ኤፌሶን 1:3-23

ኤፌሶን 1:3-23 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

በክ​ር​ስ​ቶስ ኢየ​ሱስ በሰ​ማ​ያዊ ስፍራ በመ​ን​ፈ​ሳዊ በረ​ከት ሁሉ የባ​ረ​ከን የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አባት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን። ዓለም ሳይ​ፈ​ጠር በፊቱ ቅዱ​ሳን፥ ንጹ​ሓ​ንና ያለ ነውር በፍ​ቅር ያደ​ር​ገን ዘንድ ለእ​ርሱ መረ​ጠን። በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም እንደ ውድ ፈቃዱ ለእ​ርሱ ልጆች ልን​ሆን አስ​ቀ​ድሞ ወሰ​ነን። በሚ​ወ​ደው ልጁ የሰ​ጠን የጸ​ጋው ክብር ይመ​ሰ​ገን ዘንድ። በእ​ር​ሱም እንደ ቸር​ነቱ ብዛት በደሙ ድኅ​ነ​ትን አገ​ኘን፤ ኀጢ​አ​ታ​ች​ንም ተሰ​ረ​የ​ልን። ይኸ​ውም በፍ​ጹም ጥበ​ብና ምክር ለእኛ አብ​ዝቶ ያደ​ረ​ገው ነው። እንደ ወደ​ደም በእ​ርሱ የወ​ሰ​ነ​ውን፥ የፈ​ቃ​ዱን ምሥ​ጢር ገለ​ጠ​ልን። የሚ​ደ​ር​ስ​በ​ት​ንም ጊዜ​ውን ወሰነ፤ በሰ​ማ​ይና በም​ድር ያለ​ውም ሁሉ ይታ​ደስ ዘንድ ክር​ስ​ቶ​ስን በሁሉ ላይ አላ​ቀው። እንደ ፈቃዱ ምክር ሁሉን የሚ​ሠራ እንደ እርሱ አሳብ አስ​ቀ​ድ​መን የተ​ወ​ሰን በእ​ርሱ ርስ​ትን ተቀ​በ​ልን። ይኸ​ውም አስ​ቀ​ድ​መን በክ​ር​ስ​ቶስ ኢየ​ሱስ ተስፋ ያደ​ረ​ግን እኛ ለክ​ብሩ ምስ​ጋና እን​ሆን ዘንድ ነው። እና​ን​ተም ልት​ድ​ኑ​በት የተ​ማ​ራ​ች​ሁ​ትን የእ​ው​ነት ቃል ሰም​ታ​ች​ሁና አም​ና​ችሁ፤ ተስፋ ባደ​ረ​ገ​ላ​ችሁ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ታተ​ማ​ችሁ። ይኸ​ውም ለጌ​ት​ነቱ ክብር የር​ስ​ታ​ችን መያዣ፥ የሕ​ይ​ወ​ታ​ች​ንም ቤዛ​ነት ነው። ስለ​ዚ​ህም እኔ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ማመ​ና​ች​ሁን፥ ቅዱ​ሳ​ን​ንም ሁሉ መው​ደ​ዳ​ች​ሁን ሰምቼ፥ ስለ እና​ንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማመ​ስ​ገ​ን​ንና በጸ​ሎ​ቴም እና​ን​ተን ማሰ​ብን አላ​ቋ​ረ​ጥ​ሁም። ይኸ​ውም የክ​ብር ባለ​ቤት የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አባቱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የጥ​በ​ብን መን​ፈስ ይሰ​ጣ​ችሁ ዘንድ፥ ዕው​ቀ​ቱ​ንም ይገ​ል​ጽ​ላ​ችሁ ዘንድ፥ ዐይነ ልቡ​ና​ች​ሁ​ንም ያበ​ራ​ላ​ችሁ ዘንድ፥ የተ​ጠ​ራ​ች​ሁ​በት ተስ​ፋም ምን እንደ ሆነ፥ በቅ​ዱ​ሳ​ንም የር​ስቱ ክብር ባለ​ጸ​ግ​ነት ምን እንደ ሆነ ታውቁ ዘንድ፥ በክ​ር​ስ​ቶስ እንደ አደ​ረ​ገው እንደ ከሃ​ሊ​ነቱ ታላ​ቅ​ነት በም​ና​ምን በእኛ ላይ የሚ​ያ​ደ​ር​ገው የከ​ሃ​ሊ​ነቱ ጽናት ብዛት ምን እንደ ሆነ ታውቁ ዘንድ ነው። ከሙ​ታን ለይቶ ባስ​ነ​ሣው፥ በሰ​ማ​ይም በቀኙ ባስ​ቀ​መ​ጠው፥ ከመ​ላ​እ​ክት ሁሉ በላይ ከመ​ኳ​ን​ን​ትና ከኀ​ይ​ላት፥ ከአ​ጋ​እ​ዝ​ትና ከሚ​ጠ​ራ​ውም ስም ሁሉ በላይ፥ በዚህ ዓለም ብቻ አይ​ደ​ለም፤ በሚ​መ​ጣ​ውም ዓለም እንጂ። ሁሉ​ንም ከእ​ግሩ በታች አድ​ርጎ አስ​ገ​ዛ​ለት፤ ከሁሉ በላይ የሆነ እር​ሱን ለቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ራስ አደ​ረ​ገው። ይህ​ች​ውም አካሉ ናት፤ የሁ​ሉም ፍጻ​ሜው እርሱ ነው፤ ሁሉ​ንም በሁሉ ይፈ​ጽ​ማል።

ኤፌሶን 1:3-23 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ በክርስቶስ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ፤ በፊቱ ቅዱስና እንከን አልባ እንድንሆን ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ በርሱ መርጦናልና። በፍቅር፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ልጆቹ እንሆን ዘንድ፣ እንደ በጎ ፈቃዱ አስቀድሞ ወሰነን፤ ይኸውም፣ በሚወድደው በርሱ በኩል በነጻ የተሰጠን ክቡር የሆነው ጸጋው እንዲመሰገን ነው። በርሱም እንደ እግዚአብሔር ጸጋ ባለጠግነት መጠን፣ በደሙ በተደረገ ቤዛነት፣ የኀጢአት ይቅርታ አገኘን፤ ጸጋውንም በጥበብና በማስተዋል ሁሉ አበዛልን። በክርስቶስ ያቀደውንም የፈቃዱን ምስጢር እንደ በጎ ሐሳቡ እንድናውቅ አደረገ። በዘመን ፍጻሜ ይሆን ዘንድ ያለው ሐሳቡ፣ በሰማይም ሆነ በምድር ያሉትን ነገሮች ሁሉ ራስ በሆነው በክርስቶስ ሥር ለመጠቅለል ነው። ሁሉን በፈቃዱ ምክር መሠረት እንደሚሠራው እንደ እርሱ ዕቅድ፣ አስቀድሞ የተወሰንን እኛ ደግሞ በርሱ ተመርጠናል፤ ይኸውም በክርስቶስ ተስፋ በማድረግ የመጀመሪያ የሆንነው እኛ ለክብሩ ምስጋና እንሆን ዘንድ ነው። እናንተም ደግሞ የእውነትን ቃል፣ ይህም የድነታችሁን ወንጌል በሰማችሁ ጊዜ ወደ ክርስቶስ ተጨምራችኋል። አምናችሁም በርሱ በመሆን፣ ተስፋ ሆኖ በተሰጠው በመንፈስ ቅዱስ ማኅተም ታትማችኋል። ለክብሩ ምስጋና ለመሆን የእግዚአብሔር የሆኑት እስኪዋጁ ድረስ፣ እርሱ ለርስታችን ዋስትና የሚሆን መያዣ ነው። ስለዚህ በጌታ ኢየሱስ ስላላችሁ እምነት፣ ለቅዱሳንም ሁሉ ስላላችሁ ፍቅር ከሰማሁበት ጊዜ አንሥቶ፣ በጸሎቴ እያስታወስኋችሁ ስለ እናንተ ምስጋና ማቅረብን አላቋረጥሁም። የክብር አባት የሆነውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክ ይበልጥ እንድታውቁት፣ የጥበብና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣችሁ ያለ ማቋረጥ እለምናለሁ። እንዲሁም በርሱ የተጠራችሁለት ተስፋ፣ ይህም በቅዱሳኑ ዘንድ ያለውን ክቡር የሆነውን የርስቱን ባለጠግነት ምን እንደ ሆነ ታውቁ ዘንድ የልባችሁ ዐይኖች እንዲበሩ ለእኛ ለምናምነውም ከሁሉ በላይ ታላቅ የሆነውን ኀይሉን እንድታውቁ እጸልያለሁ። ይህም ኀይል እንደ እርሱ ታላቅ ብርታት አሠራር፣ ክርስቶስን ከሙታን ሲያስነሣውና በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ ሲያስቀምጠው የታየው ነው። የተቀመጠውም ከግዛትና ከሥልጣን፣ ከኀይልና ከጌትነት እንዲሁም በአሁኑ ዘመን ብቻ ሳይሆን በሚመጣውም ዘመን ቢሆን ሊሰየም ከሚቻለው ስም ሁሉ በላይ ነው። እግዚአብሔርም ሁሉን ከእግሩ በታች አስገዛለት፤ በቤተ ክርስቲያንም በማንኛውም ነገር ላይ ራስ አድርጎ ሾመው። እርሷም ሁሉን ነገር በሁሉም ረገድ የሚሞላው፣ የርሱ ሙላት የሆነች አካሉ ናት።

ኤፌሶን 1:3-23 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

በክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ። ዓለም ሳይፈጠር፥ በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን። በበጎ ፈቃዱ እንደ ወደደ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ለእርሱ ልጆች ልንሆን አስቀድሞ ወሰነን። በውድ ልጁም እንዲያው የሰጠን የጸጋው ክብር ይመሰገን ዘንድ ይህን አደረገ። በውድ ልጁም፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፥ በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት። ጸጋውንም በጥበብና በአእምሮ ሁሉ አበዛልን። በክርስቶስ ለማድረግ እንደ ወደደ እንደ አሳቡ፥ የፈቃዱን ምሥጢር አስታውቆናልና፤ በዘመን ፍጻሜ ይደረግ ዘንድ ያለው አሳቡም በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል ነው። እንደ ፈቃዱ ምክር ሁሉን የሚሠራ እንደ እርሱ አሳብ፥ አስቀድመን የተወሰንን በክርስቶስ ደግሞ ርስትን ተቀበልን። ይኸውም፥ በክርስቶስ አስቀድመን ተስፋ ያደረግን እኛ ለክብሩ ምስጋና እንሆን ዘንድ ነው። እናንተም ደግሞ የእውነትን ቃል፥ ይኸውም የመዳናችሁን ወንጌል፥ ሰምታችሁ ደግሞም በክርስቶስ አምናችሁ፥ በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ፤ እርሱም የርስታችን መያዣ ነው፥ ለእግዚአብሔር ያለውን ሁሉ እስኪዋጅ ድረስ፥ ይህም ለክብሩ ምስጋና ይሆናል። ስለዚህ እኔ ደግሞ በእናንተ ዘንድ ስለሚሆን በጌታ በኢየሱስ ስለ ማመንና ለቅዱሳን ሁሉ ስለሚሆን መውደድ ሰምቼ፥ ስለ እናንተ እያመሰገንሁ ስጸልይ ስለ እናንተ ማሳሰብን አልተውም፤ የክብር አባት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እርሱን በማወቅ የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣችሁ እለምናለሁ። ይህም የልባችሁ ዓይኖች ሲበሩ የመጥራቱ ተስፋ ምን እንዲሆን በቅዱሳንም ዘንድ ያለው የርስት ክብር ባለ ጠግነት ምን እንዲሆን ለምናምን ከሁሉ የሚበልጥ የኃይሉ ታላቅነት ምን እንዲሆን ታውቁ ዘንድ ነው፤ ክርስቶስንም ከሙታን ሲያስነሣው ከአለቅነትና ከሥልጣንም ከኃይልም ከጌትነትም ሁሉ በላይና በዚህ ዓለም ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ሊመጣ ባለው ዓለም ደግሞ ከሚጠራው ስም ሁሉ በላይ በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ ሲያስቀምጠው በክርስቶስ ባደረገው ሥራ የብርታቱ ጉልበት ይታያል፤ ሁሉንም ከእግሩ በታች አስገዛለት ከሁሉ በላይም ራስ እንዲሆን ለቤተ ክርስቲያን ሰጠው። እርስዋም አካሉና ሁሉን በሁሉ የሚሞላ የእርሱ ሙላቱ ናት።

ኤፌሶን 1:3-23 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

በሰማይ ባለው መንፈሳዊ በረከት ሁሉ በክርስቶስ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን። ቅዱሳንና ነቀፋ የሌለብን ሆነን በፊቱ እንድንገኝ ዓለም ሳይፈጠር በክርስቶስ መረጠን። እግዚአብሔር በጎ ፈቃዱ ሆኖ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ልጆቹ እንድንሆን አስቀድሞ በፍቅሩ መረጠን። ይህንንም ያደረገው በተወደደው ልጁ አማካይነት በነጻ የሰጠን ክቡር ጸጋ እንዲመሰገን ነው። ከእግዚአብሔር ጸጋ ሙላት የተነሣ በልጁ ደም ተዋጅተን የኃጢአታችንን ይቅርታ አገኘን። ጸጋውንም በጥበብና በዕውቀት ሁሉ አብዝቶ አፈሰሰልን። እግዚአብሔር በቸርነቱ በክርስቶስ አማካይነት አስቀድሞ ባቀደው መሠረት የፈቃዱን ምሥጢር እንድናውቅ አደረገ። ጊዜው ሲደርስ እግዚአብሔር በሥራ ላይ የሚያውለው ዕቅድ በሰማይና በምድር ያሉት ፍጥረቶች ሁሉ ተጠቃለው በአንዱ በክርስቶስ ሥልጣን ሥር እንዲሆኑ ነው። ሁሉን ነገር በራሱ ፈቃድ የሚሠራ እግዚአብሔር አስቀድሞ በዐቀደልን መሠረት በክርስቶስ አማካይነት የእርሱ ወገኖች እንድንሆን መረጠን። ይህም የሆነው ክርስቶስን ተስፋ በማድረግ መጀመሪያዎች የሆንነው የእግዚአብሔርን ክብር በምስጋና እንድንገልጥ ነው። እናንተም የመዳናችሁ መልካም ዜና የሆነውን የእውነት ቃል በሰማችሁ ጊዜ በክርስቶስ አምናችኋል፤ እንዲሁም እርሱ ሊሰጣችሁ ተስፋ ባደረገላችሁ በመንፈስ ቅዱስ ታትማችኋል። ይህ መንፈስ ለክብሩ ምስጋና እንዲሆን እግዚአብሔር የራሱ የሆኑትን በሙሉ እስኪዋጅ ድረስ ልናገኝ ላለው ርስታችን መያዣችን ነው። ስለዚህ በጌታ በኢየሱስ ስላላችሁ እምነትና ለቅዱሳንም ሁሉ ስላላችሁ ፍቅር ሰምቼ እናንተን በጸሎቴ እያስታወስኩ በእናንተ ምክንያት ለእግዚአብሔር ምስጋና ማቅረቤን አላቋርጥም። ክብር የሚገባው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔርን በይበልጥ ታውቁ ዘንድ የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣችሁ እጸልያለሁ። ለምን ዐይነት ተስፋ እንደ ተጠራችሁና ቅዱሳን የሚወርሱት ክቡር ርስት ምን ያኽል ብዙ እንደ ሆነ ታውቁ ዘንድ የልቡናችሁ ዐይን እንዲበራላችሁ እጸልያለሁ። የማይለካው ታላቅ ኀይሉ ለእኛ ለምናምነው ምን ያኽል ታላቅ መሆኑን ታውቁ ዘንድ እጸልያለሁ፤ ይህንንም ታላቅ ኀይሉን በተግባር ያሳየው ከሞት አስነሥቶ በሰማይ በቀኙ ባስቀመጠው በክርስቶስ አማካይነት ነው። እግዚአብሔር አብ ክርስቶስን በሰማይ በቀኙ ያስቀመጠውም ከማንኛውም ግዛትና ሥልጣን ከኀይልና ጌትነት በላይ እንዲሁም በዚህ ዓለም ብቻ ሳይሆን በሚመጣውም ዓለም ከስም ሁሉ በላይ የሆነውን ክቡር ስም በመስጠት ነው። ሁሉንም ነገር በሥልጣኑ ሥር አድርጎ አስገዛለት፤ በቤተ ክርስቲያንም ከሁሉ በላይ እንዲሆን ራስ አደረገው። ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ አካል ናት፤ ክርስቶስም በቤተ ክርስቲያንና በሌላውም ሁሉ የመላ ነው።

ኤፌሶን 1:3-23 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ በሰማያዊ ስፍራ በክርስቶስ የባረከን፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይባረክ። ዓለም ሳይፈጠር፥ በፍቅር በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን እድንሆን በክርስቶስ መረጠን። በበጎ ፈቃዱ እንደ ወደደ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ልጆቹ እንድንሆን አስቀድሞ ወሰነን። በውድ ልጁም በነጻ የሰጠን የከበረ ጸጋው እንዲመሰገን ይህን አደረገ። በእርሱም እንደ ጸጋው ባለጠግነት መጠን፥ በደሙ ቤዛነታችንን አገኘን፤ የበደላችንም ይቅርታ ሆነ። ጸጋውንም አበዛልን። በጥበብና በአእምሮ ሁሉ፥ በክርስቶስ ለማድረግ የወደደውን የአሳቡን፥ የፈቃዱን ምሥጢር አስታውቆናል፤ በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ በክርስቶስ ለመጠቅለል፥ በዘመን ፍጻሜ እንዲሆን እንዳቀደው፥ እንደ ፈቃዱና እንደ ምክሩ ሁሉን የሚያከናውን እንደ እርሱ ዓላማ የተወሰንን በክርስቶስ በርስትነት ተቀበልን። ይኸውም በክርስቶስ አስቀድመን ተስፋ ያደረግን እኛ ደግሞ ለክብሩ ምስጋና እንድንሆን ነው። እናንተም ደግሞ የእውነትን ቃል፥ ይኸውም የመዳናችሁን ወንጌል ሰምታችሁ፥ በክርስቶስም አምናችሁ፥ በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ፤ እርሱም ለክብሩ ምስጋና ለእግዚአብሔር ሕዝብ ያለውን ሁሉ እስኪዋጅ ድረስ የርስታችን መያዣ ነው። እኔ ደግሞ፥ በጌታ ኢየሱስ ለቅዱሳኖች ሁሉ ያላችሁን እምነትና ፍቅር ሰምቻለሁ፤ በዚህም ምክንያት፥ ስለ እናንተን በጸሎቴ ባስታወስኩ ቍጥር ምስጋናዬን አላቋረጥኩም። የክብር ባለቤት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር እርሱን በማወቅ የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣችሁ እለምናለሁ። በእርሱ የተጠራችሁበት ተስፋ ምን እንደሆን፥ ከቅዱሳንም ጋር የሚኖራችሁን የርስት ክብር ባለጠግነት ምንነት እንድታውቁ፥ የልቦናችሁ ዐይኖች እንዲበሩ፤ ለእኛ ለምናምነውም ከሁሉ በላይ ታላቅ የሆነውን፥ የኀይሉ ታላቅ ብርታት አሠራር፥ ኀይሉን ምን እንደሆን እንድታውቁ፥ ይህን ኃይል እርሱ ክርስቶስን ከሙታን ሲያስነሣውና በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ ሲያስቀምጠው የታየ ነው። የተቀመጠውም ከግዛትና ከሥልጣን፥ ከኃይልና ከጌትነት እንዲሁም በዚህ ዘመን ብቻ ሳይሆን በሚመጣውም ዘመን ቢሆን ከሚጠራው ስም ሁሉ በላይ ነው። ሁሉንም ከእግሩ በታች አስገዛለት፤ ከሁሉ በላይም ራስ እንዲሆን ለቤተ ክርስቲያን ሰጠው። እርሷም አካሉና ሁሉን በሁሉ የሚሞላ የእርሱ ሙላቱ ናት።