ሐዋርያት ሥራ 27:25-26
ሐዋርያት ሥራ 27:25-26 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
አሁንም ወንድሞች ሆይ፥ ደስ ይበላችሁ፤ እንደ ነገረኝ እንደሚሆን በእግዚአብሔር አምናለሁና። ነገር ግን ወደ አንዲት ደሴት እንደርሳለን።”
ሐዋርያት ሥራ 27:25-26 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ስለዚህ፣ እናንተ ሰዎች ሆይ፤ አይዟችሁ እርሱ እንደ ነገረኝ እንደዚያው እንደሚሆን በእግዚአብሔር አምናለሁና። ይሁን እንጂ፣ ወደ አንዲት ደሴት በነፋስ ተወስደን እዚያ መጣላችን አይቀርም።”
ሐዋርያት ሥራ 27:25-26 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ስለዚህ እናንተ ሰዎች ሆይ፥ አይዞአችሁ፤ እንደ ተናገረኝ እንዲሁ እንዲሆን እግዚአብሔርን አምናለሁ። ነገር ግን ወደ አንዲት ደሴት እንድንወድቅ ያስፈልገናል።”