ሐዋርያት ሥራ 9:3-9 - Compare All Versions

ሐዋርያት ሥራ 9:3-9 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ሲሄ​ድም ወደ ደማ​ስቆ ከተማ አቅ​ራ​ቢያ በደ​ረሰ ጊዜ መብ​ረቅ ድን​ገት ከሰ​ማይ ብልጭ አለ​በት። በም​ድር ላይም ወደቀ፤ ወዲ​ያ​ውም፥ “ሳውል፥ ሳውል፥ ለምን ታሳ​ድ​ደ​ኛ​ለህ?” የሚ​ለ​ውን ቃል ሰማ። ሳው​ልም፥ “አቤቱ፥ አንተ ማነህ?” አለው፤ እር​ሱም፥ “አንተ የም​ታ​ሳ​ድ​ደኝ የና​ዝ​ሬቱ ኢየ​ሱስ ነኝ፤ በሾለ ብረት ላይ ብት​ቆም ለአ​ንተ ይብ​ስ​ሃል” አለው። እር​ሱም እየ​ፈ​ራና እየ​ተ​ን​ቀ​ጠ​ቀጠ፥ “አቤቱ፥ ምን እን​ዳ​ደ​ርግ ትሻ​ለህ?” አለው፤ ጌታም፥ “ተነ​ሣና ወደ ከተማ ግባ፤ በዚ​ያም ልታ​ደ​ር​ገው የሚ​ገ​ባ​ህን ይነ​ግ​ሩ​ሃል” አለው። ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩት ሰዎች ድምፅ እየ​ሰሙ ማን​ንም ሳያዩ ተደ​ን​ቀው ቆሙ። ሳው​ልም ከም​ድር ተነሣ፤ ነገር ግን ዐይ​ኖቹ ተገ​ል​ጠው ሳሉ የሚ​ያ​የው ነገር አል​ነ​በ​ረም፤ እየ​መ​ሩም ወደ ደማ​ስቆ አገ​ቡት። በዚ​ያም ሳያይ ሳይ​በ​ላና ሳይ​ጠጣ ሦስት ቀን ቈየ።

ሐዋርያት ሥራ 9:3-9 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ደማስቆ ለመድረስ ጥቂት ሲቀረው፣ ብርሃን ከሰማይ ድንገት በዙሪያው አንጸባረቀበት፤ እርሱም በመሬት ላይ ወደቀ፤ በዚያ ጊዜም “ሳውል፤ ሳውል፤ ለምን ታሳድደኛለህ?” የሚል ድምፅ ሰማ። ሳውልም፣ “ጌታ ሆይ፤ አንተ ማን ነህ?” አለው። እርሱም እንዲህ አለው፤ “እኔማ አንተ የምታሳድደኝ ኢየሱስ ነኝ። ነገር ግን ተነሣና ወደ ከተማዪቱ ግባ፤ ማድረግ የሚገባህም ይነገርሃል።” ከሳውል ጋራ ይጓዙ የነበሩትም ሰዎች ድምፁን እየሰሙ ማንንም ባላዩ ጊዜ፣ አፋቸውን ይዘው ቆሙ። ሳውልም ከመሬት ላይ ተነሥቶ ዐይኑን ሲገልጥ ምንም ማየት አልቻለም፤ ስለዚህ ሰዎቹ እጁን ይዘው እየመሩ ወደ ደማስቆ አስገቡት። ሦስት ቀንም ታወረ፤ እህል ውሃም አልቀመሰም።

ሐዋርያት ሥራ 9:3-9 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ሲሄድም ወደ ደማስቆ በቀረበ ጊዜ ድንገት በእርሱ ዙሪያ ከሰማይ ብርሃን አንጸባረቀ፤ በምድርም ላይ ወድቆ ሳለ፦ ሳውል ሳውል፥ ስለ ምን ታሳድደኛለህ? የሚለውን ድምፅ ሰማ። ጌታ ሆይ፥ ማን ነህ? አለው። እርሱም፦ አንተ የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ፤ የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል አለው። እየተንቀጠቀጠና እየተደነቀ፦ “ጌታ ሆይ፥ ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ?” አለው። ጌታም፦ “ተነሥተህ ወደ ከተማ ግባና ታደርገው ዘንድ የሚያስፈልግህን ይነግሩሃል” አለው። ከእርሱም ጋር በመንገድ የሄዱ ሰዎች ድምፁን እየሰሙ ማንን ግን ሳያዩ እንደ ዲዳዎች ቁሙ። ሳውልም ከምድር ተነሣ፥ አይኖቹም በተከፈቱ ጊዜ ምንም አላየም፤ እጁንም ይዘው እየመሩ ወደ ደማስቆ አገቡት። ሳያይም ሦስት ቀን ኖረ፤ አልበላምም አልጠጣምም።

ሐዋርያት ሥራ 9:3-9 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ሲሄድም ወደ ደማስቆ በቀረበ ጊዜ በእርሱ ዙሪያ በድንገት ከሰማይ ብርሃን አንጸባረቀ። በዚያን ጊዜ በምድር ላይ ወደቀ፤ “ሳውል፥ ሳውል፥ ለምን ታሳድደኛለህ?” የሚል ድምፅም ሰማ። ሳውልም “ጌታ ሆይ! አንተ ማን ነህ?” አለ፤ እርሱም “እኔ አንተ የምታሳድደኝ ኢየሱስ ነኝ፤ አሁን ግን ተነሥና ወደ ከተማ ግባ፤ ልታደርገው የሚገባህም እዚያ ይነገርሃል” አለው። ከሳውል ጋር ይሄዱ የነበሩ ሰዎች ድምፅ እየሰሙ ማንንም ባለማየታቸው የሚናገሩትን አጥተው፥ ዝም ብለው ቆሙ። ሳውልም ከወደቀበት መሬት ተነሣ፤ ዐይኖቹን በገለጠ ጊዜ ግን ምንም ማየት አልቻለም፤ ስለዚህ ሰዎቹ እጁን ይዘው እየመሩ ወደ ደማስቆ ወሰዱት። ሦስት ቀን ሙሉ ምንም ማየት ሳይችል፥ ሳይበላና ሳይጠጣም ቈየ።

ሐዋርያት ሥራ 9:3-9 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ሲሄድም ወደ ደማስቆ በቀረበ ጊዜ ድንገት በእርሱ ዙሪያ ከሰማይ ብርሃን አንጸባረቀ፤ በምድርም ላይ ወድቆ ሳለ “ሳውል! ሳውል! ስለምን ታሳድደኛለህ?” የሚለውን ድምፅ ሰማ። “ጌታ ሆይ! ማን ነህ?” አለው። እርሱም “አንተ የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ፤ የመውጊያውን ብረት ብትረግጥ ለአንተ ይብስብሃል፤” አለው። እየተንቀጠቀጠና እየተደነቀ “ጌታ ሆይ! ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ?” አለው። ጌታም “ተነሥተህ ወደ ከተማ ግባና ታደርገው ዘንድ የሚያስፈልግህን ይነግሩሃል፤” አለው። ከእርሱም ጋር በመንገድ የሄዱ ሰዎች ድምፁን እየሰሙ ማንን ግን ሳያዩ እንደ ዲዳዎች ቁሙ። ሳውልም ከምድር ተነሣ፤ ዐይኖቹም በተከፈቱ ጊዜ ምንም አላየም፤ እጁንም ይዘው እየመሩ ወደ ደማስቆ አገቡት። ሳያይም ሦስት ቀን ኖረ፤ አልበላምም፤ አልጠጣምም።