ኤፌሶን 3:20-21
ኤፌሶን 3:20-21 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ስለዚህ በእኛ ውስጥ በሚሠራው ኀይሉ አማካይነት ከምንለምነውና ከምናስበው በላይ እጅግ አትረፍርፎ ሊያደርግ ለሚቻለው አምላክ፥ ለእርሱ በቤተ ክርስቲያንና በኢየሱስ ክርስቶስ በዘመናት ሁሉ ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ክብር ይሁን፤ አሜን።
ኤፌሶን 3:20-21 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
በከሃሊነቱ እንደ ረዳን መጠን፥ የምናስበውንና የምንለምነውን ሁሉ ትሠሩ ዘንድ፥ ታበዙም ዘንድ ሊያጸናችሁ ለሚችል፥ ለእርሱ በቤተ ክርስቲያን በኢየሱስ ክርስቶስ፥ በትውልድ ሁሉ ምስጋና ይሁን ለዘለዓለሙ አሜን።
ኤፌሶን 3:20-21 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
እንግዲህ በእኛ ውስጥ እንደሚሠራው እንደ ኀይሉ መጠን፣ ከምንለምነው ወይም ከምናስበው ሁሉ በላይ እጅግ አብልጦ ማድረግ ለሚቻለው፣ በቤተ ክርስቲያን እንዲሁም በክርስቶስ ኢየሱስ፣ በዘመናት ሁሉ ከዘላለም እስከ ዘላለም ለርሱ ክብር ይሁን! አሜን።
ኤፌሶን 3:20-21 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እንግዲህ በእኛ እንደሚሠራው ኃይል መጠን ከምንለምነው ወይም ከምናስበው ሁሉ ይልቅ እጅግ አብልጦ ሊያደርግ ለሚቻለው፥ ለእርሱ በቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ኢየሱስ እስከ ትውልዶች ሁሉ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።
ኤፌሶን 3:20-21 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ስለዚህ በእኛ ውስጥ በሚሠራው ኀይሉ አማካይነት ከምንለምነውና ከምናስበው በላይ እጅግ አትረፍርፎ ሊያደርግ ለሚቻለው አምላክ፥ ለእርሱ በቤተ ክርስቲያንና በኢየሱስ ክርስቶስ በዘመናት ሁሉ ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ክብር ይሁን፤ አሜን።