ቈላስይስ 3:12-17

ቈላስይስ 3:12-17 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

እን​ግ​ዲህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ መረ​ጣ​ቸው ቅዱ​ሳ​ንና ወዳ​ጆች፥ ምሕ​ረ​ት​ንና ርኅ​ራ​ኄን፥ ቸር​ነ​ት​ንና ትሕ​ት​ናን፥ የው​ሀ​ት​ንና ትዕ​ግ​ሥ​ትን ልበ​ሱት። ባል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ች​ሁን ታገ​ሡ​አ​ቸው፤ እርስ በር​ሳ​ችሁ ይቅር ተባ​ባሉ፤ ባል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ች​ሁን የነ​ቀ​ፋ​ች​ሁ​በ​ትን ሥራ ተዉ፤ ክር​ስ​ቶስ ይቅር እን​ዳ​ላ​ችሁ እና​ን​ተም እን​ዲሁ አድ​ርጉ። ከዚ​ህም ሁሉ ጋር ዘወ​ትር ተፋ​ቀሩ፤ የመ​ጨ​ረ​ሻው ማሰ​ሪያ እርሱ ነውና። በአ​ንድ አካል የተ​ጠ​ራ​ች​ሁ​ለት የክ​ር​ስ​ቶስ ሰላም በል​ባ​ችሁ ጸንቶ ይኑር፤ ክር​ስ​ቶ​ስ​ንም በማ​መ​ስ​ገን ኑሩ። በጥ​በብ ሁሉ እን​ድ​ት​በ​ለ​ጽጉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል በእ​ና​ንተ ዘንድ ይጽና፤ በመ​ን​ፈ​ስም ራሳ​ች​ሁን አስ​ተ​ምሩ፤ ገሥፁ፤ መዝ​ሙ​ር​ንና ምስ​ጋ​ናን፥ የቅ​ድ​ስና ማሕ​ሌ​ት​ንም በል​ባ​ችሁ በጸጋ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘምሩ። በቃ​ልም ቢሆን፥ ወይም በሥራ የም​ታ​ደ​ር​ጉ​ትን ሁሉ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም አድ​ርጉ፤ ስለ እር​ሱም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብን አመ​ስ​ግ​ኑት።

ቈላስይስ 3:12-17 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እንግዲህ የእግዚአብሔር ምርጦችና ቅዱሳን፥ የተወደዳችሁም እንደ መሆናችሁ መጠን ርኅራኄን፥ ቸርነትን፥ ትሕትናን፥ ገርነትን፥ ትዕግሥትን ልበሱ። እርስ በርሳችሁ ተቻቻሉ፤ ከእናንተ አንዱ በሌላው ላይ ቅር የተሰኘበት ነገር ቢኖር ይቅር ተባባሉ፤ ክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ እናንተም ይቅር በሉ። ከዚህም ሁሉ በላይ ሁሉን ነገር ሰብስቦ በማሰር ፍጹም አንድነትን የሚያስገኘውን ፍቅርን ልበሱ። የአንድ አካል ክፍሎች ሆናችሁ በእርግጥ የተጠራችሁት ለዚህ ሰላም ስለ ሆነ የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይንገሥ፤ የምታመሰግኑም ሁኑ። የክርስቶስ ቃል በሙላት በልባችሁ ይኑር፤ በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ ተማማሩ፤ ተመካከሩ፤ በመዝሙርና በውዳሴ፥ በመንፈሳዊ ዜማም እግዚአብሔርን ከልብ እያመሰገናችሁ ዘምሩ። በኢየሱስ በኩል እግዚአብሔር አብን እያመሰገናችሁ በቃልም ሆነ በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት፤ በእርሱም እግዚአብሔር አብን አመስግኑ።

ቈላስይስ 3:12-17

ቈላስይስ 3:12-17 NASVቈላስይስ 3:12-17 NASVቈላስይስ 3:12-17 NASVቈላስይስ 3:12-17 NASVቈላስይስ 3:12-17 NASVቈላስይስ 3:12-17 NASVቈላስይስ 3:12-17 NASV