ሐዋርያት ሥራ 16:22-23
ሐዋርያት ሥራ 16:22-23 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ሕዝቡም ተነሡባቸው፤ ገዢዎቹም ልብሳቸውን ገፍፈው በበትር ይመቱአቸው ዘንድ አዘዙ። በብዙም ደብድበው አሰሩአቸው፤ የወህኒ ቤቱን ዘበኛም አጽንቶ እንዲጠብቃቸው አዘዙት።
ሐዋርያት ሥራ 16:22-23 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ሕዝቡም ተባብረው በጳውሎስና በሲላስ ላይ ተነሡባቸው፤ ገዦቹም ልብሳቸው ተገፍፎ በበትር እንዲደበደቡ አዘዙ። ክፉኛ ከተደበደቡ በኋላም ወደ ወህኒ ቤት አስገቧቸው፤ የወህኒ ቤት ጠባቂውም ተጠንቅቆ እንዲጠብቃቸው አዘዙት።
ሐዋርያት ሥራ 16:22-23 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ሕዝቡም አብረው ተነሡባቸው፥ ገዢዎቹም ልብሳቸውን ገፈው በበትር ይመቱአቸው ዘንድ አዘዙ፤ በብዙም ከደበደቡአቸው በኋላ ወደ ወኅኒ ጣሉአቸው፥ የወኅኒውንም ጠባቂ ተጠንቅቆ እንዲጠብቃቸው አዘዙት።