ዘፀአት 15:11 - Compare All Versions

ዘፀአት 15:11 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

አቤቱ፦ በአ​ማ​ል​ክት መካ​ከል አን​ተን የሚ​መ​ስል ማን ነው? በቅ​ዱ​ሳ​ንም ዘንድ እንደ አንተ የከ​በረ ማን ነው? በም​ስ​ጋና የተ​ደ​ነ​ቅህ ነህ፤ ድን​ቅ​ንም የም​ታ​ደ​ርግ ነህ፤

ዘፀአት 15:11 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፤ ከአማልክት መካከል፣ እንደ አንተ ማን አለ? በቅድስናው የከበረ፣ በክብሩ የሚያስፈራ፣ ድንቆችን የሚያደርግ፣ እንደ አንተ ማን አለ?

ዘፀአት 15:11 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

አቤቱ፥ በአማልክት መካከል እንደ አንተ ያለ ማን ነው? በምስጋና የተፈራህ፥ ድንቅንም የምታደርግ፥ በቅድስና የከበረ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?

ዘፀአት 15:11 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

“አምላክ ሆይ፥ ከአማልክት መካከል አንተን የሚመስል ማን ነው? በቅድስናስ እንደ አንተ ያለ ባለግርማ ማን ነው? አንተ ያደረግሃቸውን ተአምራትና አስገራሚ ሥራዎች ሊያደርግ የሚችልስ ማን አለ?

ዘፀአት 15:11 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ከአማልክት መካከል ጌታ ሆይ፥ እንደ አንተ ያለ ማን ነው? በቅድስና ባለግርማ፥ በምስጋና የተፈራህ፥ ድንቅንም የምታደርግ፥ እንደ አንተ ያለ ማን ነው?