ሐዋርያት ሥራ 4:1-8

ሐዋርያት ሥራ 4:1-8 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ሕዝ​ቡ​ንም ሲያ​ስ​ተ​ምሩ ሊቃነ ካህ​ና​ትና የቤተ መቅ​ደስ ሹም፥ ሰዱ​ቃ​ው​ያ​ንም መጡ። ሕዝ​ቡን ስለ አስ​ተ​ማ​ሩና በኢ​የ​ሱ​ስም የሙ​ታ​ንን ትን​ሣኤ ስለ ሰበኩ በእ​ነ​ርሱ ተና​ደዱ። እጃ​ቸ​ው​ንም ዘር​ግ​ተው ያዙ​አ​ቸው፤ ጊዜ​ዉም ፈጽሞ መሽቶ ነበ​ርና እስከ ማግ​ሥቱ ድረስ በወ​ኅኒ ቤት አገ​ቡ​አ​ቸው። ቃሉ​ንም ሰም​ተው ያመኑ ብዙ ሰዎች ናቸው፤ ያመ​ኑት ወን​ዶች ቍጥ​ርም አም​ስት ሺህ ያህል ሆነ። በማ​ግ​ሥ​ቱም አለ​ቆ​ቻ​ቸ​ውና ሽማ​ግ​ሎች፥ ጻፎ​ችም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተሰ​በ​ሰቡ። ሊቀ ካህ​ናቱ ሐና፥ ቀያ​ፋም፥ ዮሐ​ን​ስና እለ​እ​ስ​ክ​ን​ድ​ሮ​ስም፥ የሊቀ ካህ​ና​ቱም ወገን ሁሉ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ነበሩ። በአ​ደ​ባ​ባ​ይም አቆ​ሙና፥ “እና​ንተ ይህን በማን ስምና በማን ኀይል አደ​ረ​ጋ​ች​ሁት?” ብለው መረ​መ​ሩ​አ​ቸው። ያን​ጊ​ዜም በጴ​ጥ​ሮስ መን​ፈስ ቅዱስ ሞላ​በ​ትና እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ የሕ​ዝብ አለ​ቆ​ችና ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሆይ፥ ስሙ፤

ሐዋርያት ሥራ 4:1-8 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ጴጥሮስና ዮሐንስ ለሕዝቡ እየተናገሩ ሳሉ፣ ካህናትና የቤተ መቅደሱ ጥበቃ ኀላፊ እንዲሁም ሰዱቃውያን ድንገት ወደ እነርሱ መጡ። እነርሱም ሐዋርያት ሕዝቡን በማስተማራቸውና በኢየሱስ ስለ ተገኘው ትንሣኤ ሙታን በመስበካቸው እጅግ ተቈጡ። ጴጥሮስና ዮሐንስን ያዟቸው፤ ጊዜውም ምሽት ስለ ነበረ እስኪነጋ ድረስ ወህኒ ቤት አሳደሯቸው። ይሁን እንጂ ቃሉን ከሰሙት መካከል ብዙዎቹ አመኑ፤ የወንዶቹም ቍጥር ወደ ዐምስት ሺሕ ከፍ አለ። በማግስቱም አለቆቻቸውና፣ ሽማግሌዎቻቸው እንዲሁም ጸሐፍት በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ። ሊቀ ካህናቱ ሐና፣ ቀያፋ፣ ዮሐንስ፣ እስክንድሮስና የሊቀ ካህናቱ ቤተ ዘመዶች ሁሉ በዚያ ተገኝተው ነበር። እነርሱም ጴጥሮስንና ዮሐንስን በመካከል አቁመው፣ “ይህን ያደረጋችሁት በምን ኀይል ወይም በማን ስም ነው?” ብለው ጠየቋቸው። በዚህ ጊዜ፣ ጴጥሮስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ የሕዝብ አለቆችና ሽማግሌዎች ሆይ፤

ሐዋርያት ሥራ 4:1-8 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ጴጥሮስና ዮሐንስ ለሕዝቡ ሲናገሩ ሳሉ ካህናትና የቤተ መቅደሱ የዘበኞች አለቃ እንዲሁም ሰዱቃውያን ወደ እነርሱ መጡና ሁለቱ ሐዋርያት የኢየሱስን ከሞት መነሣት ለሕዝቡ በማስተማራቸውና በዚህም የሙታን ትንሣኤ መኖሩን በማስረዳታቸው ተቈጡ። ስለዚህ ያዙአቸውና ጊዜው መሽቶ ስለ ነበረ እስከ ማግስቱ ድረስ በወህኒ ቤት እንዲቈዩ አደረጉአቸው። ነገር ግን ቃላቸውን ከሰሙት ሰዎች ብዙዎቹ አመኑ፤ የአመኑትም ሰዎች ቊጥር ወደ አምስት ሺህ ከፍ አለ። በማግስቱ የአይሁድ አለቆችና ሽማግሌዎች፥ የሕግ መምህራንም በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ። ከተሰበሰቡት ሰዎች መካከል የካህናት አለቃው ሐናና ቀያፋ፥ ዮሐንስና እስክንድሮስ፥ የካህናት አለቃው ቤተሰቦች ሁሉ ይገኙባቸዋል፤ እነርሱም ሁለቱን ሐዋርያት በመካከላቸው አቁመው፥ “ይህን ያደረጋችኹት በምን ኀይል ወይም በማን ስም ነው?” ሲሉ ጠየቁአቸው። በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እናንተ የሕዝብ አለቆችና ሽማግሌዎች ሆይ!