ዘዳግም 10:12-14
ዘዳግም 10:12-14 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
“እስራኤል ሆይ፥ አሁንስ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ የሚፈልገው ምንድን ነው? አምላክህን እግዚአብሔርን ትፈራ ዘንድ፥ በመንገዱም ሁሉ ትሄድ ዘንድ፥ አምላክህንም እግዚአብሔርን ትወድድ ዘንድ፥ በፍጹምም ልብህ፥ በፍጹምም ነፍስህ ታመልከው ዘንድ ነው እንጂ፥ መልካምም እንዲሆንልህ ዛሬ ለአንተ የማዝዘውን የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዝና ሥርዐት ትጠብቅ ዘንድ ነው እንጂ፤ እነሆ፥ ሰማይ፥ ሰማየ ሰማያትም፥ ምድርም፥ በእርስዋም ያለው ሁሉ የአምላክህ የእግዚአብሔር ነው።
ዘዳግም 10:12-14 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
አሁንም እስራኤል ሆይ፤ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ የሚፈልገው ምንድን ነው? አምላክህን እግዚአብሔርን እንድትፈራው፣ በመንገዶቹ ሁሉ እንድትሄድ፣ እንድትወድደው፣ በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም ነፍስህ እንድታገለግለው፣ መልካም እንዲሆንልህና ዛሬ እኔ የምሰጥህን ትእዛዞችና የእግዚአብሔር ሥርዐቶች እንድትጠብቅ አይደለምን? ሰማያት፣ ሰማየ ሰማያት፣ ምድርና በርሷም ያለው ሁሉ የአምላክህ የእግዚአብሔር ነው።
ዘዳግም 10:12-14 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
እስራኤል ሆይ፥ አሁንስ አምላክህን እግዚአብሔርን ትፈራ ዘንድ፥ በመንገዱም ሁሉ ትሄድ ዘንድ፥ አምላክህንም እግዚአብሔርን ትወድድ ዘንድ፥ በፍጹምም ልብህ በፍጹምም ነፍስህ ታመልከው ዘንድ፥ መልካምም እንዲሆንልህ ዛሬ ለአንተ የማዝዘውን የእግዚአብሔርን ትእዛዝና ሥርዓት ትጠብቅ ዘንድ ነው እንጂ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ የሚፈልገው ምንድር ነው? እነሆ፥ ሰማይ ሰማየ ሰማያትም፥ ምድርም በእርስዋም ያለው ሁሉ የአምላክህ የእግዚአብሔር ነው።
ዘዳግም 10:12-14 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
“እንግዲህ እስራኤል ሆይ! እግዚአብሔር አምላክህን እንድትፈራው፥ በመንገዱ ሁሉ እንድትሄድ፥ እንድትወደው በሙሉ ልብህና በሙሉ ሐሳብህ እንድታመልከው፥ ለደኅንነትህ ሲባል እኔ ዛሬ የማዝህን የእግዚአብሔር አምላክህን ትእዛዝና ድንጋጌ እንድትጠብቅ ነው እንጂ እርሱ ሌላ ከአንተ ምን ይፈልጋል? ሰማይና ከሰማይ በላይ ያሉ ሰማያት፥ ምድርና በእርስዋም ላይ ያለው ማናቸውም ነገር ሁሉ የእግዚአብሔር ነው።
ዘዳግም 10:12-14 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
“እስራኤል ሆይ፥ አሁንስ ጌታ አምላክህ ከአንተ የሚፈልገው ምንድነው? ነገር ግን ጌታ እግዚአብሔርን እንድትፈራው፥ በመንገዱም ሁሉ እንድትሄድ፥ ጌታ አምላክህንም እንድትወደው፥ በፍጹም ልብህ፥ በፍጹም ነፍስህ እንድታመልከው፥ መልካም እንዲሆንልህ ዛሬ ለአንተ የማዝዘውን የጌታን ትእዛዝና ሥርዓት እንድትጠብቅ ነው። እነሆ፥ ሰማይ ሰማየ ሰማያትም፥ ምድርም በእርሷም ያለው ሁሉ የጌታ የአምላክህ ነው።