ዘፀአት 10:1-2
ዘፀአት 10:1-2 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፥ “ወደ ፈርዖን ግባ፤ እኔ የፈርዖንንና የሹሞቹን ልብ አጽንቼአለሁና፥ ተአምራቴ በእነርሱ ላይ በትክክል ይመጣ ዘንድ፤ በግብፃውያንም ላይ የተዘባበትሁትን ሁሉ፥ ያደረግሁባቸውንም ተአምራቴን በልጆቻችሁና በልጅ ልጆቻችሁ ጆሮች ትነግሩ ዘንድ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።”
ያጋሩ
ዘፀአት 10 ያንብቡዘፀአት 10:1-2 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ተመልሰህ ወደ ፈርዖን ሂድ፤ እነዚህን ታምራዊ ምልክቶች በመካከላቸው ለማድረግ የፈርዖንንና የሹማምቱን ልብ አደንድኛለሁና፤ ይኸውም ግብጻውያንን እንዴት አድርጌ እንደ ቀጣኋቸውና በመካከላቸውም ምልክቶቼን እንዴት እንዳደረግሁ ለልጆቻችሁና ለልጅ ልጆቻችሁ እንድትነግሩና እኔ እግዚአብሔር መሆኔንም እንድታውቁ ነው።”
ያጋሩ
ዘፀአት 10 ያንብቡዘፀአት 10:1-2 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ወደ ፈርዖን ግባ፤ በመካከላቸው እነዚህን ተአምራት ለማድረግ የእርሱንና የባሪያዎቹን ልብ አደንድኛለሁ። ይህንንም ያደረግሁት ለልጆቻችሁና ለልጅ ልጆቻችሁ ግብፃውያንን እንደቀጣሁና ምን ዓይነት ተአምራትን እንዳደረግሁ መንገር ትችሉ ዘንድ ነው፤ በዚህም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።”
ያጋሩ
ዘፀአት 10 ያንብቡ