ዘዳግም 8:12-14
ዘዳግም 8:12-14 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ከበላህና ከጠገብህ በኋላ፥ መልካምም ቤት ሠርተህ ከተቀመጥህባት በኋላ፤ የላምና የበግ መንጋ ከበዛልህ በኋላ፥ ብርህና ወርቅህም፥ ያለህም ሁሉ ከበዛልህ በኋላ፥ ልብህ እንዳይታበይ፤ ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣህን፥
ያጋሩ
ዘዳግም 8 ያንብቡዘዳግም 8:12-14 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
አለዚያ በልተህ ስትጠግብና ጥሩ ጥሩ ቤቶችን ሠርተህ መኖር ስትጀምር፣ ደግሞም የከብት፣ የበግና የፍየል መንጋህ ሲበዛ፣ ብርህና ወርቅህ ሲበረክት፣ ያለህም ሁሉ በላይ በላዩ እየጨመረ ሲሄድ፣ ልብህ ይታበይና ከባርነት ምድር፣ ከግብጽ ያወጣህን አምላክህን እግዚአብሔርን ትረሳለህ።
ያጋሩ
ዘዳግም 8 ያንብቡዘዳግም 8:12-14 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ከበላህና ከጠገብህ በኋላ፥ መልካምም ቤት ሠርተህ ከተቀመጥህበት በኋላ፥ የላምና የበግ መንጋ ከበዛልህ በኋላ፥ ብርህና ወርቅህም ያለህም ሁሉ ከበዛልህ በኋላ፥ ልብህ እንዳይጓደድ፤ ከግብፅም ምድር ከባርነት ቤት ያወጣህን፥
ያጋሩ
ዘዳግም 8 ያንብቡ