ሐዋርያት ሥራ 2:38-40 - Compare All Versions

ሐዋርያት ሥራ 2:38-40 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ጴጥ​ሮ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ንስሓ ግቡ፤ ሁላ​ች​ሁም በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም ተጠ​መቁ፤ ኀጢ​አ​ታ​ች​ሁም ይሰ​ረ​ይ​ላ​ች​ኋል፤ የመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስ​ንም ጸጋ ትቀ​በ​ላ​ላ​ችሁ። ተስ​ፋዉ ለእ​ና​ን​ተና ለል​ጆ​ቻ​ችሁ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ች​ንም ለሚ​ጠ​ራ​ቸው ርቀው ለነ​በሩ ሁሉ ነውና።” ሌላም ብዙ ነገር ነገ​ራ​ቸው፤ “ከዚህ ከክፉ ዓለ​ምም ነፍ​ሳ​ች​ሁን አድኑ” ብሎ መከ​ራ​ቸው።

ሐዋርያት ሥራ 2:38-40 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

ጴጥሮስም እንዲህ አላቸው፤ “ንስሓ ግቡ፤ ኀጢአታችሁም እንዲሰረይላችሁ፣ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ። የተስፋው ቃል ለእናንተና ለልጆቻችሁ እንዲሁም ጌታ አምላካችን ወደ ራሱ ለሚጠራቸው፣ በሩቅ ላሉትም ሁሉ ነውና።” በሌላ ብዙ ቃል እየመሰከረላቸው፣ “ከዚህ ጠማማ ትውልድ ራሳችሁን አድኑ” በማለት አስጠነቀቃቸው።

ሐዋርያት ሥራ 2:38-40 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

ጴጥሮስም፦ “ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ። የተስፋው ቃል ለእናንተና ለልጆቻችሁ ጌታ አምላካችንም ወደ እርሱ ለሚጠራቸው በሩቅ ላሉ ሁሉ ነውና” አላቸው። በብዙ ሌላ ቃልም መሰከረና፦ “ከዚህ ጠማማ ትውልድ ዳኑ” ብሎ መከራቸው።

ሐዋርያት ሥራ 2:38-40 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ጴጥሮስም እንዲህ አላቸው፤ “ንስሓ ግቡ፤ ኃጢአታችሁም ይቅር እንዲባልላችሁ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የእግዚአብሔር ስጦታ የሆነውን መንፈስ ቅዱስንም ትቀበላላችሁ፤ የተስፋው ቃል ለእናንተና ለልጆቻችሁ፥ ጌታ አምላካችን ወደ እርሱ ለሚጠራቸው፥ በሩቅ ላሉትም ሁሉ ነው።” በሌላም በብዙ ቃል እየመሰከረ፥ “በዚህ ጠማማ ትውልድ ላይ ከሚመጣው ቅጣት ራሳችሁን አድኑ!” በማለት መከራቸው።

ሐዋርያት ሥራ 2:38-40 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

ጴጥሮስም “ንስሐ ግቡ፤ ኀጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ። የተስፋው ቃል ለእናንተና ለልጆቻችሁ ጌታ አምላካችንም ወደ እርሱ ለሚጠራቸው በሩቅ ላሉ ሁሉ ነውና፤” አላቸው። በብዙ ሌላ ቃልም መሰከረና “ከዚህ ጠማማ ትውልድ ዳኑ፤” ብሎ መከራቸው።