መክብብ 9:11-12 - Compare All Versions

መክብብ 9:11-12 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

እኔም ተመ​ለ​ስሁ፥ ከፀ​ሓይ በታ​ችም ሩጫ ለፈ​ጣ​ኖች፥ ጦር​ነ​ትም ለኀ​ያ​ላን፥ እን​ጀ​ራም ለጠ​ቢ​ባን፥ ባለ​ጠ​ግ​ነ​ትም ለአ​ስ​ተ​ዋ​ዮች፥ ሞገ​ስም ለዐ​ዋ​ቂ​ዎች እን​ዳ​ል​ሆነ አየሁ፤ ጊዜና ዕድል ግን ሁሉን ያገ​ና​ኛ​ቸ​ዋል። ሰውም ጊዜ​ውን አያ​ው​ቅም፤ በክፉ መረብ እንደ ተጠ​መዱ ዓሣ​ዎች ፥ በወ​ጥ​መ​ድም እንደ ተያዙ ወፎች፥ እን​ዲሁ የሰው ልጆች በክፉ ጊዜ በድ​ን​ገት ሲወ​ድ​ቅ​ባ​ቸው ይጠ​መ​ዳሉ።

መክብብ 9:11-12 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ሌላም ነገር ከፀሓይ በታች አየሁ፤ ሩጫ ለፈጣኖች፣ ውጊያም ለኀያላን አይደለም፤ እንጀራ ለጥበበኞች፣ ወይም ባለጠግነት ለብልኆች፣ ወይም ሞገስ ለዐዋቂዎች አይሆንም፤ ጊዜና ዕድል ግን ሁሉን ይገናኛቸዋል። ደግሞም የራሱን ጊዜ የሚያውቅ ሰው የለም፤ ዓሦች በክፉ መረብ እንደሚያዙ፣ ወይም ወፎች በወጥመድ እንደሚጠመዱ፣ ሰዎችም ሳያስቡት በሚመጣባቸው፣ በክፉ ጊዜ ይጠመዳሉ።

መክብብ 9:11-12 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሐይ በታችም ሩጫ ለፈጣኖች፥ ሰልፍም ለኃያላን፥ እንጀራም ለጠቢባን፥ ባለጠግነትም ለአስተዋዮች፥ ሞገስም ለአዋቂዎች እንዳልሆነ አየሁ፥ ጊዜና እድል ግን ሁሉን ይገናኛቸዋል። ሰውም ጊዜውን አያውቅም፥ በክፉ መረብ እንደ ተጠመዱ ዓሣዎች፥ በወጥመድም እንደ ተያዙ ወፎች፥ እንዲሁ የሰው ልጆች በክፉ ጊዜ በድንገት ሲወድቅባቸው ይጠመዳሉ።

መክብብ 9:11-12 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

በዚህ ዓለም የተመለከትኩት ሌላም ነገር አለ፤ ይኸውም ፈጣን ሯጮች በአሸናፊነት አይወጡም፤ ጀግኖችም በጦርነት ድል አያደርጉም፤ ጠቢባን የዕለት እንጀራን፥ ብልኆች ሀብትን አያገኙም፤ ችሎታ ያላቸውም ሰዎች በማዕርግ አያድጉም፤ ነገር ግን ሁሉንም ጊዜና ዕድል ያጋጥማቸዋል፤ ይሁን እንጂ እያንዳንዱ ሰው ይህ መጥፎ ዕድል መቼ እንደሚገጥመው አያውቅም፤ ወፍ በራ በወጥመድ ውስጥ እንደምትገባ፥ ዓሣም በመጥፎ አጋጣሚ በመረብ እንደሚያዝ እንዲሁም የሰው ልጅ ሁሉ ሳያስበው ድንገት በሚደርስበት በክፉ አጋጣሚ ይጠመዳል።

መክብብ 9:11-12 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሐይ በታችም ሩጫ ለፈጣኖች፥ ፍልምያ ለኃያላን፥ እንጀራም ለጠቢባን፥ ሀብትም ለአስተዋዮች፥ ሞገስም ለአዋቂዎች እንዳልሆነ አየሁ፥ ጊዜና እድል ግን ሁሉን ይገናኛቸዋል። ሰውም ጊዜውን አያውቅም፥ በክፉ መረብ እንደ ተጠመዱ ዓሣዎች፥ በወጥመድም እንደ ተያዙ ወፎች፥ እንዲሁ የሰው ልጆች በክፉ ጊዜ በድንገት ሲወድቅባቸው ይጠመዳሉ።