ሐዋርያት ሥራ 5:12-16
ሐዋርያት ሥራ 5:12-16 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
በሐዋርያት እጅም በሕዝቡ ዘንድ ተአምራትና ድንቅ ሥራዎች ይሠሩ ነበር፤ በቤተ መቅደስም በሰሎሞን መመላለሻ በአንድነት ነበሩ። ሕዝቡም እጅግ ያከብሩአቸው ነበረ። ከሌሎችም ይቀርባቸው ዘንድ አንድ ስንኳን የሚደፍር አልነበረም። በጌታችንም የሚያምኑ ብዙዎች ይጨመሩ ነበር፤ ወንዶችና ሴቶችም ብዙዎች ነበሩ። ጴጥሮስም አልፎ ሲሄድ ጥላው ያርፍባቸው ዘንድ ድውዮችን በአልጋና በቃሬዛ እያመጡ በአደባባይ ያስቀምጡአቸው ነበር፤ ደግሞም በኢየሩሳሌም ዙሪያ ከአሉ ከተሞች ብዙዎች ይመጡ ነበር፤ የታመሙትንና ክፉዎች አጋንንት የያዙአቸውንም ያመጡ ነበር፥ ሁሉም ይፈወሱ ነበር።
ሐዋርያት ሥራ 5:12-16 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ሐዋርያትም በሕዝቡ መካከል ብዙ ታምራዊ ምልክቶችንና ድንቅ ሥራዎችን አደረጉ፤ አማኞቹም ሁሉ “የሰሎሞን ደጅ” በተባለው መመላለሻ ይሰበሰቡ ነበር። ከእነርሱ ጋራ ሊቀላቀል የደፈረ ማንም አልነበረም፤ ሆኖም ሕዝቡ እጅግ ያከብሯቸው ነበር፤ ብዙ ወንዶችና ሴቶችም ከጊዜ ወደ ጊዜ በጌታ እያመኑ ወደ እነርሱ ይጨመሩ ነበር። ከዚህም የተነሣ፣ ጴጥሮስ በዚያ ሲያልፍ፣ ቢያንስ ጥላው እንኳ በጥቂቶች ላይ እንዲያርፍባቸው በማለት ሕመምተኞችን ወደ ውጭ እያወጡ በዐልጋና በቃሬዛ በመንገድ ላይ ያስተኙ ነበር። በኢየሩሳሌም አካባቢ ከሚገኙ ከተሞች፣ ሕመምተኞችንና በርኩሳን መናፍስት የሚሠቃዩትን ይዘው የሚመጡት ሰዎች አካባቢውን ያጨናንቁት ነበር፤ የመጡትም ሁሉ ይፈወሱ ነበር።
ሐዋርያት ሥራ 5:12-16 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በሐዋርያትም እጅ ብዙ ምልክትና ድንቅ በሕዝብ መካከል ይደረግ ነበር፤ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው በሰሎሞን ደጅ መመላለሻ ነበሩ። ከሌሎችም አንድ ስንኳ ሊተባበራቸው የሚደፍር አልነበረም፥ ሕዝቡ ግን ያከብሩአቸው ነበር፤ የሚያምኑትም ከፊት ይልቅ ለጌታ ይጨመሩለት ነበር፤ ወንዶችና ሴቶችም ብዙ ነበሩ። ስለዚህም ጴጥሮስ ሲያልፍ ጥላውም ቢሆን ከእነርሱ አንዱን ይጋርድ ዘንድ ድውያንን ወደ አደባባይ አውጥተው በአልጋና በወሰካ ያኖሩአቸው ነበር። ደግሞም በኢየሩሳሌም ዙሪያ ካለችው ከተማ ድውያንንና በርኵሳን መናፍስት የተሣቀዩትን እያመጡ ብዙ ሰዎች ይሰበስቡ ነበር፤ ሁሉም ይፈወሱ ነበር።
ሐዋርያት ሥራ 5:12-16 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ብዙ ተአምራትና ድንቅ ነገሮች በሕዝቡ መካከል በሐዋርያት እጅ ይደረጉ ነበር፤ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው በሰሎሞን መመላለሻ ይሰበሰቡ ነበር። ከእነርሱ ውጪ ከሆኑት ሰዎች አንድ እንኳ ከእነርሱ ጋር ለመሆን የሚደፍር አልነበረም፤ ይሁን እንጂ ሕዝቡ ያከብራቸው ነበር። በጌታ የሚያምኑ ወንዶችና ሴቶች ቊጥራቸው በጣም እየበዛ ይሄድ ነበር። ሰዎች ብዙ በሽተኞችን ወደ መንገድ እያወጡ በአልጋ ላይና በቃሬዛ ላይ ያስተኙአቸው ነበር፤ እንዲህም ያደረጉት ጴጥሮስ በዚያ በኩል ሲያልፍ ጥላው እንኳ በአንዳንዶቹ ላይ እንዲያርፍባቸው ነበር። ሰዎች በኢየሩሳሌም ዙሪያ ካሉት ከተሞች በሽተኞቻቸውንና በርኩሳን መናፍስት የሚሠቃዩትን ያመጡ ነበር፤ ሁሉም ይድኑ ነበር።
ሐዋርያት ሥራ 5:12-16 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
በሐዋርያትም እጅ ብዙ ምልክትና ድንቅ በሕዝብ መካከል ይደረግ ነበር፤ ሁሉም በአንድ ልብ ሆነው በሰሎሞን ደጅ መመላለሻ ነበሩ። ከሌሎችም አንድ ስንኳ ሊተባበራቸው የሚደፍር አልነበረም፤ ሕዝቡ ግን ያከብሩአቸው ነበር፤ የሚያምኑትም ከፊት ይልቅ ለጌታ ይጨመሩለት ነበር፤ ወንዶችና ሴቶችም ብዙ ነበሩ። ስለዚህም ጴጥሮስ ሲያልፍ ጥላውም ቢሆን ከእነርሱ አንዱን ይጋርድ ዘንድ ድውያንን ወደ አደባባይ አውጥተው በአልጋና በወሰካ ያኖሩአቸው ነበር። ደግሞም በኢየሩሳሌም ዙሪያ ካለችው ከተማ ድውያንንና በርኩሳን መናፍስት የተሠቃዩትን እያመጡ ብዙ ሰዎች ይሰበስቡ ነበር፤ ሁሉም ይፈወሱ ነበር።