ቈላስይስ 2:1-7

ቈላስይስ 2:1-7 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ስለ እና​ንተ እና በሎ​ዶ​ቅያ ስላሉ፥ ፊቴ​ንም በሥጋ ስላ​ላ​ዩት ምእ​መ​ናን ሁሉ ምን ያህል እን​ደ​ም​ጋ​ደል ልታ​ውቁ እወ​ዳ​ለሁ። ይኸ​ውም ልቡ​ና​ቸው ደስ ይለው ዘንድ፥ ትም​ህ​ር​ታ​ቸ​ውም በማ​ወቅ፥ በፍ​ቅ​ርና ፍጹ​ም​ነት ባለው ባለ​ጸ​ግ​ነት፥ በጥ​በ​ብና በሃ​ይ​ማ​ኖት፥ ስለ ክር​ስ​ቶ​ስም የሆ​ነ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምክር በማ​ወቅ ይጸና ዘንድ ነው። የተ​ሰ​ወረ የጥ​በ​ብና የም​ክር መዝ​ገብ ሁሉ በእ​ርሱ ዘንድ አለ። ይህ​ንም የም​ላ​ችሁ በሚ​ያ​ባ​ብል ነገር የሚ​ያ​ስ​ታ​ችሁ እን​ዳ​ይ​ኖር ነው። እኔ በሥጋ ከእ​ና​ንተ ዘንድ ባል​ኖ​ርም እን​ኳን፥ በመ​ን​ፈስ ከእ​ና​ንተ ጋር ነኝ፤ እነሆ ጠባ​ያ​ች​ሁ​ንና ሥር​ዐ​ታ​ች​ሁን፥ በክ​ር​ስ​ቶ​ስም ያለ የእ​ም​ነ​ታ​ች​ሁን ጽናት ስለ አየሁ ደስ ይለ​ኛል። እን​ግ​ዲህ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን እንደ ተቀ​በ​ላ​ች​ሁት፥ በእ​ርሱ ተመ​ላ​ለሱ። በእ​ርሱ ተመ​ሥ​ር​ታ​ችሁ ታነጹ፤ በም​ስ​ጋ​ናው ትበዙ ዘንድ፥ በተ​ማ​ራ​ች​ሁት ሃይ​ማ​ኖት ጽኑ።