ሐዋርያት ሥራ 3:1-12

ሐዋርያት ሥራ 3:1-12 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ጴጥ​ሮ​ስና ዮሐ​ን​ስም በዘ​ጠኝ ሰዓት ለጸ​ሎት በአ​ን​ድ​ነት ወደ ቤተ መቅ​ደስ ወጡ። ከእ​ናቱ ማኅ​ፀ​ንም ጀምሮ እግሩ ሽባ ሆኖ የተ​ወ​ለደ አንድ ሰው ነበር፤ ወደ መቅ​ደ​ስም ከሚ​ገ​ቡት ምጽ​ዋት ይለ​ምን ዘንድ ሁል​ጊዜ እየ​ተ​ሸ​ከሙ መል​ካም በሚ​ል​ዋት በመ​ቅ​ደስ ደጃፍ ያስ​ቀ​ም​ጡት ነበር። ጴጥ​ሮ​ስ​ንና ዮሐ​ን​ስ​ንም ወደ መቅ​ደስ ሲገቡ አይቶ ምጽ​ዋት ይሰ​ጡት ዘንድ ለመ​ና​ቸው። ጴጥ​ሮ​ስም ከዮ​ሐ​ንስ ጋር ትኩር ብሎ ተመ​ለ​ከ​ተው፥ “ወደ እኛ ተመ​ል​ከት” አለው፤ ወደ እነ​ር​ሱም ተመ​ለ​ከተ፤ ምጽ​ዋት እን​ደ​ሚ​ሰ​ጡ​ትም ተስፋ አድ​ርጎ ነበር። ጴጥ​ሮ​ስም፥ “ወር​ቅና ብር የለ​ኝም፤ ያለ​ኝን ግን እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ፤ እነሆ፥ በና​ዝ​ሬቱ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም ተነ​ሥ​ተህ ሂድ” አለው። በቀኝ እጁም ይዞ አስ​ነ​ሣው፤ ያን​ጊ​ዜም እግ​ሩና ቍር​ጭ​ም​ጭ​ምቱ ጸና። ዘሎም ቆመ፤ እየ​ሮ​ጠና እየ​ተ​ራ​መ​ደም ሄደ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም እያ​መ​ሰ​ገነ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ወደ ቤተ መቅ​ደስ ገባ። ሕዝ​ቡም ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እያ​መ​ሰ​ገነ ሲመ​ላ​ለስ አዩት። እር​ሱም መል​ካም በም​ት​ባ​ለው በመ​ቅ​ደስ ደጃፍ ተቀ​ምጦ ምጽ​ዋት ይለ​ምን የነ​በ​ረው እንደ ሆነ ዐወ​ቁት፤ በእ​ር​ሱም ከሆ​ነው የተ​ነሣ መገ​ረ​ምና መደ​ነቅ ሞላ​ባ​ቸው። ጴጥ​ሮ​ስና ዮሐ​ን​ስም ይዘ​ውት ወደ መቅ​ደስ ሲገቡ ሕዝቡ ሁሉ ደን​ግ​ጠው ወደ ሰሎ​ሞን መመ​ላ​ለሻ ወደ እነ​ርሱ ሮጡ። ጴጥ​ሮ​ስም ሕዝ​ቡን ባያ​ቸው ጊዜ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንት የእ​ስ​ራ​ኤል ሰዎች ሆይ፥ ይህን ለምን ታደ​ን​ቃ​ላ​ችሁ? እኛ​ንስ በኀ​ይ​ላ​ች​ንና በጽ​ድ​ቃ​ችን ይህን ሰው በእ​ግሩ እን​ዲ​ሄድ እን​ዳ​ደ​ረ​ግ​ነው አስ​መ​ስ​ላ​ችሁ ለምን ታዩ​ና​ላ​ችሁ?

ሐዋርያት ሥራ 3:1-12 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

አንድ ቀን ጴጥሮስና ዮሐንስ በጸሎት ጊዜ፣ ይኸውም ከቀኑ በዘጠኝ ሰዓት ወደ ቤተ መቅደስ ይወጡ ነበር። ወደ ቤተ መቅደስ ከሚገቡት ሰዎች ምጽዋት እንዲለምን፣ ሰዎች በየዕለቱ ተሸክመው “ውብ” በተባለው የቤተ መቅደስ መግቢያ በር ላይ የሚያስቀምጡት አንድ ከተወለደ ጀምሮ ሽባ የሆነ ሰው ነበረ፤ እርሱም ጴጥሮስና ዮሐንስ ወደ ቤተ መቅደስ ሲገቡ አይቶ ምጽዋት ለመናቸው። ጴጥሮስም ከዮሐንስ ጋራ ወደ እርሱ ትኵር ብሎ አየውና፣ “እስኪ ወደ እኛ ተመልከት!” አለው። ሰውየውም፣ ከእነርሱ አንድ ነገር ለማግኘት ዐስቦ በትኵረት ተመለከታቸው። ጴጥሮስ ግን፣ “እኔ ብርና ወርቅ የለኝም፤ ነገር ግን ያለኝን እሰጥሃለሁ፤ በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሥተህ በእግርህ ተመላለስ” አለው፤ ቀኝ እጁንም ይዞ አስነሣው፤ ወዲያውም እግሩና ቍርጭምጭሚቱ በረታ፤ ዘልሎም ቀጥ ብሎ ቆመ፤ መራመድም ጀመረ፤ ወዲህ ወዲያ እየሄደና እየዘለለም እግዚአብሔርንም እያመሰገነ ከእነርሱ ጋራ ወደ ቤተ መቅደሱ አደባባይ ገባ። ሕዝቡም ሁሉ እየተራመደና እግዚአብሔርን እያመሰገነ ሲመላለስ ባዩት ጊዜ፣ ይህ ሰው ቀደም ሲል “ውብ” በተባለው የቤተ መቅደስ መግቢያ በር ላይ ተቀምጦ ምጽዋት ይለምን የነበረው እርሱ መሆኑን ዐወቁ፤ በርሱ ላይ ከተፈጸመውም ነገር የተነሣ በመደነቅና በመገረም ተሞሉ። የተፈወሰውም ሰው ከጴጥሮስና ዮሐንስ ጋራ ጥብቅ ብሎ ዐብሯቸው ሳለ፣ ሕዝቡ ሁሉ በመገረም እነርሱ ወደ ነበሩበት “የሰሎሞን መመላለሻ” ወደተባለው ስፍራ እየሮጡ መጡ። ጴጥሮስም ይህን ባየ ጊዜ እንዲህ አላቸው፤ “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፤ በዚህ ለምን ትደነቃላችሁ? ደግሞም በእኛ ኀይል ወይም በእኛ ጽድቅ ይህ ሰው ድኖ እንዲመላለስ እንዳደረግነው በመቍጠር፣ ለምን ወደ እኛ አትኵራችሁ ትመለከታላችሁ?

ሐዋርያት ሥራ 3:1-12 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ጴጥሮስና ዮሐንስም በጸሎት ጊዜ በዘጠኝ ሰዓት ወደ መቅደስ ይወጡ ነበር። ወደ መቅደስም ከሚገቡት ምጽዋት ይለምን ዘንድ፥ ሰዎች ተሸክመው መልካም በሚሉአት በመቅደስ ደጅ በየቀኑ ያስቀምጡት የነበሩ ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ አንካሳ የሆነ አንድ ሰው ነበረ። እርሱም ጴጥሮስና ዮሐንስ ወደ መቅደስ ሊገቡ እንዳላቸው ባየ ጊዜ፥ ምጽዋትን ለመናቸው። ጴጥሮስም ከዮሐንስ ጋር ትኵር ብሎ ወደ እርሱ ተመልክቶ፦ “ወደ እኛ ተመልከት” አለው። እርሱም አንድ ነገር ከእነርሱ እንዲቀበል ሲጠብቅ ወደ እነርሱ ተመለከተ። ጴጥሮስ ግን፦ “ብርና ወርቅ የለኝም፤ ይህን ያለኝን ግን እሰጥሃለሁ፤ በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሣና ተመላለስ” አለው። በቀኝ እጁም ይዞ አስነሣው፤ በዚያን ጊዜም እግሩና ቍርጭምጭምቱ ጸና፥ ወደ ላይ ዘሎም ቆመ፥ ይመላለስም ጀመር፤ እየተመላለሰም እየዘለለም እግዚአብሔርንም እያመሰገነ ከእነርሱ ጋር ወደ መቅደስ ገባ። ሕዝቡም ሁሉ እግዚአብሔርን እያመሰገነ ሲመላለስ አዩት፤ መልካምም በሚሉአት በመቅደስ ደጅ ስለ ምጽዋት ተቀምጦ የነበረው እርሱ እንደ ሆነ አወቁት፤ በእርሱም ከሆነው የተነሣ መደነቅና መገረም ሞላባቸው። እርሱም ጴጥሮስንና ዮሐንስን ይዞ ሳለ፥ ሕዝቡ ሁሉ እየተደነቁ የሰሎሞን ደጅ መመላለሻ በሚባለው አብረው ወደ እነርሱ ሮጡ። ጴጥሮስም አይቶ ለሕዝቡ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “የእስራኤል ሰዎች ሆይ፥ በዚህ ስለ ምን ትደነቃላችሁ? ወይስ በገዛ ኃይላችን ወይስ እግዚአብሔርን በመፍራታችን ይህ ይመላለስ ዘንድ እንዳደረግነው ስለ ምን ትኵር ብላችሁ ታዩናላችሁ?

ሐዋርያት ሥራ 3:1-12 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

አንድ ቀን ጴጥሮስና ዮሐንስ በጸሎት ጊዜ ከቀኑ በዘጠኝ ሰዓት ወደ ቤተ መቅደስ ወጡ፤ እዚያ “ውብ” እየተባለ የሚጠራ በር ነበር፤ ሲወለድ ጀምሮ ሽባ የሆነውን አንድ ሰው ሰዎች በየቀኑ እያመጡ እዚያ ያስቀምጡት ነበር፤ እርሱ እዚያ ተቀምጦ ወደ ቤተ መቅደስ ከሚገቡት ሰዎች ምጽዋት ይለምን ነበር። ይህ ሰው ጴጥሮስና ዮሐንስ ወደ ቤተ መቅደስ ሲገቡ አይቶ ምጽዋት ለመናቸው። እነርሱም ሰውየውን ትኲር ብለው አዩትና ጴጥሮስ “ወደ እኛ ተመልከት!” አለው። እርሱም ምጽዋት የሚሰጡት መስሎት ትኲር ብሎ አያቸው። ጴጥሮስ ግን “ብርና ወርቅ የለኝም፤ ያለኝን ግን እሰጥሃለሁ፤ በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሥና ተራመድ!” አለው። ቀኝ እጁንም ይዞ አስነሣው፤ ወዲያውኑ እግሩና ቊርጭምጭሚቱ በረታ። ብድግ ብሎም ቆመ፤ እየተራመደም ከእነርሱ ጋር ወደ ቤተ መቅደስ ገባ፤ እየተራመደና እየዘለለም እግዚአብሔርን ያመሰግን ነበር። ሰዎቹም ሁሉ ሲራመድና እግዚአብሔርን ሲያመሰግን አዩት። “ውብ በር” እየተባለ በሚጠራው በቤተ መቅደሱ በር አጠገብ ተቀምጦ ምጽዋት ይለምን የነበረው እርሱ መሆኑን ዐወቁ፤ በእርሱ ላይም በተደረገው ነገር ይገረሙና ይደነቁ ጀመር። የዳነው ሰው ከጴጥሮስና ከዮሐንስ አልለይም በማለት ይዞአቸው ሳለ ሰዎቹ ተደንቀው “የሰሎሞን መመላለሻ” ወደሚባለው ስፍራ ወደ እነርሱ ሮጠው ሄዱ፤ ጴጥሮስም ሰዎቹን ባየ ጊዜ እንዲህ አላቸው፦ “የእስራኤል ሰዎች ሆይ! በዚህ ነገር ስለምን ትደነቃላችሁ? ስለምንስ ትኲር ብላችሁ ታዩናላችሁ? እኛ በራሳችን ኀይል ወይም በራሳችን መልካም ሥራ ይህን ሰው እንዲራመድ ያደረግነው ይመስላችኋልን?

ሐዋርያት ሥራ 3:1-12 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ጴጥሮስና ዮሐንስም በጸሎት ጊዜ በዘጠኝ ሰዓት ወደ መቅደስ ይወጡ ነበር። ወደ መቅደስም ከሚገቡት ምጽዋት ይለምን ዘንድ፥ ሰዎች ተሸክመው መልካም በሚሉአት በመቅደስ ደጅ በየቀኑ ያስቀምጡት የነበሩ ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ አንካሳ የሆነ አንድ ሰው ነበረ። እርሱም ጴጥሮስና ዮሐንስ ወደ መቅደስ ሊገቡ እንዳላቸው ባየ ጊዜ፥ ምጽዋትን ለመናቸው። ጴጥሮስም ከዮሐንስ ጋር ትኩር ብሎ ወደ እርሱ ተመልክቶ “ወደ እኛ ተመልከት፤” አለው። እርሱም አንድ ነገር ከእነርሱ እንዲቀበል ሲጠብቅ ወደ እነርሱ ተመለከተ። ጴጥሮስ ግን “ብርና ወርቅ የለኝም፤ ይህን ያለኝን ግን እሰጥሃለሁ፤ በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሣና ተመላለስ፤” አለው። በቀኝ እጁም ይዞ አስነሣው፤ በዚያን ጊዜም እግሩና ቁርጭምጭሚቱ ጸና፤ ወደ ላይ ዘሎም ቆመ፤ ይመላለስም ጀመር፤ እየተመላለሰም እየዘለለም እግዚአብሔርንም እያመሰገነ ከእነርሱ ጋር ወደ መቅደስ ገባ። ሕዝቡም ሁሉ እግዚአብሔርን እያመሰገነ ሲመላለስ አዩት፤ “መልካም” በሚሉአትም በመቅደስ ደጅ ስለ ምጽዋት ተቀምጦ የነበረው እርሱ እንደሆነ አወቁት፤ በእርሱም ከሆነው የተነሣ መደነቅና መገረም ሞላባቸው። እርሱም ጴጥሮስንና ዮሐንስን ይዞ ሳለ፥ ሕዝቡ ሁሉ እየተደነቁ የሰሎሞን ደጅ መመላለሻ በሚባለው አብረው ወደ እነርሱ ሮጡ። ጴጥሮስም አይቶ ለሕዝቡ እንዲህ ሲል መለሰ “የእስራኤል ሰዎች ሆይ! በዚህ ስለምን ትደነቃላችሁ? ወይስ በገዛ ኀይላችን ወይስ እግዚአብሔርን በመፍራታችን ይህ ይመላለስ ዘንድ እንዳደረግነው ስለምን ትኩር ብላችሁ ታዩናላችሁ?