ዘዳግም 11:8-32

ዘዳግም 11:8-32 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

“በሕ​ይ​ወት ትኖሩ ዘንድ፥ ትበ​ዙም ዘንድ፥ ትወ​ር​ሱ​አ​ትም ዘንድ ዮር​ዳ​ኖ​ስን የም​ት​ሻ​ገ​ሩ​ላ​ትን ምድር እን​ድ​ት​ወ​ር​ሷት ዛሬ ለእ​ና​ንተ የማ​ዝ​ዘ​ውን ትእ​ዛዝ ሁሉ ጠብቁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ነ​ር​ሱና ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ ለዘ​ራ​ቸው ወተ​ትና ማር የም​ታ​ፈ​ስ​ሰ​ውን ምድር ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ በማ​ለ​ላ​ቸው ምድር ላይ ዕድ​ሜ​ያ​ችሁ እን​ዲ​ረ​ዝም። ትወ​ር​ሳት ዘንድ የም​ት​ገ​ባ​ባት ምድር፥ በአ​ት​ክ​ልት ስፍራ እን​ደ​ሚ​ዘሩ ዘር​ህን እንደ ዘራ​ህ​ባት፥ በእ​ግ​ር​ህም እን​ዳ​ጠ​ጣ​ሃት፥ እንደ ወጣ​ህ​ባት እንደ ግብፅ ምድር አይ​ደ​ለ​ችም። ነገር ግን ትወ​ር​ሱ​አት ዘንድ ተሻ​ግ​ራ​ችሁ የም​ት​ገ​ቡ​ባት ምድር ተራ​ሮ​ችና ሜዳ​ዎች ያሉ​ባት ሀገር ናት፤ በሰ​ማይ ዝናብ ውኃ ትረ​ካ​ለች። አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ጐ​በ​ኛት ሀገር ናት፤ ከዓ​መቱ መጀ​መ​ሪያ እስከ ዓመቱ መጨ​ረሻ ድረስ የአ​ም​ላ​ክህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐይን ሁል ጊዜ በእ​ር​ስዋ ላይ ነው። “እና​ንተ አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትወ​ድዱ ዘንድ፥ በፍ​ጹም ልባ​ችሁ፥ በፍ​ጹ​ምም ነፍ​ሳ​ችሁ ታመ​ል​ኩት ዘንድ ዛሬ ለእ​ና​ንተ የማ​ዝ​ዘ​ውን ትእ​ዛ​ዜን ፈጽ​ማ​ችሁ ብት​ሰሙ፥ እህ​ል​ህን፥ ወይ​ን​ህ​ንም፥ ዘይ​ት​ህ​ንም ትሰ​በ​ስብ ዘንድ በየ​ጊ​ዜው የበ​ል​ጉን ዝና​ብና የክ​ረ​ም​ቱን ዝናብ ለም​ድ​ርህ ይሰ​ጣል። በሜ​ዳህ ለእ​ን​ስ​ሶ​ችህ ሣርን ይሰ​ጣል፤ ትበ​ላ​ማ​ለህ፤ ትጠ​ግ​ብ​ማ​ለህ። ልባ​ችሁ እን​ዳ​ይ​ስት፥ ፈቀቅ እን​ዳ​ትሉ፥ ሌሎ​ች​ንም አማ​ል​ክት እን​ዳ​ታ​መ​ልኩ፥ እን​ዳ​ት​ሰ​ግ​ዱ​ላ​ቸ​ውም ተጠ​ን​ቀቁ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቍጣ እን​ዳ​ይ​ነ​ድ​ድ​ባ​ችሁ፥ ዝና​ብም እን​ዳ​ይ​ዘ​ንብ፥ ምድ​ሪ​ቱም ፍሬ​ዋን እን​ዳ​ት​ሰጥ ሰማ​ይን እን​ዳ​ይ​ዘ​ጋ​ባ​ችሁ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ከመ​ል​ካ​ሚቱ ምድር ፈጥ​ና​ችሁ እን​ዳ​ት​ጠፉ ተጠ​ን​ቀቁ። “እን​ግ​ዲህ እነ​ዚ​ህን ቃሎች በል​ባ​ች​ሁና በነ​ፍ​ሳ​ችሁ አኑሩ፤ እነ​ር​ሱ​ንም ለም​ል​ክት በእ​ጃ​ችሁ ላይ እሰ​ሩ​አ​ቸው፤ በዐ​ይ​ኖ​ቻ​ች​ሁም መካ​ከል እን​ደ​ማ​ይ​ን​ቀ​ሳ​ቀስ ይሁኑ። ልጆ​ቻ​ች​ሁ​ንም አስ​ተ​ም​ሩ​አ​ቸው፤ በቤ​ትም ሲቀ​መጡ፥ በመ​ን​ገ​ድም ሲሄዱ፥ ሲተ​ኙም፥ ሲነ​ሡም እን​ዲ​ነ​ጋ​ገ​ሩ​በት፤ በቤ​ትህ መቃ​ኖ​ችና በደ​ጃ​ፍ​ህም በሮች ላይ ጻፈው። በም​ድር ላይ የሰ​ማ​ይን ዘመን ያህል ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ በማ​ለ​ላ​ቸው ምድር ዘመ​ና​ችሁ የል​ጆ​ቻ​ች​ሁም ዘመን ይረ​ዝም ዘንድ፤ አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትወ​ድዱ ዘንድ፥ በመ​ን​ገ​ዱም ሁሉ ትሄዱ ዘንድ፥ እር​ሱ​ንም ትከ​ተሉ ዘንድ፥ ዛሬ ለእ​ና​ንተ የማ​ዝ​ዘ​ውን ትእ​ዛዝ ሁሉ ብት​ጠ​ብቁ ብታ​ደ​ር​ጉ​አ​ትም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እነ​ዚ​ህን አሕ​ዛብ ሁሉ ከፊ​ታ​ችሁ ያወ​ጣል፤ ከእ​ና​ን​ተም የሚ​በ​ል​ጡ​ትን፥ የሚ​በ​ረ​ቱ​ት​ንም አሕ​ዛብ ትወ​ር​ሳ​ላ​ችሁ። የእ​ግ​ራ​ችሁ ጫማ የም​ት​ረ​ግ​ጣት ስፍራ ሁሉ ለእ​ና​ንተ ትሆ​ና​ለች፤ ከም​ድረ በዳም፥ ከአ​ን​ጢ​ሊ​ባ​ኖ​ስም፥ ከታ​ላ​ቁም ከኤ​ፍ​ራ​ጥስ ወንዝ ጀምሮ እስከ ምዕ​ራብ ባሕር ድረስ ዳር​ቻ​ችሁ ይሆ​ናል። በእ​ና​ን​ተም ፊት ማንም መቆም አይ​ች​ልም፤ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ እንደ ተና​ገ​ራ​ችሁ፥ ማስ​ፈ​ራ​ታ​ች​ሁን፥ ማስ​ደ​ን​ገ​ጣ​ች​ሁ​ንም በም​ት​ረ​ግ​ጡ​አት ምድር ሁሉ ላይ ያኖ​ራል። “እነሆ፥ እኔ ዛሬ በፊ​ታ​ችሁ በረ​ከ​ት​ንና መር​ገ​ምን አኖ​ራ​ለሁ፤ በረ​ከ​ትም፥ እኔ ዛሬ ለእ​ና​ንተ የማ​ዝ​ዘ​ውን የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ብት​ሰሙ ነው፤ መር​ገ​ምም፥ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ባት​ሰሙ፥ ዛሬ ካዘ​ዝ​ኋ​ችሁ መን​ገድ ፈቀቅ ብትሉ፥ ሌሎ​ች​ንም የማ​ታ​ው​ቁ​አ​ቸ​ውን አማ​ል​ክት ብት​ከ​ተሉ፥ ብታ​መ​ል​ኳ​ቸ​ውም ነው። አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትወ​ር​ሳት ዘንድ አን​ተን ወደ​ም​ት​ሄ​ድ​ባት ምድር ባገ​ባህ ጊዜ፥ በረ​ከ​ቱን በገ​ሪ​ዛን ተራራ፥ መር​ገ​ሙ​ንም በጌ​ባል ተራራ ታኖ​ራ​ለህ። እነ​ር​ሱም በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ፥ ከፀ​ሐይ መግ​ቢያ ካለ​ችው መን​ገድ በኋላ በዓ​ረባ በተ​ቀ​መ​ጡት በከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያን ምድር፥ በጌ​ል​ጌላ ፊት ለፊት በረ​ዥሙ ዛፍ አጠ​ገብ ናቸው። አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዕ​ጣ​ችሁ ለሁ​ል​ጊዜ የሚ​ሰ​ጣ​ች​ሁን ምድር ትገ​ቡና ትወ​ርሱ ዘንድ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ትሻ​ገ​ራ​ላ​ችሁ፤ ትወ​ር​ሱ​አ​ታ​ላ​ች​ሁም፤ ትቀ​መ​ጡ​ባ​ታ​ላ​ች​ሁም። እኔም ዛሬ በፊ​ታ​ችሁ የማ​ኖ​ራ​ትን ሥር​ዐ​ትና ፍርድ ሁሉ ታደ​ርጉ ዘንድ ጠብቁ።

ዘዳግም 11:8-32 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ስለዚህ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ወደምትወርሷት ምድር ለመግባትና ለመያዝ ብርታት እንድታገኙ፣ ዛሬ እኔ የምሰጣችሁን ትእዛዞች ሁሉ ጠብቁ፤ ለአባቶቻቸውና ለዘሮቻቸው እግዚአብሔር ሊሰጣቸው በማለላቸው፣ በዚያች ማርና ወተት በምታፈስሰው ምድር ረዥም ዕድሜ ትኖሩ ዘንድ፣ የምትገባባት ምድር እንደ ወጣህባትና ዘርህን ዘርተህባት በእግርህ ውሃ እንዳጠጣሃት የአትክልት ቦታ እንደ ግብጽ ምድር አይደለችም። ዮርዳኖስን ተሻግረህ ልትወርሳት ያለችው ምድር ግን፣ ከሰማይ ዝናብ የምትጠጣ፣ ተራሮችና ሸለቆች ያሉባት ምድር ናት። ይህች ምድር አምላክህ እግዚአብሔር የሚንከባከባት፣ ከዓመቱ መጀመሪያ እስከ ዓመቱ መጨረሻ የአምላክህ የእግዚአብሔር ዐይን ምን ጊዜም የማይለያት ናት። ዛሬ እኔ የምሰጣችሁን ትእዛዞች በታማኝነት ብትጠብቁ፣ ይኸውም አምላካችሁን እግዚአብሔርን ብትወድዱና በፍጹም ልባችሁ፣ በፍጹም ነፍሳችሁም እርሱን በማገልገል በታማኝነት ብትጠብቁ፣ እህልህን፣ ወይንህንና ዘይትህን እንድትሰበስብ የበልጉንና የክረምቱን ዝናብ በምድርህ ላይ በየወቅቱ አዘንባለሁ። በሜዳ ላይ ለከብቶችህ ሣር እሰጣለሁ፤ አንተም ትበላለህ፤ ትጠግባለህም። ተጠንቀቁ፤ አለዚያ ተታልላችሁ ሌሎች አማልክትን ታመልካላችሁ፤ ትሰግዳላችሁም። ከዚያም የእግዚአብሔር ቍጣ በላያችሁ ይነድዳል፤ እርሱም ዝናብ እንዳይዘንብ፣ ምድሪቱም ፍሬ እንዳትሰጥ ሰማያትን ይዘጋል፤ እናንተም እግዚአብሔር ከሚሰጣችሁ ከመልካሚቱ ምድር ወዲያውኑ ትጠፋላችሁ። እነዚህን ቃሎቼን፣ በልባችሁና በአእምሯችሁ አኑሯቸው፤ በእጆቻችሁ ላይ ምልክት አድርጋችሁ እሰሯቸው፣ በግንባራችሁም ላይ ይሁኑ። ልጆቻችሁንም አስተምሯቸው፤ በቤትህ ስትቀመጥ፣ በመንገድም ስትሄድ፣ ስትተኛና ስትነሣም ስለ እነርሱ ተናገር። በቤትህ መቃኖችና በግቢህም በሮች ላይ ጻፋቸው፤ ይህን ካደረጋችሁ፣ እግዚአብሔር ለአባቶቻችሁ ለመስጠት በማለላቸው ምድር የእናንተና የልጆቻችሁ ዘመን ከምድር በላይ ያሉ ሰማያትን ርቀት ያህል ይሆናል። አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትወድዱ ዘንድ፣ በመንገዶቹም ሁሉ ትሄዱና ከርሱም ጋራ ትጣበቁ ዘንድ እንድትከተሏቸው የምሰጣችሁን እነዚህን ትእዛዞች ሁሉ በጥንቃቄ ብትጠብቁ፣ እግዚአብሔር እነዚህን አሕዛብ ሁሉ ከፊታችሁ ያስወጣቸዋል፤ እናንተም፣ ከእናንተ ይልቅ ታላላቅና ብርቱ የሆኑትን አሕዛብ ታስለቅቃላችሁ። በእግራችሁ የምትረግጡት ስፍራ ሁሉ የእናንተ ይሆናል፤ ግዛታችሁም ከምድረ በዳው እስከ ሊባኖስ፣ ከኤፍራጥስ ወንዝ አንሥቶ በስተምዕራብ እስካለው ባሕር ይደርሳል። ማንም ሰው ሊቋቋማችሁ አይችልም፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር በሰጣችሁ ተስፋ መሠረት ማስደንገጣችሁንና መፈራታችሁን በምትሄዱበት በየትኛውም ምድር ሁሉ ላይ ያሳድራል። እነሆ፤ ዛሬ በረከትንና መርገምን በፊታችሁ አኖራለሁ፤ በረከቱ ዛሬ የምሰጣችሁን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዞች ስትፈጽሙ ሲሆን፣ መርገሙ ደግሞ፣ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዞች የማትፈጽሙ፣ የማታውቋቸውንም ሌሎች አማልክት ለመከተል እኔ ከማዝዛችሁ መንገድ የምትወጡ ከሆነ ነው። ልትወርሳት ወደምትሄድባት ምድር አምላክህ እግዚአብሔር በሚያስገባህ ጊዜ በረከቱን በገሪዛን ተራራ፣ መርገሙን ደግሞ በጌባል ተራራ ላይ ታሰማለህ። እነዚህ ተራሮች የሚገኙት ከዮርዳኖስ ማዶ ፀሓይ በምትጠልቅበት አቅጣጫ ካለው መንገድ በስተምዕራብ በዓረባ በሚኖሩ የከነዓናውያን ምድር ውስጥ ከጌልገላ ፊት ለፊት፣ በሞሬ ታላላቅ ዛፎች አጠገብ አይደለምን? አምላካችሁ እግዚአብሔር በሚሰጣችሁ ምድር ትገቡባትና ትወርሷት ዘንድ ዮርዳኖስን ልትሻገሩ ስለ ሆነ፣ ምድሪቱን ወርሳችሁ በምትኖሩባት ጊዜ፣ ዛሬ በፊታችሁ እኔ ያስቀመጥኋቸውን ሥርዐቶችና ሕጎች ሁሉ ለመፈጸም ተጠንቀቁ።

ዘዳግም 11:8-32 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

እንግዲህ እንድትጠነክሩ፥ ትወርሱአትም ዘንድ ወደምትሻገሩባት ምድር እንድትገቡ እንድትወርሱአትም፥ እግዚአብሔርም ለእነርሱና ለዘራቸው ይሰጣት ዘንድ በማለላቸው ወተትና ማርም በምታፈስሰው ምድር ዕድሜአችሁ እንዲረዝም፥ ዛሬ ለእናንተ የማዝዘውን ትእዛዝ ሁሉ ጠብቁ። ትወርሳት ዘንድ የምትገባባት ምድር፥ በአትክልት ስፍራ እንደሚዘሩ ዘርህን እንደዘራህባት፥ በእግርህም እንዳጠጣሃት፥ እንደ ወጣህባት እንደ ግብፅ ምድር አይደለችም። ነገር ግን ትወርሱአት ዘንድ ተሻግራችሁ የምትገቡባት ምድር ኮረብታና ሸለቆ ያለባት አገር ናት፤ በሰማይ ዝናብ ውኃ ትረካለች። አምላክህ እግዚአብሔር የሚጎበኛት አገር ናት፤ ከዓመቱ መጀመሪያ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ የአምላክህ የእግዚአብሔር ዓይን ሁልጊዜ በእርስዋ ላይ ነው። እንዲህም ይሆናል፤ እናንተ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትወድዱ ዘንድ፥ በፍጹምም ልባችሁ በፍጹምም ነፍሳችሁ ታመልኩት ዘንድ ዛሬ ለእናንተ የማዝዘውን ትእዛዜን ፈጽማችሁ ብትሰሙ፥ እህልህን ወይንህንም ዘይትህንም ትሰበስብ ዘንድ በየጊዜው የበልጉን ዝናብና የክረምቱን ዝናብ ለምድራችሁ አወርዳለሁ። በሜዳ ለእንስሶችህ ሣርን እሰጣለሁ፥ ትበላማለህ፥ ትጠግብማለህ። ልባችሁ እንዳይስት፥ ፈቀቅ እንዳትሉ፥ ሌሎችንም አማልክት እንዳታመልኩ፥ እንዳትሰግዱላቸውም፥ የእግዚአብሔርም ቁጣ እንዳይነድድባችሁ፥ ዝናብም እንዳይዘንብ ምድሪቱም ፍሬዋን እንዳትሰጥ ሰማይን እንዳይዘጋባችሁ፤ እግዚአብሔርም ከሚሰጣችሁ ከመልካሚቱ ምድር ፈጥናችሁ እንዳትጠፉ ተጠንቀቁ። እንግዲህ እነዚህን ቃሎች በልባችሁና በነፍሳችሁ አኑሩ፤ እነርሱንም ለምልክት በእጃችሁ ላይ እሰሩአቸው፥ በዓይኖቻችሁም መካከል እንደክታብ ይሁኑ። ልጆቻችሁንም አስተምሩአቸው፥ በቤትህም ስትቀመጥ፥ በመንገድም ስትሄድ፥ ስትተኛም ስትነሣም አጫውቱአቸው። እርስዋንም እንዲሰጣቸው እግዚአብሔር ለአባቶቻችሁ በማለላቸው ምድር፥ እንደ ሰማይ ዘመን በምድር ላይ፥ ዘመናችሁ የልጆቻችሁም ዘመን ይረዝም ዘንድ በቤትህ መቃኖችና በደጃፍህም በሮች ላይ ጻፈው። አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትወድዱ ዘንድ፥ በመንገዱም ሁሉ ትሄዱ ዘንድ፥ ከእርሱም ጋር ትጣበቁ ዘንድ፥ ዛሬ ለእናንተ የማዝዘውን ትእዛዝ ሁሉ ብትጠብቁ ብታደርጉአትም፥ እግዚአብሔር እነዚህን አሕዛብ ሁሉ ከፊታችሁ ያወጣል፥ ከእናንተም የሚበልጡትን የሚበረቱትንም አሕዛብ ትወርሳላችሁ። የእግራችሁ ጫማ የምትረግጣት ስፍራ ሁሉ ለእናንተ ትሆናለች፤ ከምድረ በዳም ከሊባኖስም ከታላቁም ከኤፍራጥስ ወንዝ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ባሕር ድረስ ዳርቻችሁ ይሆናል። በእናንተም ፊት ማንም መቆም አይችልም፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር፥ እርሱ እንደ ተናገራችሁ፥ ማስፈራታችሁን ማስደንገጣችሁንም በምትረግጡአት ምድር ሁሉ ላይ ያኖራል። እነሆ፥ እኔ ዛሬ በፊታችሁ በረከትንና መርገምን አኖራለሁ፤ በረከትም፥ እኔ ዛሬ ለእናንተ የማዝዘውን የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ብትሰሙ፤ መርገምም፥ የአምላካችሁን የእግዚአብሕርን ትእዛዝ ባትሰሙ፥ ዛሬ ካዘዝኋችሁ መንገድ ፈቀቅ ብትሉ፥ ሌሎችንም የማታውቍቸውን አማልክት ብትከተሉ ነው። አምላክህም እግዚአብሔር ትወርሳት ዘንድ አንተን ወደምትሄድባት ምድር ባገባህ ጊዜ፥ በረከቱን በገሪዛን ተራራ መርገሙንም በጌባል ተራራ ታኖራለህ። እነርሱም በዮርዳኖስ ማዶ፥ ከፀሐይ መግቢያ ካለችው መንገድ በኋላ፥ በዓረባ በተቀመጡት በከነዓናውያን ምድር፥ በጌልገላ ፊት ለፊት በሞሬ የአድባር ዛፍ አጠገብ ናቸው። አምላካችሁ እግዚአብሔር የሚሰጣችሁን ምድር ትወርሱ ዘንድ ዮርዳኖስን ትሻገራላችሁ፥ ትወርሱአታላችሁም፥ ትቀመጡባታላችሁም። እኔም ዛሬ በፊታችሁ የማኖራትን ሥርዓትና ፍርድ ሁሉ ታደርጉ ዘንድ ጠብቁ።

ዘዳግም 11:8-32 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

“እንግዲህ ወደምትወርሱት ምድር ተሻግራችሁ ለመያዝ ኀይል ታገኙ ዘንድ እኔ ዛሬ የማዛችሁን ትእዛዞች ሁሉ ጠብቁ። ትእዛዞቹንም ብትጠብቁ እግዚአብሔር ለቀድሞ አባቶቻችሁና ለዘሮቻቸው ሊሰጣቸው ቃል በገባላቸው በማርና በወተት በበለጸገችው፥ በዚያች ለምለም ምድር ለረጅም ዘመን ትኖራላችሁ። ይህች የምትወርሳት ምድር ከዚህ በፊት እንደ ነበርክባት እንደ ግብጽ ምድር አይደለችም። በግብጽ ምድር እህል ከዘራህ በኋላ እንደ ጓሮ አትክልት ማሳውን ውሃ ለማጠጣት ቦዩን በእግርህ አማካይነት ትቈጣጠረው ነበር። ነገር ግን የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግራችሁ የምትወርሱአት ምድር ተራራዎችና ሸለቆዎች ያሉአት ሆና የዝናብ ውሃ የምትጠጣ ናት። ይህችን ምድር የሚንከባከባትና ዓመቱን ሙሉ የሚጠብቃት እግዚአብሔር አምላክህ ነው። “ስለዚህም ዛሬ እኔ የማዛችሁን ሕግ ሁሉ ጠብቁ፤ እግዚአብሔር አምላካችሁንም ውደዱ፤ በፍጹም ልባችሁም አገልግሉት። ይህን ብታደርጉ እግዚአብሔር የክረምቱንና የበልጉን ዝናብ በወቅቱ ለምድራችሁ ይልካል፤ በዚህም ዐይነት ለእናንተ ሲሳይ የሚሆነው እህል፥ ወይን ጠጅና የወይራ ዘይት፥ እንስሶችህ የሚመገቡት ሣር ይበዛላችኋል፤ የሚያስፈልግህን ምግብ ሁሉ ታገኛለህ። ከእግዚአብሔር ርቃችሁ ባዕዳን አማልክትን ለመከተልና ለማምለክ ዘወር እንዳትሉ ተጠንቀቁ። ይህን ብታደርጉ እግዚአብሔር በእናንተ ላይ ይቈጣል፤ ሰማያትን ዘግቶ ምድሪቱን ዝናብ እንዳይዘንብባትና ፍሬ እንዳትሰጥ ያደርጋል፤ እናንተም እግዚአብሔር ከሚሰጣችሁ ምድር ፈጥናችሁ ትጠፋላችሁ። “እነዚህን ትእዛዞች ዘወትር በልቡናችሁና በአእምሮአችሁ ቅረጹአቸው፤ መታሰቢያም ይሆኑላችሁ ዘንድ እነርሱን በክንዳችሁ ላይ እሰሩ፤ በግንባራችሁም ላይ እንደማስታወሻ አኑሩአቸው፤ ለልጆቻችሁም አስተምሩአቸው፤ በቤት በምትቀመጡበት ጊዜ፥ ወይም ስትሄዱ፥ ዕረፍት በምታደርጉበትም ሆነ በምትሠሩበት ጊዜ ሁሉ ስለ እነርሱ ተነጋገሩ፤ በቤትህ የበር መቃኖችና በቅጽር በሮችህም ሳንቃ ላይ ጻፋቸው። ይህን ብታደርግ እግዚአብሔር አምላክህ ለቀድሞ አባቶችህ ሊሰጣቸው በመሐላ ቃል በገባላቸው ምድር የአንተና የልጆችህ ዘመን ከምድር በላይ እንዳለው ሰማይ ይረዝማል። “ስለዚህም እኔ የሰጠኋችሁን ትእዛዞች በጥንቃቄ ፈጽሙ፤ እግዚአብሔር አምላካችሁን ውደዱ፤ በእርሱ መንገድም በመጓዝ ለእርሱ ታማኞች ሁኑ። ይህን ብታደርጉ እግዚአብሔር እነዚህን በፊታችሁ ያሉትን ሕዝቦች ሁሉ ያስወጣል፤ እናንተም በብዛትና በኀይል ከእናንተ እጅግ ብርቱዎች የሆኑትን ሕዝቦች ምድር ትወርሳላችሁ። ስታልፉ በእግራችሁ የምትረግጡት መሬት ሁሉ የእናንተ ይሆናል፤ ግዛታችሁም በደቡብ በኩል ካለው በረሓ ተነሥቶ በሰሜን በኩል እስካሉት እስከ ሊባኖስ ተራራዎች፥ እንዲሁም በምሥራቅ በኩል ከሚገኘው ከኤፍራጥስ ወንዝ ተነሥቶ በምዕራብ በኩል እስከሚገኘው እስከ ታላቁ ሜዲቴራኒያን ባሕር ድረስ ይሰፋል። በዚያች ምድር በምትሄዱበት ስፍራ ሁሉ እግዚአብሔር አምላካችሁ በሰጣችሁ ተስፋ መሠረት ሕዝቦች ሁሉ እንዲፈሩአችሁ ያደርጋል፤ ሊቋቋማችሁ የሚችልም ከቶ አይገኝም። “እነሆ! እኔ ዛሬ ከበረከትና ከመርገም አንዱን እንድትመርጡ ዕድል እሰጣችኋለሁ። ዛሬ እኔ የምሰጣችሁን የእግዚአብሔር አምላካችሁን ትእዛዞች ሁሉ ብትፈጽሙ በረከት ታገኛላችሁ፤ ከዚህ በፊት ያላወቃችኋቸውን ባዕዳን አማልክት ወደ መከተል አዘንብላችሁ እነዚህን ትእዛዞች ባትፈጽሙ ግን ርግማን ይመጣባችኋል። እግዚአብሔር ወደምትወርሳት ምድር በሚያስገባህ ጊዜ በረከቱን በገሪዛን ተራራ፥ መርገሙንም በዔባል ተራራ ታውጃለህ። እነዚህም ተራራዎች ከዮርዳኖስ ማዶ በስተምዕራብ በኩል፥ በአራባ በሚኖሩት በከነዓናውያንም ምድር በጌልገላ ፊት ለፊት ከሞሬ ዛፍ አጠገብ የሚገኙ ናቸው። አምላካችሁ እግዚአብሔር እንድትኖሩባት የሰጣችሁን ምድር ለመውረስ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁና ወርሳችሁም በምትኖሩባት ጊዜ፥ ዛሬ እኔ የምሰጣችሁን ሕግና ሥርዓት ሁሉ በጥንቃቄ ጠብቁ።

ዘዳግም 11:8-32 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

“ስለዚህ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ወደምትወርሷት ምድር ለመግባትና ለመያዝ ብርታት እንድታገኙ፥ ዛሬ እኔ የምሰጣችሁን ትእዛዞች ሁሉ ጠብቁ፤ ለአባቶቻቸውና ለዘሮቻቸው ጌታ ሊሰጣቸው በማለላቸው፥ በዚያች ማርና ወተት በምታፈሰው ምድር ረጅም ዕድሜ ትኖሩ ዘንድ፥ የምትገባባት ምድር እንደ ወጣህባትና ዘርህን ዘርተህባት በእግርህ ውሃ እንዳጠጣሃት የአትክልት ቦታ እንደ ግብጽ ምድር አይደለችም። ዮርዳኖስን ተሻግረህ ልትወርሳት ያለችው ምድር ግን፥ ከሰማይ ዝናብ የምትጠጣ፥ ተራሮችና ሸለቆች ያሉባት ምድር ናት። ይህች ምድር ጌታ እግዚአብሔር የሚንከባከባት፥ ከዓመቱ መጀመሪያ እስከ ዓመቱ መጨረሻ የጌታ የአምላክህ ዐይን ምንጊዜም የማይለያት ናት።” “ጌታ አምላክህን በመውደድ ዛሬ እኔ የምሰጣችሁን ትእዛዞች በታማኝነት ብትጠብቁ፥ በፍጹም ልባችሁ፥ በፍጹም ነፍሳችሁም እርሱን በማገልገል፥ በታማኝነት ብትጠብቁ፥ እህልህን፥ ወይንህንና ዘይትህን እንድትሰበስብ የበልጉንና የክረምቱን ዝናብ በምድርህ ላይ በየወቅቱ አዘንባለሁ። በሜዳ ላይ ለከብቶችህ ሣር እሰጣለሁ፤ አንተም ትበላለህ፤ ትጠግባለህም። ተጠንቀቁ! ተታላችሁ ሌሎች አማልክትን እንዳታመልኩ፤ እንዳትሰግዱላቸውም። የጌታም ቁጣ በላያችሁ እንዳይነድ፤ እርሱም ዝናብ እንዳይከለክላችሁ፤ ምድሪቱም ፍሬ እንዳትሰጥ ሰማያትን ይዘጋል፤ እናንተም ጌታ ከሚሰጣችሁ ከመልካሚቱ ምድር ወዲያውኑ ትጠፋላችሁ።” “እነዚህን ቃሎቼን፥ በልባችሁና በአእምሮአችሁ አኑሯቸው፤ በእጆቻችሁ ላይ ምልክት አድርጋችሁ እሰሯቸው፥ በግምባራችሁም ላይ ይሁኑ። ልጆቻችሁንም አስተምሯቸው፤ ቤት ስትቀመጥ፥ መንገድ ስትሄድ፥ ስትተኛና ስትነሣ ስለዚህ አጫውታቸው። በቤትህ መቃኖችና በግቢህ በሮች ላይ ጻፋቸው፤ ይህን ካደረጋችሁ፥ ጌታ ለአባቶቻችሁ ለመስጠት በማለላቸው ምድር የእናንተና የልጆቻችሁ ዘመን ከምድር በላይ ያሉ ሰማያትን ርቀት ያህል ይሆናል።” “አምላካችሁን ጌታን ትወዱ ዘንድ፥ በመንገዶቹም ሁሉ ትሄዱና ከእርሱም ጋር ትጣበቁ ዘንድ እንድትከተሏቸው የምሰጣችሁን እነዚህን ትእዛዞች ሁሉ በጥንቃቄ ብትጠብቁ፥ ከዚያም ጌታ እነዚህን አሕዛብ ሁሉ ከፊታችሁ ያስወጣቸዋል፤ እናንተም፥ ከእናንተ ይልቅ ታላላቅና ብርቱ የሆኑትን አሕዛብ ታስለቅቃላችሁ። በእግራችሁ የምትረግጡት ስፍራ ሁሉ የእናንተ ይሆናል፤ ግዛታችሁም ከምድረ በዳው እስከ ሊባኖስ፥ ከኤፍራጥስ ወንዝ አንሥቶ በስተ ምዕራብ እስካለው ባሕር ይደርሳል። ማንም ሰው ሊቋቋማችሁ አይችልም፤ ጌታ እግዚአብሔር በሰጣችሁ ተስፋ መሠረት ማስደንገጣችሁንና መፈራታችሁን በምትሄዱበት በየትኛውም ምድር ሁሉ ላይ ያሳድራል።” “እነሆ፤ ዛሬ በረከትንና መርገምን በፊታችሁ አኖራለሁ፤ በረከቱ ዛሬ የምሰጣችሁን የጌታ የእግዚአብሔርን ትእዛዞች ስትፈጽሙ ሲሆን፥ መርገሙ ደግሞ፥ የጌታ የአምላካችሁን ትእዛዞች የማትፈጽሙ፥ የማታውቋቸውንም ሌሎች አማልክት ለመከተል እኔ ከማዛችሁ መንገድ የምትወጡ ከሆነ ነው።” “ልትወርሳት ወደምትሄድባት ምድር ጌታ አምላክህ በሚያስገባህ ጊዜ በረከቱን በገሪዛን ተራራ፥ መርገሙን ደግሞ በጌባል ተራራ ላይ ታሰማለህ። እነዚህ ተራሮች የሚገኙት ከዮርዳኖስ ማዶ ፀሓይ በምትጠልቅበት አቅጣጫ ካለው መንገድ በስተ ምዕራብ በዓረባ በሚኖሩ የከነዓናውያን ምድር ውስጥ ከጌልገላ ፊትለፊት፥ በሞሬ ታላላቅ ዛፎች አጠገብ አይደለምን? አምላካችሁ ጌታ በሚሰጣችሁ ምድር ትገቡባትና ትወርሷት ዘንድ ዮርዳኖስን ልትሻገሩ ስለሆነ፥ ምድሪቱን ወርሳችሁ በምትኖሩባት ጊዜ፥ ዛሬ በፊታችሁ እኔ ያስቀመጥኳቸውን ሥርዓቶችና ሕጎች ሁሉ ለመፈጸም ትጉ።”