ሐዋርያት ሥራ 20:20-21 - Compare All Versions

ሐዋርያት ሥራ 20:20-21 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

በጉ​ባ​ኤም ሆነ በቤት ስነ​ግ​ራ​ች​ሁና ሳስ​ተ​ም​ራ​ችሁ ከሚ​ጠ​ቅ​ማ​ችሁ ነገር አን​ዳች ስን​ኳን አላ​ስ​ቀ​ረ​ሁ​ባ​ች​ሁም። ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መመ​ለ​ስ​ንና በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ማመ​ንን ለአ​ይ​ሁ​ድና ለአ​ረ​ማ​ው​ያን እየ​መ​ሰ​ከ​ርሁ፤

ሐዋርያት ሥራ 20:20-21 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

በአደባባይም ሆነ ከቤት ቤት በመዘዋወር፣ እናንተን ከማስተማርና ይጠቅማችኋል ብዬ ያሰብሁትን ከመስበክ ወደ ኋላ አላልሁም። በንስሓ ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱና በጌታችን በኢየሱስ እንዲያምኑ፣ ለአይሁድም ለግሪክ ሰዎችም አጥብቄ መስክሬላቸዋለሁ።

ሐዋርያት ሥራ 20:20-21 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ወደ እግዚአብሔር ዘንድ ንስሐንና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ማመንን ለአይሁድና ለግሪክ ሰዎች እየመሰከርሁ በጉባኤም በየቤታችሁም አወራሁላችሁና አስተማርኋችሁ እንጂ፥ ከሚጠቅማችሁ ነገር አንዳች ስንኳ አላስቀረሁባችሁም።

ሐዋርያት ሥራ 20:20-21 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

በአደባባይም ሆነ በየቤታችሁ ሳስተምራችሁ የሚጠቅማችሁን ሁሉ ነገርኳችሁ እንጂ፥ ምንም ነገር አላስቀረሁባችሁም። አይሁድም ሆኑ አሕዛብ ንስሓ ገብተው ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እንዲያምኑ አስጠነቀቅኋቸው።

ሐዋርያት ሥራ 20:20-21 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

በአደባባይም ሆነ በየቤታችሁ ሳስተምራችሁ የሚጠቅማችሁን ሁሉ ነገርኳችሁ እንጂ፥ ምንም ነገር አላስቀረሁባችሁም። አይሁድም ሆኑ አሕዛብ ንስሓ ገብተው ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እንዲያምኑ አስጠነቀቅኋቸው።