ሐዋርያት ሥራ 3:14 - Compare All Versions

ሐዋርያት ሥራ 3:14 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

እና​ንተ ግን ቅዱ​ሱ​ንና ጻድ​ቁን ካዳ​ች​ሁት፤ ነፍሰ ገዳ​ዩን ሰውም እን​ዲ​ያ​ድ​ን​ላ​ችሁ ለመ​ና​ችሁ።

ሐዋርያት ሥራ 3:14 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ቅዱሱንና ጻድቁን ክዳችሁ ነፍሰ ገዳዩ እንዲፈታላችሁ ለመናችሁ፤

ሐዋርያት ሥራ 3:14 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

እናንተ ግን ቅዱሱን ጻድቁንም ክዳችሁ ነፍሰ ገዳዩን ሰው ይሰጣችሁ ዘንድ ለመናችሁ፥

ሐዋርያት ሥራ 3:14 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

እናንተ ቅዱሱንና ጻድቁን ‘አንፈልገውም’ ብላችሁ አንድ ነፍሰ ገዳይ እንዲፈታላችሁ ለመናችሁ።

ሐዋርያት ሥራ 3:14 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

እናንተ ግን ቅዱሱን ጻድቁንም ክዳችሁ ነፍሰ ገዳዩን ሰው ይሰጣችሁ ዘንድ ለመናችሁ፤