ሐዋርያት ሥራ 8:1-9

ሐዋርያት ሥራ 8:1-9 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

በዚያ ወራ​ትም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ባለ​ችው ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ላይ ታላቅ ስደት ሆነ፤ ከሐ​ዋ​ር​ያ​ትም በቀር ሁሉም በይ​ሁ​ዳና በሰ​ማ​ርያ ባሉ አው​ራ​ጃ​ዎች ሁሉ ተበ​ተኑ። እስ​ጢ​ፋ​ኖ​ስ​ንም ደጋግ ሰዎች አን​ሥ​ተው ቀበ​ሩት፤ ታላቅ ልቅ​ሶም አለ​ቀ​ሱ​ለት። ሳውል ግን ገና አብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ና​ትን ይቃ​ወም ነበር፤ የሰ​ው​ንም ቤት ሁሉ ይበ​ረ​ብር ነበር፤ ወን​ዶ​ች​ንም ሴቶ​ች​ንም እየ​ጐ​ተተ ወደ ወኅኒ ቤት ያስ​ገ​ባ​ቸው ነበር። የተ​በ​ተ​ኑት ግን እየ​ተ​ዘ​ዋ​ወሩ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ሰበኩ፥ አስ​ተ​ማ​ሩም። ፊል​ጶ​ስም ወደ ሰማ​ርያ ከተማ ወረደ፤ ስለ ክር​ስ​ቶ​ስም ሰበ​ከ​ላ​ቸው። ሕዝ​ቡም የነ​ገ​ራ​ቸ​ውን በሰ​ሙና ያደ​ር​ገው የነ​በ​ረ​ውን ተአ​ም​ራት በአዩ ጊዜ በአ​ንድ ልብ የፊ​ል​ጶ​ስን ነገር ተቀ​በሉ። ርኩ​ሳን መና​ፍ​ስት ያደ​ሩ​ባ​ቸ​ውም ብዙ​ዎች ነበ​ሩና፥ በታ​ላቅ ቃል እየ​ጮኹ ይወጡ ነበር፤ ብዙ​ዎች ልም​ሾ​ዎ​ችና አን​ካ​ሶ​ችም ይፈ​ወሱ ነበር። በዚ​ያ​ችም ከተማ ታላቅ ደስታ ሆነ። በዚ​ያ​ችም ከተማ ሲሞን የሚ​ባል አንድ ሰው ነበር፤ የሰ​ማ​ርያ ሰዎ​ች​ንም ያስት ነበር፤ ሰው​የዉ ሥራ​የኛ ነበር፤ ራሱ​ንም ታላቅ ያደ​ርግ ነበር።

ሐዋርያት ሥራ 8:1-9 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ሳውልም በእስጢፋኖስ መገደል ተስማምቶ ነበር። በዚያ ቀን በኢየሩሳሌም በነበረችው ቤተ ክርስቲያን ላይ ታላቅ ስደት ተነሣ፤ ከሐዋርያትም በቀር አማኞች በሙሉ በይሁዳና በሰማርያ አውራጃዎች ሁሉ ተበተኑ፤ በመንፈሳዊ ነገር የተጉ ሰዎችም እስጢፋኖስን ቀበሩት፤ ደግሞም እጅግ አለቀሱለት። ሳውል ግን ቤተ ክርስቲያንን ለማጥፋት ታጥቆ ተነሣ፤ ከቤት ወደ ቤት በመግባትም ወንዶችንና ሴቶችን ጐትቶ እያወጣ ወህኒ ቤት ያስገባቸው ነበር። የተበተኑትም በሄዱበት ሁሉ ቃሉን ሰበኩ፤ ፊልጶስም ወደ አንዲት የሰማርያ ከተማ ወርዶ ክርስቶስን ሰበከላቸው። ብዙ ሕዝብም ፊልጶስ የተናገረውን ሲሰሙና ያደረገውንም ታምራዊ ምልክቶች ሲያዩ፣ አንድ ልብ ሆነው ያዳምጡት ነበር። ርኩሳን መናፍስትም እየጮኹ ከብዙ ሰዎች ወጡ፤ ብዙ ሽባዎችና ዐንካሶችም ተፈወሱ፤ ከዚህ የተነሣም በከተማዪቱ ታላቅ ደስታ ሆነ። ነገር ግን ከዚህ ቀደም ሲል በከተማዪቱ ውስጥ እየጠነቈለ የሰማርያን ሰዎች ሁሉ ያስገረመ፣ ሲሞን የሚሉት አንድ ሰው ነበር፤ እርሱም ራሱን እንደ ታላቅ ሰው ይቈጥር ነበር።

ሐዋርያት ሥራ 8:1-9 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ሳውልም በእስጢፋኖስ መገደል ተስማምቶ ነበር፤ እስጢፋኖስ በሞተበት ቀን በኢየሩሳሌም በምትገኘው ቤተ ክርስቲያን ላይ ታላቅ ስደት ተነሣ፤ ከሐዋርያት በቀር አማኞች ሁሉ ወደ ይሁዳና ወደ ሰማርያ ምድር ተበተኑ። አንዳንድ መንፈሳውያን ሰዎች እስጢፋኖስን ቀበሩት፤ በታላቅ ድምፅም እየጮኹ አለቀሱለት። ሳውል ግን ቤተ ክርስቲያንን ለማጥፋት ይጥር ነበር፤ ከቤት ወደ ቤትም እየገባ ወንዶችና ሴቶች አማኞችን እየጐተተ ያወጣ ነበር፤ ወደ እስር ቤትም ያስገባቸው ነበር። የተበተኑትም አማኞች በሄዱበት ስፍራ ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ያስተምሩ ነበር። ፊልጶስም ወደ ሰማርያ ከተማ ሄዶ ሰዎቹን ስለ መሲሕ አስተማራቸው። ሰዎቹም የፊልጶስን ቃል በሰሙና የሚያደርጋቸውን ተአምራት ባዩ ጊዜ በአንድ ሐሳብ በጥንቃቄ ያዳምጡት ነበር። ርኩሳን መናፍስትም በታላቅ ድምፅ እየጮኹ ከብዙ ሰዎች ይወጡ ነበር፤ ብዙ ሽባዎችና አንካሶችም ይድኑ ነበር። ስለዚህ በዚያች ከተማ ታላቅ ደስታ ሆነ። በዚያች ከተማ ስምዖን የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤ ይህ ሰው በከተማይቱ ውስጥ አስማት እያደረገ የሰማርያን ሕዝብ ሲያስደንቅ ቈይቶአል፤ “እኔ ትልቅ ሰው ነኝ!” እያለም ይናገር ነበር።