ቀርበዋል” ብሎ ወደ ጌታ ጮኸ። ጌታም ሙሴን፦ በሕዝቡ ፊት እለፍ፥ ከእስራኤልም ሽማግሌዎች ከአንተ ጋር ውሰድ፤ የዓባይን ወንዝ የመታህበትን በትር በእጅህ ይዘህ ሂድ። እነሆ እኔ በዚያ በኮሬብ በዓለት ላይ በፊትህ እቆማለሁ፤ ዓለቱንም ትመታለህ፥ ከእርሱ ውኃ ይወጣል፥ ሕዝቡም ከእርሱ ይጠጣል አለው። ሙሴም በእስራኤል ሽማግሌዎች ፊት እንዲሁ አደረገ። እርሱም የዚያን ስፍራ ስም ማሳህና መሪባ ብሎ ጠራው፥ ይህም ስለ እስራኤል ልጆች ጥልና “ጌታ በመካከላችን ነው ወይስ አይደለም?” በማለት ጌታን ስለተፈታተኑት ነው። አማሌቅም መጥቶ በረፊድም ከእስራኤል ጋር ተዋጋ። ሙሴም ኢያሱን፦ “ሰዎችን ምረጥልን፥ ከአማሌቅም ጋር ለመዋጋትም ውጣ፤ እኔ ነገ የእግዚአብሔርን በትር በእጄ ይዤ በኮረብታው ጫፍ ላይ እቆማለሁ” አለው። ኢያሱም ሙሴ እንዳለው አደረገ፥ ከአማሌቅም ጋር ተዋጋ፤ ሙሴ፥ አሮንና ሑር ወደ ኮረብታው ጫፍ ወጡ። እንዲህም ሆነ ሙሴ እጁን ባነሣ ጊዜ እስራኤል ይበረታ ነበር፤ እጁንም ባወረደ ጊዜ አማሌቅ ይበረታ ነበር። የሙሴ እጆች ግን ዝለው ነበር፤ ድንጋይም ወሰዱ፥ በበታቹም አኖሩ፥ እርሱም ተቀመጠበት፤ አሮንና ሑርም አንዱ በዚህ አንዱ በዚያ ሆነው እጆቹን ያዙ፤ ፀሐይም እስክትገባ ድረስ እጆቹ ቀጥ አሉ። ኢያሱም ዓማሌቅንና ሕዝቡን በሰይፍ ስለት አሸነፈ። ጌታም ሙሴን፦ “ይህንን ለመታሰቢያ በመጽሐፍ ጻፈው፥ በኢያሱም ጆሮ አኑረው፥ የአማሌቅን መታሰቢያ ከሰማይ በታች ጨርሼ እደመስሳለሁና” አለው። ሙሴም መሠዊያ ሠራ፥ ስሙንም “ጌታ ሰንደቅ ዓላማዬ ነው” ብሎ ጠራው፤ እርሱም፦ “እጅ በጌታ ዙፋን ላይ ስለጫነ የጌታ ሰልፍ በአማሌቅ ላይ ከትውልድ እስከ ትውልድ ይሁን አለ።”