ሐዋርያት ሥራ 4:1-37 - Compare All Versions

ሐዋርያት ሥራ 4:1-37 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ሕዝ​ቡ​ንም ሲያ​ስ​ተ​ምሩ ሊቃነ ካህ​ና​ትና የቤተ መቅ​ደስ ሹም፥ ሰዱ​ቃ​ው​ያ​ንም መጡ። ሕዝ​ቡን ስለ አስ​ተ​ማ​ሩና በኢ​የ​ሱ​ስም የሙ​ታ​ንን ትን​ሣኤ ስለ ሰበኩ በእ​ነ​ርሱ ተና​ደዱ። እጃ​ቸ​ው​ንም ዘር​ግ​ተው ያዙ​አ​ቸው፤ ጊዜ​ዉም ፈጽሞ መሽቶ ነበ​ርና እስከ ማግ​ሥቱ ድረስ በወ​ኅኒ ቤት አገ​ቡ​አ​ቸው። ቃሉ​ንም ሰም​ተው ያመኑ ብዙ ሰዎች ናቸው፤ ያመ​ኑት ወን​ዶች ቍጥ​ርም አም​ስት ሺህ ያህል ሆነ። በማ​ግ​ሥ​ቱም አለ​ቆ​ቻ​ቸ​ውና ሽማ​ግ​ሎች፥ ጻፎ​ችም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተሰ​በ​ሰቡ። ሊቀ ካህ​ናቱ ሐና፥ ቀያ​ፋም፥ ዮሐ​ን​ስና እለ​እ​ስ​ክ​ን​ድ​ሮ​ስም፥ የሊቀ ካህ​ና​ቱም ወገን ሁሉ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ነበሩ። በአ​ደ​ባ​ባ​ይም አቆ​ሙና፥ “እና​ንተ ይህን በማን ስምና በማን ኀይል አደ​ረ​ጋ​ች​ሁት?” ብለው መረ​መ​ሩ​አ​ቸው። ያን​ጊ​ዜም በጴ​ጥ​ሮስ መን​ፈስ ቅዱስ ሞላ​በ​ትና እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ የሕ​ዝብ አለ​ቆ​ችና ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሆይ፥ ስሙ፤ ዛሬ ለበ​ሽ​ተ​ኛው በተ​ደ​ረ​ገው ረድ​ኤት ምክ​ን​ያት በእ​ና​ንተ ዘንድ እኛ የሚ​ፈ​ረ​ድ​ብን ከሆነ እን​ግ​ዲያ ይህ ሰው በምን ዳነ? እን​ግ​ዲህ እና​ንተ ሁላ​ችሁ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ወገን ሁሉ፥ እና​ንተ በሰ​ቀ​ላ​ች​ሁት፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከሙ​ታን ለይቶ በአ​ስ​ነ​ሣው በና​ዝ​ሬቱ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም ይህ ሰው እንደ ዳነና በፊ​ታ​ች​ሁም እንደ ቆመ በር​ግጥ ዕወቁ። ይህ እና​ንተ ግን​በ​ኞች የና​ቃ​ች​ሁት ድን​ጋይ ነውና፤ እር​ሱም የማ​ዕ​ዘን ራስ ሆነ። መዳ​ንም በሌላ በማ​ንም የለም፤ ከሰ​ማይ በታች እን​ድ​ን​በት ዘንድ የሚ​ገ​ባን ለሰው የተ​ሰጠ ሌላ ስም ከቶ የለ​ምና።” ጴጥ​ሮ​ስና ዮሐ​ን​ስም ግልጥ አድ​ር​ገው ሲና​ገሩ ባዩ​አ​ቸው ጊዜ፥ ያል​ተ​ማ​ሩና መጽ​ሐ​ፍን የማ​ያ​ውቁ ሰዎች እንደ ሆኑ ዐው​ቀው አደ​ነቁ፤ ሁል​ጊ​ዜም ከኢ​የ​ሱስ ጋር እንደ ነበሩ ዐወቁ። ያን የዳ​ነ​ውን ሰውም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ቆሞ በአ​ዩት ጊዜ የሚ​ሉ​ትን አጡ። ከሸ​ን​ጎ​ውም ጥቂት ፈቀቅ አደ​ረ​ጉ​አ​ቸ​ውና እርስ በር​ሳ​ቸው ተነ​ጋ​ገሩ። እን​ዲ​ህም አሉ፥ “እነ​ዚ​ህን ሰዎች ምን እና​ድ​ር​ጋ​ቸው? እነሆ፥ በእ​ነ​ርሱ የሚ​ደ​ረ​ገው ተአ​ምር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በሚ​ኖ​ሩት ሁሉ ዘንድ ታወቀ፤ ግል​ጥም ሆነ፤ ልን​ሰ​ው​ረ​ውም አን​ች​ልም። ነገር ግን በሕ​ዝቡ ዘንድ እጅግ እን​ዳ​ይ​ስ​ፋፋ ዳግ​መኛ በኢ​የ​ሱስ ስም ሰውን እን​ዳ​ያ​ስ​ተ​ምሩ አጠ​ን​ክ​ረን እን​ገ​ሥ​ጻ​ቸው።” ጠር​ተ​ውም፦“ በኢ​የ​ሱስ ስም ፈጽሞ አት​ና​ገሩ አታ​ስ​ተ​ም​ሩም” ብለው አዘ​ዙ​አ​ቸው። ጴጥ​ሮ​ስና ዮሐ​ን​ስም እን​ዲህ ብለው መለ​ሱ​ላ​ቸው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያይ​ደለ እና​ን​ተን ልን​ሰማ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይገ​ባ​ልን? እስኪ እና​ንተ ራሳ​ችሁ ፍረዱ። እኛስ ያየ​ነ​ው​ንና የሰ​ማ​ነ​ውን ከመ​ና​ገር ዝም እንል ዘንድ አን​ች​ልም።” እነ​ር​ሱ​ንም የሚ​ቀ​ጡ​በት ምክ​ን​ያት ስለ አጡ​ባ​ቸው ገሥ​ጸው ለቀ​ቁ​አ​ቸው፤ ስለ ተደ​ረ​ገው ተአ​ምር ሕዝቡ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግኑ ነበ​ርና። ይህ የድ​ኅ​ነት ምል​ክት ለተ​ደ​ረ​ገ​ለት ለዚያ ሰው ከአ​ርባ ዓመት ይበ​ል​ጠው ነበ​ረና። ተፈ​ት​ተ​ውም ወደ ሰዎ​ቻ​ቸው ሄዱ፤ ሊቃነ ካህ​ና​ትና ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችም ያሉ​አ​ቸ​ውን ሁሉ ነገ​ሩ​አ​ቸው። ይህ​ንም በሰሙ ጊዜ በአ​ን​ድ​ነት ቃላ​ቸ​ውን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፍ አድ​ር​ገው እን​ዲህ አሉ፥ “ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን፥ ባሕ​ር​ንም፥ በው​ስ​ጣ​ቸው ያለ​ው​ንም ሁሉ የፈ​ጠ​ርህ አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ አንተ ራስህ በአ​ባ​ታ​ችን በባ​ሪ​ያህ በዳ​ዊት አፍ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ እን​ዲህ ብለህ የተ​ና​ገ​ርህ፦ አሕ​ዛብ ለምን ተሰ​በ​ሰቡ? ሕዝ​ቡስ ለምን ከንቱ ነገ​ርን ተና​ገሩ? የም​ድር ነገ​ሥ​ታት ለምን ተነሡ? አለ​ቆ​ችስ ከእ​ነ​ርሱ ጋር አብ​ረው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና በመ​ሲሑ ላይ ለምን ዶለቱ? በቀ​ባ​ኸው በቅ​ዱስ ልጅህ ላይ ሄሮ​ድ​ስና ጰን​ጤ​ና​ዊው ጲላ​ጦስ ከወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸ​ውና ከእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ ጋር በእ​ው​ነት በዚች ሀገር ላይ ዶለቱ። እጅ​ህና ምክ​ርህ እን​ዲ​ደ​ረግ የወ​ሰ​ኑ​ትን ይፈ​ጽሙ ዘንድ። አሁ​ንም አቤቱ፥ ትም​ክ​ህ​ታ​ቸ​ውን ተመ​ል​ከት፤ ቃል​ህ​ንም በግ​ልጥ ያስ​ተ​ምሩ ዘንድ ለባ​ሮ​ችህ ስጣ​ቸው። በቅ​ዱሱ ልጅ​ህም በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም ሕሙ​ማ​ንን ትፈ​ውስ ዘንድ ተአ​ም​ራ​ት​ንና ድንቅ ሥራ​ንም ታደ​ርግ ዘንድ እጅ​ህን ዘርጋ።” ሲጸ​ል​ዩም በአ​ን​ድ​ነት ተሰ​ብ​ስ​በው የነ​በ​ሩ​በት ቦታ ተና​ወጠ፤ በሁ​ሉም ላይ መን​ፈስ ቅዱስ መላ​ባ​ቸ​ውና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል በግ​ልጥ አስ​ተ​ማሩ። ያመ​ኑ​ትም ሁሉ አንድ ልብና አን​ዲት ነፍስ ሆነው ይኖሩ ነበር፤ በው​ስ​ጣ​ቸ​ውም የሁሉ ገን​ዘብ በአ​ን​ድ​ነት ነበር እንጂ “ይህ የእኔ ገን​ዘብ ነው” የሚል አል​ነ​በ​ረም። ሐዋ​ር​ያ​ትም የጌ​ታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ትን​ሣኤ በታ​ላቅ ኀይል ይመ​ሰ​ክሩ ነበር፤ በሕ​ዝ​ቡም ዘንድ ታላቅ ጸጋ ነበ​ራ​ቸው። ከእ​ነ​ር​ሱም አንድ ስንኳ ችግ​ረኛ አል​ነ​በ​ረም፤ ቤትና መሬት ያላ​ቸ​ውም ሁሉ እየ​ሸጡ ገን​ዘ​ቡን ያመጡ ነበር። አም​ጥ​ተ​ውም በሐ​ዋ​ር​ያት እግር አጠ​ገብ ያኖ​ሩት ነበር፤ እነ​ር​ሱም ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ እንደ ፍላ​ጎቱ ይከ​ፍ​ሉት ነበር። በሐ​ዋ​ር​ያ​ትም ዘንድ ትር​ጓ​ሜዉ የመ​ጽ​ና​ናት ልጅ የሚ​ሆን በር​ና​ባስ የተ​ባለ የሌዊ ወገን ስሙን ዮሴፍ የሚ​ሉት አንድ የቆ​ጵ​ሮስ ሰው ነበር። እር​ሻም ነበ​ረ​ውና ሽጦ ገን​ዘ​ቡን አም​ጥቶ በሐ​ዋ​ር​ያት እግር አጠ​ገብ አኖ​ረው።

ሐዋርያት ሥራ 4:1-37 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ጴጥሮስና ዮሐንስ ለሕዝቡ እየተናገሩ ሳሉ፣ ካህናትና የቤተ መቅደሱ ጥበቃ ኀላፊ እንዲሁም ሰዱቃውያን ድንገት ወደ እነርሱ መጡ። እነርሱም ሐዋርያት ሕዝቡን በማስተማራቸውና በኢየሱስ ስለ ተገኘው ትንሣኤ ሙታን በመስበካቸው እጅግ ተቈጡ። ጴጥሮስና ዮሐንስን ያዟቸው፤ ጊዜውም ምሽት ስለ ነበረ እስኪነጋ ድረስ ወህኒ ቤት አሳደሯቸው። ይሁን እንጂ ቃሉን ከሰሙት መካከል ብዙዎቹ አመኑ፤ የወንዶቹም ቍጥር ወደ ዐምስት ሺሕ ከፍ አለ። በማግስቱም አለቆቻቸውና፣ ሽማግሌዎቻቸው እንዲሁም ጸሐፍት በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ። ሊቀ ካህናቱ ሐና፣ ቀያፋ፣ ዮሐንስ፣ እስክንድሮስና የሊቀ ካህናቱ ቤተ ዘመዶች ሁሉ በዚያ ተገኝተው ነበር። እነርሱም ጴጥሮስንና ዮሐንስን በመካከል አቁመው፣ “ይህን ያደረጋችሁት በምን ኀይል ወይም በማን ስም ነው?” ብለው ጠየቋቸው። በዚህ ጊዜ፣ ጴጥሮስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ የሕዝብ አለቆችና ሽማግሌዎች ሆይ፤ ዛሬ ለዚህ ሽባ ሰው ስለ ተደረገው በጎ ሥራ፣ እንዴት እንደ ዳነ የምትጠይቁን ከሆነ፣ እናንተ በሰቀላችሁት፣ እግዚአብሔር ግን ከሙታን ባስነሣው በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም መዳኑንና ፊታችሁ መቆሙን እናንተም ሆናችሁ የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ይህን ይወቅ። እርሱም፣ “ ‘እናንተ ግንበኞች የናቃችሁት፣ የማእዘን ራስ የሆነው ድንጋይ’ ነው። ድነት በሌላ በማንም አይገኝም፤ እንድንበት ዘንድ ለሰዎች የተሰጠ ከዚህ ስም በቀር ሌላ ስም ከሰማይ በታች የለምና።” ሰዎቹም፣ ጴጥሮስና ዮሐንስ እንዲህ በድፍረት ሲናገሩ ባዩአቸው ጊዜ፣ ያልተማሩ ተራ ሰዎች መሆናቸውን ተረድተው ተደነቁ፤ ከኢየሱስ ጋራ እንደ ነበሩም ተገነዘቡ። የተፈወሰውን ሰው እዚያው ከእነርሱ ጋራ ቆሞ ስላዩት የሚናገሩበትን ሰበብ ዐጡ። ስለዚህ ከሸንጎው እንዲያወጧቸው አዘዙ፤ ከዚያም በአንድነት ተሰብስበው ተመካከሩ፤ እንዲህም ተባባሉ፤ “እንግዲህ እነዚህን ሰዎች ምን እናድርጋቸው? በኢየሩሳሌም የሚኖር ሁሉ በእነርሱ እጅ የተደረገውን ድንቅ ታምር ዐውቋል፣ ስለዚህ ይህን ማስተባበል አንችልም፤ ይሁን እንጂ፣ ይህ ነገር ከእንግዲህ በሕዝቡ መካከል ይበልጥ እንዳይስፋፋ፣ እነዚህም ሰዎች ዳግመኛ በዚህ ስም ለማንም እንዳይናገሩ እናስጠንቅቃቸው።” ከጠሯቸውም በኋላ፣ በኢየሱስ ስም ፈጽሞ እንዳይናገሩና እንዳያስተምሩ አዘዟቸው። ጴጥሮስና ዮሐንስ ግን መልሰው እንዲህ አሏቸው፤ “ከእግዚአብሔር ይልቅ ለእናንተ መታዘዝ በእግዚአብሔር ፊት ይገባ እንደ ሆነ እስኪ እናንተው ፍረዱ! እኛስ ያየነውንና የሰማነውን ከመናገር ወደ ኋላ አንልም።” እንደ ገና ከዛቱባቸው በኋላም ለቀቋቸው፤ ምክንያቱም ሕዝቡ ሁሉ ስለ ሆነው ነገር እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ስለ ነበር ሊቀጧቸው አልቻሉም፤ በዚህ ታምር የተፈወሰውም ሰው ዕድሜው ከአርባ ዓመት በላይ ነበርና። ጴጥሮስና ዮሐንስም ከተፈቱ በኋላ ወደ ወገኖቻቸው ተመልሰው፣ የካህናት አለቆችና ሽማግሌዎች ያሏቸውን ሁሉ ነገሯቸው። እነርሱም ይህን በሰሙ ጊዜ ድምፃቸውን በአንድነት ወደ እግዚአብሔር ከፍ አድርገው እንዲህ አሉ፤ “ልዑል ጌታ ሆይ፤ አንተ ሰማይንና ምድርን፣ ባሕርንም፣ በውስጣቸውም የሚኖሩትን ሁሉ ፈጥረሃል፤ በመንፈስ ቅዱስም አማካይነት በብላቴናህ በአባታችን በዳዊት አፍ እንዲህ ብለህ ተናግረሃል፤ “ ‘አሕዛብ ለምን በቍጣ ተነሣሡ? ሕዝቡስ ለምን በከንቱ አሤሩ? የምድር ነገሥታት ተነሡ፤ ገዦችም በጌታና በመሲሑ ላይ ሊመክሩ ተሰበሰቡ።’ በእውነትም ሄሮድስና ጳንጥዮስ ጲላጦስ ከአሕዛብና ከእስራኤል ሕዝብ ጋራ በዚህች ከተማ አንተ በቀባኸው በቅዱሱ ብላቴናህ በኢየሱስ ላይ ለማሤር ተሰበሰቡ፤ ይህም የሆነው የአንተ ክንድና ፈቃድ ጥንት የወሰኑት እንዲፈጸም ነው። አሁንም ጌታ ሆይ፤ ዛቻቸውን ተመልከት፤ ባሮችህም ቃልህን በፍጹም ድፍረት መናገር እንዲችሉ አድርጋቸው። ለመፈወስ እጅህን ዘርጋ፤ በቅዱሱ ብላቴናህም በኢየሱስ ስም ድንቅና ታምራት አድርግ።” ከጸለዩም በኋላ የነበሩበት ስፍራ ተናወጠ፤ ሁሉም በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ፤ የእግዚአብሔርንም ቃል በድፍረት ተናገሩ። ያመኑትም ሁሉ በአንድ ልብና በአንድ ሐሳብ ተስማምተው ነበር፤ ያላቸውም ሁሉ የጋራ ነበር እንጂ የራሱ የሆነውን ሀብት እንኳ እንደ ግሉ የሚቈጥር ማንም አልነበረም። ሐዋርያትም ስለ ጌታ ኢየሱስ ትንሣኤ በታላቅ ኀይል መመስከራቸውን ቀጠሉ፤ በሁላቸውም ላይ ታላቅ ጸጋ ነበር። ከመካከላቸውም አንድ ችግረኛ አልነበረም፤ ምክንያቱም መሬትም ሆነ ቤት የነበራቸውን ሁሉ እየሸጡ ዋጋውን አምጥተው፣ በሐዋርያት እግር ሥር በማስቀመጥ ለእያንዳንዱ በሚያስፈልገው መጠን ያካፍሉት ነበር። በቆጵሮስ የሚኖር ዮሴፍ የሚባል አንድ ሌዋዊ ነበረ፤ ሐዋርያትም “በርናባስ” ብለው ጠሩት፤ ትርጕሙም “የመጽናናት ልጅ” ማለት ነው፤ እርሱም መሬቱን ሸጦ፣ ገንዘቡን አምጥቶ በሐዋርያት እግር ሥር አስቀመጠ።

ሐዋርያት ሥራ 4:1-37 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ለሕዝቡም ሲናገሩ የካህናት አለቆችና የመቅደስ አዛዥ ሰዱቃውያንም፥ ሕዝቡን ስለ አስተማሩና በኢየሱስ የሙታንን ትንሣኤ ስለ ሰበኩ ተቸግረው፥ ወደ እነርሱ ቀረቡ፥ እጃቸውንም ጭነውባቸው አሁን መሽቶ ነበርና እስከ ማግሥቱ ድረስ በወኅኒ አኖሩአቸው። ነገር ግን ቃሉን ከሰሙት ብዙዎች አመኑ፥ የወንዶችም ቍጥር አምስት ሺህ ያህል ሆነ። በነገውም አለቆቻቸውና ሽማግሌዎች ጻፎችም ሊቀ ካህናቱ ሐናም ቀያፋም ዮሐንስም እስክንድሮስም የሊቀ ካህናቱም ዘመዶች የነበሩት ሁሉ በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ፤ እነርሱንም በመካከል አቁመው፦ “በምን ኃይል ወይስ በማን ስም እናንተ ይህን አደረጋችሁ?” ብለው ጠየቁአቸው። በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ መንፈስ ቅዱስንም ተሞልቶ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ የሕዝብ አለቆችና ሽማግሌዎች፥ እኛ ዛሬ ለድውዩ ሰው ስለ ተደረገው መልካም ሥራ ይህ በምን እንደዳነ ብንመረመር፥ እናንተ በሰቀላችሁት እግዚአብሔርም ከሙታን ባስነሣው በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይህ ደኅና ሆኖ በፊታችሁ እንደ ቆመ፥ ለእናንተ ለሁላችሁ ለእስራኤልም ሕዝብ ሁሉ የታወቀ ይሁን። እናንተ ግንበኞች የናቃችሁት፥ የማዕዘን ራስ የሆነው ይህ ድንጋይ ነው። መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።” ጴጥሮስና ዮሐንስም በግልጥ እንደ ተናገሩ ባዩ ጊዜ፥ መጽሐፍን የማያውቁና ያልተማሩ ሰዎች እንደ ሆኑ አስተውለው አደነቁ፥ ከኢየሱስም ጋር እንደ ነበሩ አወቁአቸው፤ የተፈወሰውንም ሰው ከእነርሱ ጋር ቆሞ ሲያዩ የሚመልሱትን አጡ። ከሸንጎም ወደ ውጭ ይወጡ ዘንድ አዝዘው፦ “በእነዚህ ሰዎች ምን እንሥራ? የታወቀ ምልክት በእነርሱ እጅ እንደ ተደረገ በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ሁሉ ተገልጦአልና፥ እንሸሽገው ዘንድ አንችልም፤ ነገር ግን በሕዝቡ ዘንድ አብዝቶ እንዳይስፋፋ፥ ከእንግዲህ ወዲህ ለማንም ሰው በዚህ ስም እንዳይናገሩ እየዛትን እንዘዛቸው” ብለው እርስ በርሳቸው ተማከሩ። ጠርተውም በኢየሱስ ስም ፈጽመው እንዳይናገሩና እንዳያስተምሩ አዘዙአቸው። ጴጥሮስና ዮሐንስ ግን መልሰው፦ “እግዚአብሔርን ከመስማት ይልቅ እናንተን እንሰማ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት የሚገባ እንደ ሆነ ቍረጡ፤ እኛስ ያየነውንና የሰማነውን ከመናገር ዝም ማለት አንችልም” አሉአቸው። እነርሱም እንደ ምን እንደሚቀጡ ምክንያት ስላላገኙባቸው፥ እንደ ገና ዝተው ከሕዝቡ የተነሣ ፈቱአቸው፤ ሰዎች ሁሉ ስለ ሆነው ነገር እግዚአብሔርን ያከብሩ ነበርና። ይህ የመፈወስ ምልክት የተደረገለት ሰው ከአርባ ዓመት ይበልጠው ነበርና። ተፈትተውም ወደ ወገኖቻቸው መጡና የካህናት አለቆችና ሽማግሌዎች ያሉአቸውን ሁሉ ነገሩአቸው። እነርሱም በሰሙ ጊዜ በአንድ ልብ ሆነው ውፍደ እፍዚአብሔር ድምፃቸውን ከፍ አደረጉ እንዲህም አሉ፦ ጌታ ሆይ፥ አንተ ሰማዩንና ምድሩን ባሕሩንም በእነርሱም የሚኖረውን ሁሉ የፈጠርህ፥ በመንፈስ ቅዱስም በብላቴናህ በአባታችን በዳዊት አፍ፦ አሕዛብ ለምን አጕረመረሙ? ሕዝቡስ ከንቱን ነገር ለምን አሰቡ? የምድር ነገሥታት ተነሡ አለቆችም በጌታና በተቀባው ላይ አብረው ተከማቹ ብለህ የተናገር አምላክ ነህ። በቀባኸው በቅዱሱ ብላቴናህ በኢየሱስ ላይ ሄሮድስና ጴንጤናዊው ጲላጦስ ከአሕዛብና ከእስራኤል ሕዝብ ጋር፥ እጅህና አሳብህ እንዲሆን አስቀድመው የወሰኑትን ሁሉ ሊፈጽሙ፥ በዚች ከተማ በእውነት ተሰበሰቡ። አሁንም፥ ጌታ ሆይ፥ ወደ ዛቻቸው ተመልከት፤ ለመፈወስም እጅህን ስትዘረጋ በቅዱስ ብላቴናህም በኢየሱስ ስም ምልክትና ድንቅ ሲደረግ፥ ባሪያዎችህ በፍጹም ግልጥነት ቃልህን እንዲናገሩ ስጣቸው።” ከጸለዩም በኋላ ተሰብስበው የነበሩበት ስፍራ ተናወጠ፥ በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፥ የእግዚአብሔርንም ቃል በግልጥ ተናገሩ። ያመኑትም ሕዝብ አንድ ልብ አንዲትም ነፍስ ነበሩአቸው፥ ገንዘባቸውም ሁሉ በአንድነት ነበረ እንጂ ካለው አንድ ነገር ስንኳ የራሱ እንደ ሆነ ማንም አልተናገረም። ሐዋርያትም የጌታን የኢየሱስ ክርስቶስን ትንሣኤ በታላቅ ኃይል ይመሰክሩ ነበር፤ በሁሉም ላይ ታላቅ ጸጋ ነበረባቸው። በመካከላቸው አንድ ስንኳ ችግረኛ አልነበረምና፤ መሬት ወይም ቤት ያላቸው ሁሉ እየሸጡ የተሸጠውን ዋጋ ያመጡ ነበርና፥ በሐዋርያትም እግር አጠገብ ያኖሩ ነበር፤ ማናቸውም እንደሚፈልግ መጠን ለእያንዳንዱ ያካፍሉት ነበር። ትውልዱም የቆጵሮስ ሰው የነበረ አንድ ሌዋዊ ዮሴፍ የሚሉት ነበረ፥ እርሱም በሐዋርያት በርናባስ ተባለ ትርጓሜውም የመጽናናት ልጅ ነው፤ እርሻም ነበረውና ሽጦ ገንዘቡን አምጥቶ ከሐዋርያት እግር አጠገብ አኖረው።

ሐዋርያት ሥራ 4:1-37 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ጴጥሮስና ዮሐንስ ለሕዝቡ ሲናገሩ ሳሉ ካህናትና የቤተ መቅደሱ የዘበኞች አለቃ እንዲሁም ሰዱቃውያን ወደ እነርሱ መጡና ሁለቱ ሐዋርያት የኢየሱስን ከሞት መነሣት ለሕዝቡ በማስተማራቸውና በዚህም የሙታን ትንሣኤ መኖሩን በማስረዳታቸው ተቈጡ። ስለዚህ ያዙአቸውና ጊዜው መሽቶ ስለ ነበረ እስከ ማግስቱ ድረስ በወህኒ ቤት እንዲቈዩ አደረጉአቸው። ነገር ግን ቃላቸውን ከሰሙት ሰዎች ብዙዎቹ አመኑ፤ የአመኑትም ሰዎች ቊጥር ወደ አምስት ሺህ ከፍ አለ። በማግስቱ የአይሁድ አለቆችና ሽማግሌዎች፥ የሕግ መምህራንም በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ። ከተሰበሰቡት ሰዎች መካከል የካህናት አለቃው ሐናና ቀያፋ፥ ዮሐንስና እስክንድሮስ፥ የካህናት አለቃው ቤተሰቦች ሁሉ ይገኙባቸዋል፤ እነርሱም ሁለቱን ሐዋርያት በመካከላቸው አቁመው፥ “ይህን ያደረጋችኹት በምን ኀይል ወይም በማን ስም ነው?” ሲሉ ጠየቁአቸው። በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እናንተ የሕዝብ አለቆችና ሽማግሌዎች ሆይ! እኛ ዛሬ የምንጠየቀው ለአንድ ሽባ ሰው ስለ ተደረገለት መልካም ሥራና በምን ዐይነት ሁኔታ እንደ ዳነ ነው። ይህ ሰው ድኖ በፊታችሁ የቆመው እናንተ በሰቀላችሁትና እግዚአብሔር ግን ከሞት ባስነሣው በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንደ ሆነ ለእናንተ ለሁላችሁና ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ የታወቀ ይሁን። እናንተ ግንበኞች ንቃችሁ የጣላችሁትም ድንጋይ እርሱ ነው፤ ነገር ግን እርሱ የማእዘን ራስ ሆነ። ስለዚህ መዳን ከእርሱ በቀር በሌላ በማንም የለም፤ እኛ ልንድንበት የሚገባን እግዚአብሔር ለሰዎች የሰጠው ስም ከእርሱ በቀር በመላው ዓለም ማንም የለም።” ጴጥሮስና ዮሐንስ በድፍረት መናገራቸውን የሸንጎ አባሎች ባዩ ጊዜ ያልተማሩ ተራ ሰዎች መሆናቸውን ያውቁ ስለ ነበረ ተደነቁ፤ ከኢየሱስ ጋር እንደ ነበሩም ዐወቁ፤ የዳነውንም ሰው ከእነርሱ ጋር ቆሞ በማየታቸው በእነርሱ ላይ የሚሉትን አጡ። ስለዚህ ከሸንጎው ወዲያ ገለል አደረጉአቸውና በቈይታ እንዲህ ሲሉ ተማከሩ። “እንግዲህ በእነዚህ ሰዎች ላይ ምን እናድርግ? ይህ ታላቅ ተአምር በእነርሱ እጅ መደረጉ በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሁሉ ታውቆአል፤ ስለዚህ ልንክደው አንችልም። ነገር ግን በሕዝቡ ዘንድ እየተስፋፋ እንዳይሄድ ከእንግዲህ ወዲህ የኢየሱስን ስም በመጥራት ለማንም እንዳይናገሩ፥ እናስጠንቅቃቸው።” ከዚህ በኋላ ጠሩአቸውና የኢየሱስን ስም በመጥራት ከቶ እንዳይናገሩ ወይም እንዳያስተምሩ በጥብቅ አዘዙአቸው። ጴጥሮስና ዮሐንስ ግን እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፦ “ለእግዚአብሔር ከመታዘዝ ይልቅ ለእናንተ መታዘዝ በእግዚአብሔር ፊት ተገቢ ነውን? እስቲ እናንተ ራሳችሁ ፍረዱ። እኛስ ያየነውንና የሰማነውን ከመናገር አንቈጠብም።” የሕዝብ አለቆችና የሸንጎው አባሎች ጴጥሮስንና ዮሐንስን የሚያስቀጣ ምንም ምክንያት ባለማግኘታቸው፥ ሕዝቡንም ስለ ፈሩ እንደገና አስጠንቅቀው ለቀቁአቸው፤ ይህንንም ያደረጉት ሕዝቡ በሆነው ነገር እግዚአብሔርን ያመሰግን ስለ ነበር ነው። በዚህ ተአምር የተፈወሰው ያ ሰው ዕድሜው ከአርባ ዓመት በላይ ነበር። ጴጥሮስና ዮሐንስ ተለቀው ወደ ጓደኞቻቸው በተመለሱ ጊዜ የካህናት አለቆችና የአይሁድ ሽማግሌዎች ያሉአቸውን ሁሉ ነገሩአቸው። እነርሱም ይህን በሰሙ ጊዜ ድምፃቸውን በአንድነት ከፍ አድርገው ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ሲሉ ጸለዩ፤ “ሰማይን፥ ምድርን፥ ባሕርን፥ በውስጣቸው የሚኖረውን ሁሉ የፈጠርክ ልዑል እግዚአብሔር ሆይ! በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት በአገልጋይህ በአባታችን በዳዊት አፍ እንዲህ ብለህ የተናገርክ አንተ ነህ፤ ‘አሕዛብ ስለምን ተቈጡ? ሕዝቦችስ ስለምን በከንቱ ዶለቱ? የምድር ነገሥታት ተሰልፈው፥ ገዢዎችም በአንድነት ተሰብስበው፥ በጌታና በመሲሑ ላይ ተነሡ።’ “በእርግጥም ሄሮድስና ጴንጤናዊ ጲላጦስ ከአሕዛብና ከእስራኤል ሕዝብ ጋር በዚህች ከተማ ተሰብስበው መሲሕ ባደረግኸው በቅዱሱ አገልጋይህ በኢየሱስ ላይ ተነሡ፤ እንዲህም የሆነው አንተ አስቀድመህ በገዛ ኀይልህና በገዛ ፈቃድህ ያቀድከውን ለመፈጸም ነው፤ አሁንም ጌታ ሆይ፥ ዛቻቸውን ተመልከት፤ አገልጋዮችህ ቃልህን ያለ ፍርሀት በድፍረት እንዲናገሩ አድርግ፤ በቅዱሱ ልጅህ በኢየሱስ ስም በሽተኞች እንዲድኑና ተአምራትም፥ ድንቅ ነገሮችም እንዲደረጉ እጅህን ዘርጋ።” ጸሎት ከጨረሱ በኋላ ተሰብስበው የነበሩበት ስፍራ ተናወጠ፤ ሁሉም በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ፤ የእግዚአብሔርንም ቃል ያለ ፍርሀት በድፍረት ተናገሩ። አማኞች ሁሉ አንድ ልብና አንድ አሳብ ነበራቸው፤ ማንም ሰው “ይህ የእኔ ነው” የሚለው ነገር አልነበረውም፤ በመካከላቸውም ሁሉ ነገር የጋራ ነበር፤ ሐዋርያትም የጌታን የኢየሱስን ትንሣኤ በታላቅ ኀይል ይመሰክሩ ነበር፤ በሁሉም ላይ ታላቅ የእግዚአብሔር ጸጋ ነበረ። መሬት ወይም ቤት ያላቸው ሁሉ እየሸጡ ገንዘቡን ያመጡ ስለ ነበር በመካከላቸው አንድም ችግረኛ አልነበረም። ገንዘቡንም አምጥተው ለሐዋርያት ያስረክቡ ነበር። ለእያንዳንዱም እንደ አስፈላጊነቱ ይከፋፈል ነበር። የቆጵሮስ ተወላጅ የሆነ፥ ዮሴፍ የሚባል አንድ ሌዋዊ ነበረ፤ ሐዋርያት “በርናባስ” እያሉ ይጠሩት ነበር፤ ትርጓሜው “የመጽናናት ልጅ” ማለት ነው። እርሱም መሬቱን ሸጠና ገንዘቡን አምጥቶ ለሐዋርያት አስረከበ።

ሐዋርያት ሥራ 4:1-37 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ለሕዝቡም ሲናገሩ የካህናት አለቆችና የመቅደስ አዛዥ ሰዱቃውያንም፥ ሕዝቡን ስለ አስተማሩና በኢየሱስ የሙታንን ትንሣኤ ስለ ሰበኩ እጅግም ተቆጥተው ወደ እነርሱ ቀረቡ፤ እጃቸውንም ጭነውባቸው አሁን መሽቶ ነበርና እስከ ማግሥቱ ድረስ በወኅኒ አኖሩአቸው። ነገር ግን ቃሉን ከሰሙት ብዙዎች አመኑ፥ የወንዶችም ቍጥር አምስት ሺህ ያህል ሆነ። በነገውም አለቆቻቸውና ሽማግሌዎች ጻፎችም ሊቀ ካህናቱ ሐናም ቀያፋም ዮሐንስም እስክንድሮስም የሊቀ ካህናቱም ዘመዶች የነበሩት ሁሉ በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ፤ እነርሱንም በመካከል አቁመው “በምን ኃይል ወይስ በማን ስም እናንተ ይህን አደረጋችሁ?” ብለው ጠየቁአቸው። በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ መንፈስ ቅዱስንም ተሞልቶ እንዲህ አላቸው “እናንተ የሕዝብ አለቆችና ሽማግሌዎች፥ እኛ ዛሬ ለድውዩ ሰው ስለተደረገው መልካም ሥራ ይህ በምን እንደ ዳነ ብንመረመር፥ እናንተ በሰቀላችሁት እግዚአብሔርም ከሙታን ባስነሣው በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይህ ደኅና ሆኖ በፊታችሁ እንደ ቆመ፥ ለእናንተ ለሁላችሁ ለእስራኤልም ሕዝብ ሁሉ የታወቀ ይሁን። ‘እናንተ ግንበኞች የናቃችሁት፥ የማዕዘን ራስ የሆነው ይህ ድንጋይ ነው።’ መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።” ጴጥሮስና ዮሐንስም በግልጥ እንደ ተናገሩ ባዩ ጊዜ፥ መጽሐፍን የማያውቁና ያልተማሩ ሰዎች እንደ ሆኑ አስተውለው አደነቁ፤ ከኢየሱስም ጋር እንደ ነበሩ አወቁአቸው፤ የተፈወሰውንም ሰው ከእነርሱ ጋር ቆሞ ሲያዩ የሚመልሱትን አጡ። ከሸንጎም ወደ ውጭ ይወጡ ዘንድ አዝዘው “በእነዚህ ሰዎች ምን እንሥራ? የታወቀ ምልክት በእነርሱ እጅ እንደ ተደረገበኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ሁሉ ተገልጦአልና፤ እንሸሽገው ዘንድ አንችልም፤ ነገር ግን በሕዝቡ ዘንድ አብዝቶ እንዳይስፋፋ፥ ከእንግዲህ ወዲህ ለማንም ሰው በዚህ ስም እንዳይናገሩ እየዛትን እንዘዛቸው፤” ብለው እርስ በርሳቸው ተማከሩ። ጠርተውም በኢየሱስ ስም ፈጽመው እንዳይናገሩና እንዳያስተምሩ አዘዙአቸው። ጴጥሮስና ዮሐንስ ግን መልሰው “እግዚአብሔርን ከመስማት ይልቅ እናንተን እንሰማ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት የሚገባ እንደሆነ ቁረጡ፤ እኛስ ያየነውንና የሰማነውን ከመናገር ዝም ማለት አንችልም፤” አሉአቸው። እነርሱም እንደምን እንደሚቀጡ ምክንያት ስላላገኙባቸው፥ እንደገና ዝተው ከሕዝቡ የተነሣ ፈቱአቸው፤ ሰዎች ሁሉ ስለ ሆነው ነገር እግዚአብሔርን ያከብሩ ነበርና። ይህ የመፈወስ ምልክት የተደረገለት ሰው ከአርባ ዓመት ይበልጠው ነበርና። ተፈትተውም ወደ ወገኖቻቸው መጡና የካህናት አለቆችና ሽማግሌዎች ያሉአቸውን ሁሉ ነገሩአቸው። እነርሱም በሰሙ ጊዜ በአንድ ልብ ሆነው ውፍደ እፍዚአብሔር ድምፃቸውን ከፍ አደረጉ፤ እንዲህም አሉ “ጌታ ሆይ! አንተ ሰማዩንና ምድሩን ባሕሩንም በእነርሱም የሚኖረውን ሁሉ የፈጠርህ፥ በመንፈስ ቅዱስም በብላቴናህ በአባታችን በዳዊት አፍ ‘አሕዛብ ለምን አጉረመረሙ? ሕዝቡስ ከንቱን ነገር ለምን አሰቡ? የምድር ነገሥታት ተነሡ፤ አለቆችም በጌታና በተቀባው ላይ አብረው ተከማቹ፤’ ብለህ የተናገር አምላክ ነህ። በቀባኸው በቅዱሱ ብላቴናህ በኢየሱስ ላይ ሄሮድስና ጴንጤናዊው ጲላጦስ ከአሕዛብና ከእስራኤል ሕዝብ ጋር፥ እጅህና አሳብህ እንዲሆን አስቀድመው የወሰኑትን ሁሉ ሊፈጽሙ፥ በዚች ከተማ በእውነት ተሰበሰቡ። አሁንም፥ ጌታ ሆይ! ወደ ዛቻቸው ተመልከት፤ ለመፈወስም እጅህን ስትዘረጋ በቅዱስ ብላቴናህም በኢየሱስ ስም ምልክትና ድንቅ ሲደረግ፥ ባርያዎችህ በፍጹም ግልጥነት ቃልህን እንዲናገሩ ስጣቸው።” ከጸለዩም በኋላ ተሰብስበው የነበሩበት ስፍራ ተናወጠ፤ በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፤ የእግዚአብሔርንም ቃል በግልጥ ተናገሩ። ያመኑትም ሕዝብ አንድ ልብ አንዲትም ነፍስ ነበሩአቸው፤ ገንዘባቸውም ሁሉ በአንድነት ነበረ እንጂ ካለው አንድ ነገር ስንኳ የራሱ እንደሆነ ማንም አልተናገረም። ሐዋርያትም የጌታን የኢየሱስ ክርስቶስን ትንሣኤ በታላቅ ኃይል ይመሰክሩ ነበር፤ በሁሉም ላይ ታላቅ ጸጋ ነበረባቸው። በመካከላቸው አንድ ስንኳ ችግረኛ አልነበረምና፤ መሬት ወይም ቤት ያላቸው ሁሉ እየሸጡ የተሸጠውን ዋጋ ያመጡ ነበርና፤ በሐዋርያትም እግር አጠገብ ያኖሩ ነበር፤ ማናቸውም እንደሚፈልግ መጠን ለእያንዳንዱ ያካፍሉት ነበር። ትውልዱም የቆጵሮስ ሰው የነበረ አንድ ዮሴፍ የሚሉት ሌዋዊ ነበረ፤ እርሱም በሐዋርያት በርናባስ ተባለ፤ ትርጓሜውም የመጽናናት ልጅ ነው፤ እርሻም ነበረውና ሽጦ ገንዘቡን አምጥቶ ከሐዋርያት እግር አጠገብ አኖረው።