ሐዋርያት ሥራ 5:38-39
ሐዋርያት ሥራ 5:38-39 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
አሁንም እላችኋለሁ፥ ከእነዚህ ሰዎች ራቁ፤ ተዉአቸውም፤ ይህ ምክራቸው፥ ይህም ሥራቸው ከሰው የተገኘ ከሆነ ያልፋል ይጠፋልም። ከእግዚአብሔር የመጣ ከሆነ ግን ልታፈርሱት አትችሉም፤ ከእግዚአብሔርም ጋር እንደሚጣላ አትሁኑ።”
ሐዋርያት ሥራ 5:38-39 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ስለዚህ አሁንም የምላችሁ፦ እነዚህን ሰዎች ተዉአቸው! አትንኳቸው! ሐሳባቸው ወይም አድራጎታቸው ከሰው ከሆነ ይጠፋልና፤ ከእግዚአብሔር ከሆነ ግን ልትገቷቸው አትችሉም፤ እንዲያውም ከእግዚአብሔር ጋራ ስትጣሉ ትገኙ ይሆናል።”
ሐዋርያት ሥራ 5:38-39 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
አሁንም እላችኋለሁ፦ ከእነዚህ ሰዎች ተለዩ ተዉአቸውም፤ ይህ አሳብ ወይም ይህ ሥራ ከሰው እንደ ሆነ ይጠፋልና፤ ከእግዚአብሔር እንደ ሆነ ግን ታጠፉአቸው ዘንድ አይቻላችሁም፥ በእርግጥ ከእግዚአብሔር ጋር ስትጣሉ ምናልባት እንዳትገኙ።”