ሐዋርያት ሥራ 5:31 - Compare All Versions

ሐዋርያት ሥራ 5:31 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

እርሱም ለእስራኤል ንስሓንና የኀጢአትን ስርየት ይሰጥ ዘንድ፣ እግዚአብሔር የሁሉ ራስና አዳኝ አድርጎ በቀኙ ከፍ ከፍ አደረገው።

ሐዋርያት ሥራ 5:31 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

እግዚአብሔር ለእስራኤል ሕዝብ ንስሓንና የኃጢአትን ይቅርታ እንዲሰጥ ኢየሱስን መሪና አዳኝ አድርጎ በቀኙ በክብር እንዲቀመጥ አድርጎታል፤

ሐዋርያት ሥራ 5:31 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እር​ሱን ለእ​ስ​ራ​ኤል ንስ​ሓን፥ የኀ​ጢ​አ​ት​ንም ስር​የት ይሰጥ ዘንድ ራስም አዳ​ኝም አደ​ረ​ገው፤ በቀ​ኙም አስ​ቀ​መ​ጠው።

ሐዋርያት ሥራ 5:31 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ይህን እግዚአብሔር፥ ለእስራኤል ንስሐን የኃጢአትንም ስርየት ይሰጥ ዘንድ፥ ራስም መድኃኒትም አድርጎ በቀኙ ከፍ ከፍ አደረገው።

ሐዋርያት ሥራ 5:31 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ይህን እግዚአብሔር፥ ለእስራኤል ንስሐን የኃጢአትንም ስርየት እንዲሰጥ፥ ራስም መድኃኒትም አድርጎ በቀኙ ከፍ ከፍ አደረገው።