ሐዋርያት ሥራ 2:44-45
ሐዋርያት ሥራ 2:44-45 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ያመኑትም ሁሉ በአንድነት ይኖሩ ነበር፤ ገንዘባቸውም ሁሉ በአንድነት ነበር። መሬታቸውንና ጥሪታቸውንም እየሸጡ ለእያንዳንዱ እንደሚያሻው ይሰጡ ነበር።
ሐዋርያት ሥራ 2:44-45 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ያመኑት ሁሉ በአንድነት ነበሩ፤ ያላቸውንም ሁሉ የጋራ አደረጉ። ሀብታቸውንና ንብረታቸውንም እየሸጡ ለእያንዳንዱ ሰው የሚያስፈልገውን ያህል ይሰጡት ነበር።
ሐዋርያት ሥራ 2:44-45 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ያመኑትም ሁሉ አብረው ነበሩ፤ ያላቸውንም ሁሉ አንድነት አደረጉ። መሬታቸውንና ጥሪታቸውንም እየሸጡ፥ ማንኛውም እንደሚፈልግ ለሁሉ ያካፍሉት ነበር።