መክብብ 7:1-6
መክብብ 7:1-6 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ከመልካም ሽቱ መልካም ስም፥ ከመወለድ ቀንም የሞት ቀን ይሻላል። ወደ ግብዣ ቤትም ከመሄድ ወደ ልቅሶ ቤት መሄድ ይሻላል፤ እርሱ የሰው ሁሉ ፍጻሜ ነውና፥ ሕያውም የሆነ ይህን መልካም ነገር በልቡ ያኖረዋል። ከሣቅ ኀዘን ይሻላል፥ ከፊት ኀዘን የተነሣ ልብ ደስ ይሰኛልና። የጠቢባን ልብ በልቅሶ ቤት ነው፤ የሰነፎች ልብ ግን በደስታ ቤት ነው። ለሰው የሰነፎችን ዘፈን ከሚሰማ ይልቅ የጠቢባንን ተግሣጽ መስማት ይሻለዋል። ከድስት በታች እንደሚቃጠል እሾህ ድምፅ የሰነፍ ሣቅ እንዲሁ ነው፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።
መክብብ 7:1-6 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
መልካም ስም ከመልካም ሽቱ ይበልጣል፤ ከልደትም ቀን የሞት ቀን ይሻላል። ወደ ግብዣ ቤት ከመሄድ፣ ወደ ሐዘን ቤት መሄድ ይሻላል፤ ሞት የሰው ሁሉ ፍጻሜ ነውና፤ ሕያው የሆነም ይህን ልብ ማለት ይገባዋል። ሐዘን ከሣቅ ይሻላል፤ ያዘነ ፊት ለልብ መልካም ነውና። የጠቢባን ልብ በሐዘን ቤት ነው፤ የሞኞች ልብ ግን በደስታ ቤት ነው። የሞኞችን መዝሙር ከመስማት፣ የጠቢባንን ሰዎች ተግሣጽ መስማት ይሻላል። የሞኞች ሣቅ፣ ከድስት ሥር እንደሚንጣጣ የእሾኽ ማገዶ ነው፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።
መክብብ 7:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ከመልካም ሽቱ መልካም ስም፥ ከመወለድ ቀንም የሞት ቀን ይሻላል። ወደ ግብዣ ቤት ከመሄድ ወደ ልቅሶ ቤት መሄድ ይሻላል፥ እርሱ የሰው ሁሉ ፍጻሜ ነውና፥ ሕያውም የሆነ በልቡ ያኖረዋልና። ከሳቅ ኀዘን ይሻላል፥ ከፊት ኀዘን የተነሣ ልብ ደስ ይሰኛልና። የጠቢባን ልብ በልቅሶ ቤት ነው፥ የሰነፎች ልብ ግን በደስታ ቤት ነው። ሰው የሰነፎችን ዜማ ከሚሰማ ይልቅ የጠቢባንን ተግሣጽ መስማት ይሻለዋል። ከድስት በታች እንደሚቃጠል እሾህ ድምፅ የሰነፍ ሳቅ እንዲሁ ነው፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።
መክብብ 7:1-6 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ዋጋው ውድ ከሆነ ከመልካም ሽቶ መልካም ስም ይሻላል፤ ከልደትም ቀን የሞት ቀን ይሻላል። ሞት በሰው ሁሉ ላይ የሚደርስ መሆኑን እንዲገነዘቡ ስለሚያደርግ ወደ ግብዣ ቤት ከመሄድ ይልቅ ወደ ለቅሶ ቤት መሄድ ይመረጣል። ፊትህን በሐዘን የሚያጠቁር ቢመስልም አእምሮህን የሚያበራ በመሆኑ ከሳቅ ይልቅ ሐዘን ይሻላል። ሁልጊዜ ስለ አስደሳች ነገር ብቻ የሚያስብ ሰው ሞኝ ነው፤ ብልኅ ግን የሞትንም ነገር ያስባል። የሞኞችን ዘፈን ከመስማት የጥበበኞችን ተግሣጽ መስማት ይሻላል። የሞኝ ሳቅ ከድስት ሥር እንደሚንጣጣ እሾኽ ስለ ሆነ ትርጒም የሌለው ከንቱ ነገር ነው።
መክብብ 7:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ከመልካም ሽቱ መልካም ስም፥ ከመወለድ ቀንም የሞት ቀን ይሻላል። ወደ ግብዣ ቤት ከመሄድ ወደ ልቅሶ ቤት መሄድ ይሻላል፥ እርሱ የሰው ሁሉ ፍጻሜ ነውና፥ ሕያውም የሆነ በልቡ ያኖረዋልና። ከሳቅ ኀዘን ይሻላል፥ ከፊት ኀዘን የተነሣ ልብ ደስ ይሰኛልና። የጠቢባን ልብ በልቅሶ ቤት ነው፥ የአላዋቂዎች ልብ ግን በደስታ ቤት ነው። ሰው የአላዋቂዎችን ዜማ ከሚሰማ ይልቅ የጠቢባንን ተግሣጽ መስማት ይሻለዋል። ከድስት በታች እንደሚቀጣጠል እሾህ ድምፅ የአላዋቂ ሳቅ እንዲሁ ነው፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።