ሐዋርያት ሥራ 17:27
ሐዋርያት ሥራ 17:27 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ይህንንም ያደረገው ሰዎች ጌታን እንዲፈልጉና በመመራመርም ፈልገው እርሱን ማግኘት እንዲችሉ ነው፤ ሆኖም እርሱ ከእኛ ከእያንዳንዳችን ሩቅ ነው ማለት አይደለም።
ሐዋርያት ሥራ 17:27 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ምናልባት ያገኙት እንደ ሆነ እግዚአብሔርን ይፈልጉት ዘንድ፤ ነገር ግን ከሁላችን የራቀ አይደለም።
ሐዋርያት ሥራ 17:27 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ይኸውም ሰዎች እግዚአብሔርን ፈልገው ተመራምረው ምናልባት ያገኙት እንደ ሆነ ብሎ ነው፤ ይህም ቢሆን እርሱ ከእያንዳንዳችን የራቀ ሆኖ አይደለም፤
ሐዋርያት ሥራ 17:26-27 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ምናልባትም እየመረመሩ ያገኙት እንደ ሆነ፥ እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩ የሰውን ወገኖች ሁሉ ከአንድ ፈጠረ፥ የተወሰኑትንም ዘመኖችና ለሚኖሩበት ስፍራ ዳርቻ መደበላቸው። ቢሆንም ከእያንዳንዳችን የራቀ አይደለም።