ሐዋርያት ሥራ 8:26-29 - Compare All Versions

ሐዋርያት ሥራ 8:26-29 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ክም ፊል​ጶ​ስን ተና​ገ​ረው፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “በቀ​ትር ጊዜ ተነ​ሣና በደ​ቡብ በኩል ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ጋዛ በሚ​ያ​ወ​ር​ደው በም​ድረ በዳው መን​ገድ ሂድ።” ተነ​ሥ​ቶም ሄደ፤ እነ​ሆም፥ የኢ​ት​ዮ​ጵያ ንግ​ሥት የሕ​ን​ደኬ ጃን​ደ​ረባ ከሹ​ሞ​ችዋ የበ​ለጠ፥ በሀ​ብ​ቷም ሁሉ ላይ በጅ​ሮ​ንድ የነ​በረ፥ አንድ የኢ​ት​ዮ​ጵያ ሰው ነበር፤ እር​ሱም ሊሰ​ግድ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም መጣ። ሲመ​ለ​ስም በሰ​ረ​ገ​ላው ላይ ተቀ​ምጦ የነ​ቢዩ የኢ​ሳ​ይ​ያ​ስን መጽ​ሐፍ ያነብ ነበር። መን​ፈስ ቅዱ​ስም ፊል​ጶ​ስን፥ “ሂድ፤ ይህን ሰረ​ገላ ተከ​ተ​ለው” አለው።

ሐዋርያት ሥራ 8:26-29 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

የጌታም መልአክ ፊልጶስን፣ “ተነሥተህ በደቡብ በኩል ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ በሚያወርደው በምድረ በዳው መንገድ ሂድ” አለው፤ እርሱም ተነሥቶ ሄደ። እነሆ፤ የኢትዮጵያ ንግሥት የህንደኬ ባለሟልና የሀብት ንብረቷ ሁሉ አዛዥ የሆነ አንድ ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ አገኘ። ይህም ሰው ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ነበር። ሲመለስም በሠረገላ ተቀምጦ የነቢዩን የኢሳይያስን መጽሐፍ ያነብብ ነበር። መንፈስም ፊልጶስን፣ “ሂድ፤ ወደዚህ ሠረገላ ቅረብ” አለው።

ሐዋርያት ሥራ 8:26-29 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

የጌታም መልአክ ፊልጶስን፦ “ተነሥተህ በደቡብ በኩል ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ ወደሚያወርደው ምድረ በዳ ወደ ሆነ መንገድ ሂድ” አለው። ተነሥቶም ሄደ። እነሆም፥ ህንደኬ የተባለች የኢትዮጵያ ንግሥት አዛዥና ጃንደረባ የነበረ በገንዘብዋም ሁሉ የሠለጠነ አንድ የኢትዮጵያ ሰው ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ነበር፤ ሲመለስም በሰረገላ ተቀምጦ የነቢዩን የኢሳይያስን መጽሐፍ ያነብ ነበር። መንፈስም ፊልጶስን፦ “ወደዚህ ሰረገላ ቅረብና ተገናኝ” አለው።

ሐዋርያት ሥራ 8:26-29 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

የጌታ መልአክ ፊልጶስን፥ “ተነሥና ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ በሚወስደው መንገድ ወደ ደቡብ ሂድ” አለው፤ ያ መንገድ የበረሓ መንገድ ነበር። እርሱም ተነሥቶ ሄደ፤ እነሆ፥ አንድ ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ ለእግዚአብሔር ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዶ ነበር፤ ይህ ሰው ሕንደኬ ለተባለች የኢትዮጵያ ንግሥት ባለሟልና የገንዘብዋ ሁሉ ኀላፊ ነበረ። እርሱ ወደ አገሩ ሲመለስ በሠረገላ ተቀምጦ የነቢዩን የኢሳይያስን መጽሐፍ ያነብ ነበር። በዚህ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ፊልጶስን “ሂድ ወደዚያ ሠረገላ ቅረብና ተገናኘው” አለው።

ሐዋርያት ሥራ 8:26-29 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

የጌታም መልአክ ፊልጶስን “ተነሥተህ በደቡብ በኩል ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ ወደሚያወርደው ምድረ በዳ ወደ ሆነ መንገድ ሂድ፤” አለው። ተነሥቶም ሄደ። እነሆም፥ ሕንደኬ የተባለች የኢትዮጵያ ንግሥት ባለሥልጣን የነበረ በገንዘብዋም ሁሉ ኀላፊ አንድ ኢትዮጵያ ጃንደረባ ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ነበር፤ ሲመለስም በሠረገላ ተቀምጦ የነቢዩን የኢሳይያስን መጽሐፍ ያነብ ነበር። መንፈስም ፊልጶስን “ወደዚህ ሠረገላ ቅረብና ተገናኝ፤” አለው።