ሐዋርያት ሥራ 15:1-41 - Compare All Versions

ሐዋርያት ሥራ 15:1-41 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

ከይ​ሁዳ ሀገ​ርም የወ​ረዱ ሰዎች፥ “እንደ ሙሴ ሕግ ካል​ተ​ገ​ዘ​ራ​ችሁ ልት​ድኑ አት​ች​ሉም” እያሉ ወን​ድ​ሞ​ችን ያስ​ተ​ምሩ ነበር። ሕዝ​ቡም እጅግ ታወኩ፤ ጳው​ሎ​ስ​ንና በር​ና​ባ​ስ​ንም ተከ​ራ​ከ​ሩ​አ​ቸው፤ ስለ​ዚህ ነገ​ርም ጳው​ሎ​ስ​ንና በር​ና​ባ​ስን፥ ጓደ​ኞ​ቻ​ቸ​ው​ንም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ አሉት ወደ ሐዋ​ር​ያ​ትና ቀሳ​ው​ስት ሊል​ኳ​ቸው ተማ​ከሩ። ከቤተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ንም በተ​ላኩ ጊዜ ወደ ሰማ​ር​ያና ወደ ፊንቄ ደር​ሰው አሕ​ዛብ ወደ ሃይ​ማ​ኖት እንደ ተመ​ለሱ ነገ​ሩ​ቸ​አ​ቸው፤ ወን​ድ​ሞ​ች​ንም ሁሉ እጅግ ደስ አሰ​ኙ​አ​ቸው። ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በደ​ረሱ ጊዜም ምእ​መ​ና​ንና ሐዋ​ር​ያት፥ ቀሳ​ው​ስ​ትም ተቀ​በ​ሉ​አ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ያደ​ረ​ገ​ላ​ቸ​ውን ነገ​ሩ​አ​ቸው። ነገር ግን ካመ​ኑት ከፈ​ሪ​ሳ​ው​ያን ወገን አን​ዳ​ን​ዶች ተነ​ሥ​ተው፥ “ትገ​ዝ​ሩ​አ​ቸው ዘን​ድና የሙ​ሴን ሕግ እን​ዲ​ጠ​ብቁ ታዝ​ዙ​አ​ቸው ዘንድ ይገ​ባል” አሉ። ሐዋ​ር​ያ​ትና ቀሳ​ው​ስ​ትም ስለ​ዚህ ነገር የሚ​ያ​ደ​ር​ጉ​ትን ያዩ ዘንድ ተሰ​በ​ሰቡ። ብዙ ክር​ክ​ርም ከተ​ከ​ራ​ከሩ በኋላ ጴጥ​ሮስ ተነ​ሥቶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ ስሙ፤ ለአ​ሕ​ዛብ ከአፌ የወ​ን​ጌ​ሉን ቃል እን​ዳ​ሰ​ማ​ቸ​ውና እን​ዲ​ያ​ምኑ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አስ​ቀ​ድሞ እንደ መረ​ጠኝ እና​ንተ ራሳ​ችሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ። ልብን የሚ​ያ​ውቅ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለእኛ እንደ ሰጠን መን​ፈስ ቅዱ​ስን በመ​ስ​ጠት መሰ​ከ​ረ​ላ​ቸው። ልባ​ቸ​ው​ንም በእ​ም​ነት አን​ጽቶ ከእኛ አል​ለ​ያ​ቸ​ውም። አሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አት​ፈ​ታ​ተ​ኑት፤ እኛም አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም ልን​ሸ​ከ​መው ያል​ቻ​ል​ነ​ውን ቀን​በር በደቀ መዛ​ሙ​ርት ጫንቃ ላይ ለምን ትጭ​ና​ላ​ችሁ? ነገር ግን በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ጸጋ እን​ድን ዘንድ እን​ታ​መ​ና​ለን፤ እነ​ር​ሱም እንደ እኛ ይድ​ናሉ።” ያን​ጊ​ዜም ሕዝቡ ሁሉ ጸጥ ብለው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ሕ​ዛብ ዘንድ ያደ​ረ​ገ​ላ​ቸ​ውን ተአ​ም​ራ​ትና ድንቅ ሥራ ሁሉ ሲና​ገሩ ጳው​ሎ​ስ​ንና በር​ና​ባ​ስን አዳ​መ​ጡ​አ​ቸው። እነ​ር​ሱም ጸጥ ባሉ ጊዜ ያዕ​ቆብ መልሶ እን​ዲህ አለ፥ “ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ ስሙኝ። ስም​ዖ​ንም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አስ​ቀ​ድሞ አሕ​ዛ​ብን ይቅር እን​ዳ​ላ​ቸ​ውና ከው​ስ​ጣ​ቸ​ውም ለስሙ ሕዝ​ብን እንደ መረጠ ተና​ግ​ሮ​አል። በዚ​ህም መጽ​ሐፍ እን​ዲህ ብሎ እንደ ተና​ገረ የነ​ቢ​ያት ቃል ይስ​ማ​ማል። ከዚ​ህም በኋላ የወ​ደ​ቀ​ች​ውን የዳ​ዊ​ትን ቤት መልሼ እሠ​ራ​ታ​ለሁ፤ ፍራ​ሽ​ዋ​ንም አድ​ሳ​ለሁ፤ የቀ​ሩት ሰዎ​ችና ስሜም የተ​ጠ​ራ​ባ​ቸው አሕ​ዛብ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ይፈ​ልጉ ዘንድ፥ ይላል ይህን የሚ​ያ​ደ​ርግ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ከጥ​ንት ጀምሮ ሥራው ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የታ​ወቀ ነው። “አሁ​ንም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በተ​መ​ለሱ አሕ​ዛብ ላይ ሥር​ዐት አታ​ክ​ብዱ እላ​ች​ኋ​ለሁ። ነገር ግን ለጣ​ዖት ከሚ​ሠ​ዋው፥ ከዝ​ሙት፥ ሞቶ የተ​ገ​ኘ​ው​ንና ደም ከመ​ብ​ላት እን​ዲ​ርቁ፥ ለራ​ሳ​ቸው የሚ​ጠ​ሉ​ት​ንም በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ላይ እን​ዳ​ያ​ደ​ርጉ እዘ​ዙ​አ​ቸው። ሙሴም ከጥ​ንት ጀምሮ በየ​ከ​ተ​ማዉ የሚ​ሰ​ብ​ክ​ላ​ቸው ትም​ህ​ርት ነበር፤ በየ​ም​ኵ​ራ​ቡም በየ​ሰ​ን​በቱ ያነ​ብ​ቡት ነበር።” ከዚ​ህም በኋላ ሐዋ​ር​ያ​ትና ቀሳ​ው​ስት ሕዝ​ቡም ሁሉ ከጳ​ው​ሎ​ስና ከበ​ር​ና​ባስ ጋር ወደ አን​ጾ​ኪያ የሚ​ል​ኳ​ቸ​ውን ሰዎች ይመ​ርጡ ዘንድ ተስ​ማሙ፤ ከባ​ል​ን​ጀ​ሮ​ቻ​ቸው መካ​ከ​ልም የተ​ማ​ሩ​ትን ሰዎች በር​ና​ባስ የተ​ባለ ይሁ​ዳ​ንና ሲላ​ስን መረጡ። እን​ዲህ የም​ትል መል​እ​ክ​ትም በእ​ጃ​ቸው ጻፉ፤ “ከሐ​ዋ​ር​ያ​ትና ከቀ​ሳ​ው​ስት ከወ​ን​ድ​ሞ​ችም በአ​ን​ጾ​ኪያ፥ በሶ​ር​ያና በኪ​ል​ቅያ ለሚ​ኖሩ፥ ከአ​ሕ​ዛብ ላመኑ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ትድ​ረስ፤ ሰላም ለእ​ና​ንተ ይሁን፥ ደስ ይበ​ላ​ችሁ። ያላ​ዘ​ዝ​ና​ቸው ሰዎች ከእኛ ወጥ​ተው፦ ‘ትገ​ዘሩ ዘን​ድና የኦ​ሪ​ት​ንም ሕግ ትጠ​ብቁ ዘንድ ይገ​ባ​ች​ኋል’ ብለው በነ​ገር እንደ አወ​ኩ​አ​ች​ሁና ልባ​ች​ሁን እንደ አና​ወ​ጡት ሰም​ተ​ናል። ሁላ​ችን ከተ​ሰ​በ​ሰ​ብን በኋላ በአ​ንድ ቃል በየን፤ አንድ ሆነ​ንም ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ከጳ​ው​ሎ​ስና ከበ​ር​ና​ባስ ጋር ወደ እና​ንተ የም​ን​ል​ካ​ቸ​ውን ሰዎች መረ​ጥን። እነ​ር​ሱም ስለ ጌታ​ችን ስለ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን አሳ​ል​ፈው የሰጡ ሰዎች ናቸው። ይሁ​ዳ​ንና ሲላ​ስን ልከ​ና​ቸ​ዋ​ልና እነ​ርሱ በቃ​ላ​ቸው ይህን ያስ​ረ​ዱ​አ​ች​ኋል። ሥር​ዐት እን​ዳ​ና​ከ​ብድ ሌላም ሸክም እን​ዳ​ን​ጨ​ምር መን​ፈስ ቅዱስ ከእኛ ጋር ነውና፤ ነገር ግን ይህን በግድ ትተዉ ዘንድ እና​ዝ​ዛ​ች​ኋ​ለን። ለአ​ማ​ል​ክት የተ​ሠ​ዋ​ውን፥ ሞቶ የተ​ገ​ኘ​ውን፥ ደም​ንም አት​ብሉ፤ ከዝ​ሙ​ትም ራቁ፤ በራ​ሳ​ችሁ የም​ት​ጠ​ሉ​ት​ንም በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ ላይ አታ​ድ​ርጉ፥ ከእ​ነ​ዚህ ሥራ​ዎ​ችም ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ብት​ጠ​ብቁ በሰ​ላም ትኖ​ራ​ላ​ችሁ፤ ደኅና ሁኑ።” እነ​ር​ሱም ተል​ከው ወደ አን​ጾ​ኪያ ወረዱ፤ ሕዝ​ቡ​ንም ሰብ​ስ​በው የተ​ላ​ከ​ውን ደብ​ዳቤ ሰጡ​አ​ቸው። እነ​ር​ሱም አን​ብ​በው እጅግ ደስ አላ​ቸው፥ ተጽ​ና​ኑም። ይሁ​ዳና ሲላ​ስም መም​ህ​ራን ነበ​ሩና አስ​ተ​ማ​ሩ​አ​ቸው፤ ወን​ድ​ሞ​ች​ንም በብዙ ቃል አጽ​ና​ኑ​አ​ቸው። በእ​ነ​ር​ሱም ዘንድ አያሌ ቀን ከተ​ቀ​መጡ በኋላ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውን ተሰ​ና​ብ​ተው በሰ​ላም ወደ ሐዋ​ር​ያት ተመ​ለሱ። ሲላስ ግን በዚያ ሊቈይ ወደደ። ጳው​ሎ​ስና በር​ና​ባ​ስም በአ​ን​ጾ​ኪያ ቈዩ፤ ከሌ​ሎች ብዙ ሰዎች ጋርም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ሰበኩ፤ አስ​ተ​ማ​ሩም። ከጥ​ቂት ቀን በኋ​ላም ጳው​ሎስ በር​ና​ባ​ስን፦“እን​ግ​ዲ​ህስ እን​መ​ለ​ስና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ባስ​ተ​ማ​ር​ን​ባ​ቸው ሀገ​ሮች ያሉ​ትን ወን​ድ​ሞች እን​ጐ​ብ​ኛ​ቸው፤ እን​ዴት እን​ዳ​ሉም እን​ወቅ” አለው። በር​ና​ባ​ስም ማር​ቆስ የተ​ባ​ለ​ውን ዮሐ​ን​ስን ከእ​ነ​ርሱ ጋር ይዞት ሊሄድ ወደደ። ጳው​ሎስ ግን ከእ​ነ​ርሱ ጋር ሊወ​ስ​ደው አል​ፈ​ቀ​ደም፤ እነ​ርሱ በጵ​ን​ፍ​ልያ ሳሉ ትቶ​አ​ቸው ሄዶ​አ​ልና፤ አብ​ሮ​አ​ቸ​ውም ለሥራ አል​መ​ጣም ነበ​ርና። ስለ​ዚ​ህም ተኰ​ራ​ር​ፈው እርስ በር​ሳ​ቸው ተለ​ያዩ፤ በር​ና​ባ​ስም ማር​ቆ​ስን ይዞ በመ​ር​ከብ ወደ ቆጵ​ሮስ ሄደ። ጳው​ሎስ ግን ሲላ​ስን መረጠ፤ ወን​ድ​ሞ​ችም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ አደራ ከሰ​ጡት በኋላ ሄደ። በሶ​ር​ያና በኪ​ል​ቅ​ያም እየ​ዞረ አብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያ​ና​ትን አጽ​ናና።

ሐዋርያት ሥራ 15:1-41 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

አንዳንድ ሰዎችም ከይሁዳ ወደ አንጾኪያ ወርደው፣ “በሙሴ ሥርዐት መሠረት ካልተገረዛችሁ ልትድኑ አትችሉም” በማለት ወንድሞችን ማስተማር ጀመሩ። ይህም ጳውሎስንና በርናባስን ከእነርሱ ጋራ ወደ ከረረ ጠብና ክርክር ውስጥ ከተታቸው። ስለዚህ ጳውሎስና በርናባስ ከሌሎች አንዳንድ ምእመናን ጋራ ወደ ኢየሩሳሌም ወጥተው ስለዚሁ ጕዳይ ሐዋርያትንና ሽማግሌዎችን እንዲጠይቁ ተወሰነ። ቤተ ክርስቲያኒቱም እግረ መንገዳቸውን በፊንቄና በሰማርያ በኩል እንዲያልፉ ላከቻቸው፤ እነርሱም በእነዚህ ቦታዎች ለነበሩት የአሕዛብን መመለስና ማመን ነገሯቸው፤ ወንድሞችም ሁሉ በዚህ እጅግ ደስ አላቸው። ኢየሩሳሌም በደረሱ ጊዜም፣ ቤተ ክርስቲያንና ሐዋርያት እንዲሁም ሽማግሌዎች ተቀበሏቸው፤ የተላኩትም እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋራ ሆኖ የሠራውን ሁሉ ነገሯቸው። ከፈሪሳውያን ወገን ያመኑት አንዳንዶቹ ተነሥተው በመቆም፣ “አሕዛብ እንዲገረዙና የሙሴን ሕግ እንዲጠብቁ ማድረግ አስፈላጊ ነው” አሉ። ሐዋርያትና ሽማግሌዎችም ይህንኑ ጕዳይ ለማጤን ተሰበሰቡ። ከብዙ ክርክር በኋላ ጴጥሮስ ተነሥቶ እንዲህ አላቸው፤ “ወንድሞች ሆይ፤ እግዚአብሔር ከጥቂት ጊዜ በፊት በእናንተ መካከል እኔን መርጦ፣ አሕዛብ የወንጌልን ቃል ከእኔ አንደበት ሰምተው እንዲያምኑ ማድረጉን ታውቃላችሁ። ልብን የሚያውቅ አምላክ ለእኛ እንደ ሰጠን ሁሉ፣ ለእነርሱም መንፈስ ቅዱስን በመስጠት የተቀበላቸው መሆኑን መሰከረላቸው፤ ልባቸውንም በእምነት በማንጻት፣ በእኛና በእነርሱ መካከል ምንም ልዩነት አላደረገም። እንግዲህ፣ አባቶቻችንም እኛም ልንሸከመው ያልቻልነውን ቀንበር በደቀ መዛሙርት ጫንቃ ላይ በመጫን ለምን አሁን እግዚአብሔርን ትፈታተኑታላችሁ? እኛም የዳንነው ልክ እንደ እነርሱ በጌታ በኢየሱስ ጸጋ መሆኑን እናምናለን።” ጉባኤውም በሙሉ ዝም ብሎ፣ በርናባስና ጳውሎስ እግዚአብሔር በእነርሱ አማካይነት በአሕዛብ መካከል ስላደረጋቸው ታምራዊ ምልክቶችና ድንቅ ነገሮች ሲናገሩ ያዳምጣቸው ነበር። እነርሱም ተናግረው ሲጨርሱ፣ ያዕቆብ ተነሥቶ በመቆም እንዲህ አለ፤ “ወንድሞች ሆይ፤ ስሙኝ፤ እግዚአብሔር ከአሕዛብ ወገን ለርሱ የሚሆነውን ሕዝብ አስቀድሞ እንዴት እንደ ጐበኘ ስምዖን አስረድቶናል። እንዲህ ተብሎ የተጻፈው የነቢያቱም ቃል ከዚህ ጋራ ይስማማል፤ “ ‘ከዚህ በኋላ እመለሳለሁ፤ የወደቀውን የዳዊትን ቤት እገነባለሁ። ፍርስራሹን መልሼ አቆማለሁ፤ እንደ ገናም እሠራዋለሁ፤ ይኸውም የቀሩት ሰዎች ጌታን እንዲፈልጉ፣ ስሜን የተሸከሙ አሕዛብም ሁሉ እንዲሹኝ ነው፤ እነዚህን ያደረገ ጌታ እንዲህ ይላል፤’ እነርሱም ከጥንት ጀምሮ የታወቁ ናቸው። “ስለዚህ ወደ እግዚአብሔር የተመለሱትን አሕዛብ እንዳናስጨንቃቸው ይህ የእኔ ብያኔ ነው። ይልቁን በጣዖት ከረከሰ ነገር፣ ከዝሙት ርኩሰት፣ ታንቆ የሞተ እንስሳ ሥጋ ከመብላትና ደም ከመመገብ እንዲርቁ ልንጽፍላቸው ይገባል፤ የሙሴ ሕግማ ከጥንት ጀምሮ በየሰንበቱ በምኵራብ ሲነበብና በየከተማው ሲሰበክ ኖሯልና።” በዚህ ጊዜ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ከመላው ቤተ ክርስቲያን ጋራ ሆነው ከመካከላቸው አንዳንድ ሰዎችን መርጠው፣ ከጳውሎስና ከበርናባስ ጋራ ወደ አንጾኪያ ለመላክ ወሰኑ፤ ከወንድሞችም መካከል ዋነኛ የነበሩትን በርስያን የተባለውን ይሁዳንና ሲላስን መረጡ፤ በእነርሱም እጅ ቀጥሎ ያለውን ደብዳቤ ላኩ፤ ወንድሞቻችሁ ከሆኑት ከሐዋርያትና ከሽማግሌዎች፣ ከአሕዛብ ወገን አምነው በአንጾኪያ፣ በሶርያና በኪልቅያ ለሚገኙ ወንድሞች፤ ሰላምታችን ይድረሳችሁ። አንዳንድ ሰዎች ያለ እኛ ፈቃድ ከእኛ ዘንድ ወጥተው በንግግራቸው ልባችሁን እንዳወኩና እንዳናወጧችሁ ሰምተናል። ስለዚህ ጥቂት ሰዎች መርጠን ከተወዳጆቹ ከበርናባስና ከጳውሎስ ጋራ ወደ እናንተ ለመላክ ሁላችንም ተስማምተናል፤ በርናባስና ጳውሎስም ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሕይወታቸውን አሳልፈው የሰጡ ናቸው። ስለዚህ እኛ የጻፍነውን በቃል እንዲያረጋግጡላችሁ፣ እነሆ፤ ይሁዳንና ሲላስን ልከናል። ከእነዚህ አስፈላጊ ነገሮች በቀር ሌላ ተጨማሪ ሸክም እንዳንጭንባችሁ፣ ለመንፈስ ቅዱስም ለእኛም መልካም መስሎ ታይቶናል፤ ይኸውም፦ ለጣዖት ከተሠዋ ነገር፣ ከደም፣ ታንቆ ከሞተ እንስሳ ሥጋ እንዲሁም ከዝሙት ርኩሰት እንድትርቁ ነው። ከእነዚህ ዐይነት ነገሮች ብትርቁ ለእናንተ መልካም ነው። ደኅና ሁኑ። የተላኩትም ሰዎች ከተሰናበቱ በኋላ ወደ አንጾኪያ ወረዱ፤ በዚያም የምእመናኑን ጉባኤ በአንድነት ሰብስበው ደብዳቤውን ሰጧቸው። ሕዝቡም ካነበቡት በኋላ አበረታታች በሆነው ቃሉ ደስ ተሠኙ። ይሁዳና ሲላስም ራሳቸው ነቢያት ስለ ነበሩ፣ ወንድሞችን ብዙ ንግግር በማድረግ መከሯቸው፤ አበረቷቸውም። በዚያም ጥቂት ጊዜ ከቈዩ በኋላ፣ ከወንድሞች በሰላም ተሰናብተው ወደ ላኳቸው ሰዎች ተመለሱ። [ሲላስ ግን እዚያው ለመቅረት ወሰነ።] ጳውሎስና በርናባስም ከሌሎች ብዙ ሰዎች ጋራ ሆነው የጌታን ቃል እያስተማሩና እየሰበኩ በአንጾኪያ ተቀመጡ። ጳውሎስ ከጥቂት ጊዜ በኋላ በርናባስን፣ “ተነሣና የጌታን ቃል ወደ ሰበክንባቸው ከተሞች ሁሉ እንሂድ፤ በዚያ ያሉ ወንድሞችም በምን ሁኔታ እንዳሉ ለማወቅ እንጐብኛቸው” አለው። በርናባስም ማርቆስ የተባለው ዮሐንስ ዐብሯቸው እንዲሄድ ፈለገ፤ ጳውሎስ ግን እርሱን ይዞ ለመሄድ አልፈለገም፤ ምክንያቱም፣ ቀደም ሲል ማርቆስ ከእነርሱ ተለይቶ በጵንፍልያ ስለ ቀረ እና ወደ ሥራ ዐብሯቸው ስላልሄደ ነበር። እንዲህ የከረረ አለመግባባት በመካከላቸው ስለ ተፈጠረ እርስ በርስ ተለያዩ፤ ስለዚህ በርናባስ ማርቆስን ይዞ በመርከብ ወደ ቆጵሮስ ሄደ። ጳውሎስ ግን ሲላስን መረጠ፤ ወንድሞችም ለጌታ ጸጋ ዐደራ ከሰጡት በኋላ ተለይቷቸው ሄደ፤ አብያተ ክርስቲያናትንም እያበረታታ በሶርያና በኪልቅያ በኩል ዐለፈ።

ሐዋርያት ሥራ 15:1-41 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

አንዳንዶችም ከይሁዳ ወረዱና፦ “እንደ ሙሴ ሥርዓት ካልተገረዛችሁ ትድኑ ዘንድ አትችሉም” ብለው ወንድሞችን ያስተምሩ ነበር። በእነርሱና በጳውሎስ በበርናባስም መካከል ብዙ ጥልና ክርክር በሆነ ጊዜ፥ ስለዚህ ክርክር ጳውሎና በርናባስ ከእነርሱም አንዳንዶች ሌሎች ሰዎች ወደ ሐዋርያት ወደ ሽማግሌዎችም ወደ ኢየሩሳሌም ይወጡ ዘንድ ተቈረጠ። ቤተ ክርስቲያኑም በመንገድ እየረዳቸው እነርሱ የአሕዛብን መመለስ እየተረኩ በፊንቄና በሰማርያ አለፉ፥ ወንድሞችንም ሁሉ እጅግ ደስ አሰኙአቸው። ወደ ኢየሩሳሌምም በደረሱ ጊዜ ቤተ ክርስቲያንና ሐዋርያት ሽማግሌዎችም ተቀበሉአቸው፥ እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር ያደረገውን ሁሉ አወሩ። ከፈሪሳውያን ወገን ግን ያመኑት አንዳንዶቹ ተነሥተው፦ “ትገርዙአቸው ዘንድና የሙሴን ሕግ እንዲጠብቁ ታዙአቸው ዘንድ ይገባል” አሉ። ሐዋርያትና ሽማግሌዎችም ስለዚህ ነገር ለመማከር ተሰበሰቡ። ከብዙ ክርክርም በኋላ ጴጥሮስ ተነሥቶ እንዲህ አላቸው ወንድሞች ሆይ፥ አሕዛብ ከአፌ የወንጌልን ቃል ሰምተው ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር በመጀመሪያው ዘመን ከእናንተ እኔን እንደ መረጠኝ እናንተ ታውቃላችሁ። ልብንም የሚያውቅ አምላክ ለእኛ ደግሞ እንደ ሰጠን መንፈስ ቅዱስን በመስጠት መሰከረላቸው፤ ልባቸውንም በእምነት ሲያነጻ በእኛና በእነርሱ መካከል አንዳች አልለየም። እንግዲህ አባቶቻችንና እኛ ልንሸከመው ያልቻልነውን ቀንበር በደቀ መዛሙርት ጫንቃ ላይ በመጫን እግዚአብሔርን አሁን ስለ ምን ትፈታተናላችሁ? ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ እንደ እነርሱ ደግሞ እንድን ዘንድ እናምናለን።” ሕዝቡም ሁሉ ዝም አሉ፥ በርናባስና ጳውሎስም እግዚአብሔር በእጃቸው በአሕዛብ መካከል ያደረገውን ምልክትና ድንቅ ሁሉ ሲተርኩላቸው ይሰሙ ነበር። እነርሱም ዝም ካሉ በኋላ ያዕቆብ እንዲህ ብሎ መለሰ፦ “ወንድሞች ሆይ፥ ስሙኝ። እግዚአብሔር ለስሙ የሚሆንን ወገን ከአሕዛብ ይወስድ ዘንድ አስቀድሞ እንዴት እንደ ጐበኘ ስምዖን ተርኮአል። ከዚህም ጋር የነቢያት ቃል ይሰማማል፥ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፦ ‘ከዚህ በኋላ የቀሩት ሰዎችና በስሜ የተጠሩት አሕዛብ ሁሉ ጌታን ይፈልጉ ዘንድ እመለሳለሁ፥ የወደቀችውንም የዳዊትን ድንኳን እንደ ገና እሠራታለሁ፥ ፍራሽዋንም እንደ ገና እሠራታለሁ እንደ ገናም አቆማታለሁ ይላል ይህን የሚያደርግ ጌታ። ከጥንት ጀምሮ ሥራው ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ የታወቀ ነው።’ ስለዚህ ከአሕዛብ ወደ እግዚአብሔር የዞሩትን እንዳናስቸግራቸው፥ ነገር ግን ከጣዖት ርኵሰትና ከዝሙት ከታነቀም ከደምም ይርቁ ዘንድ እንድንጽፍላቸው እቈርጣለሁ። ሙሴስ ከቀደሙት ትውልድ ጀምሮ በሰንበት በሰንበት በምኵራቦቹ ሲያነቡ በየከተማው እርሱን የሚሰብኩ አሉት።” ያን ጊዜ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ከቤተ ክርስቲያኑ ሁሉ ጋር ከእነርሱ የተመረጡትን ሰዎች ከጳውሎስና ከበርናባስ ጋር ወደ አንጾኪያ ይልኩ ዘንድ ፈቀዱ፤ እነርሱም በወንድሞች መካከል ዋናዎች ሆነው በርስያን የተባለው ይሁዳና ሲላስ ነበሩ። እንዲህም ጽፈው በእነርሱ እጅ ላኩ፦ “ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ወንድሞችም በአንጾኪያና በሶርያ በኪልቅያም ለሚኖሩ ከአሕዛብ ወገን ለሆኑ ወንድሞች ሰላምታ ያቀርባሉ። ያላዘዝናቸው ሰዎች ከእኛ ወጥተው፦ ‘ትገረዙ ዘንድና ሕግን ትጠብቁ ዘንድ ይገባችኋል’ ብለው ልባችሁን እያወኩ በቃል እንዳናወጡአችሁ ስለ ሰማን፥ ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነፍሳቸውን ከሰጡት ከምንወዳቸው ከበርናባስና ከጳውሎስ ጋር የተመረጡትን ሰዎች ወደ እናንተ እንልክ ዘንድ በአንድ ልብ ሆነን ፈቀድን። ራሳቸውም ደግሞ በቃላቸው ያንኑ ይነግሩአችሁ ዘንድ ይሁዳንና ሲላስን ልከናል። ለጣዖት ከተሠዋ፥ ከደምም፥ ከታነቀም፥ ከዝሙትም ትርቁ ዘንድ ከዚህ ከሚያስፈልገው በቀር ሌላ ሸክም እንዳንጭንባችሁ እኛና መንፈስ ቅዱስ ፈቅደናልና፤ ከዚህም ሁሉ ራሳችሁን ብትጠብቁ በመልካም ትኖራላችሁ። ጤና ይስጣችሁ።” እነርሱም ተሰናብተው ወደ አንጾኪያ ወረዱ፥ ሕዝቡንም ሰብስበው ደብዳቤውን ሰጡአቸው። ባነበቡትም ጊዜ ከምክሩ የተነሣ ደስ አላቸው። ይሁዳና ሲላስም ደግሞ ነቢያት ነበሩና ወንድሞችን በብዙ ቃል መክረው አጸኑአቸው። አያሌ ቀንም ከተቀመጡ በኋላ ከወንድሞች በሰላም ተሰናብተው ወደ ሐዋርያት ሄዱ። ሲላስ ግን በዚያ ይኖር ዘንድ ፈቀደ። ጳውሎስና በርናባስም ከሌሎች ከብዙ ሰዎች ጋር ደግሞ የጌታን ቃል እያስተማሩና ወንጌልን እየሰበኩ በአንጾኪያ ይቀመጡ ነበር። ከጥቂት ቀንም በኋላ ጳውሎስ በርናባስን፦ “ተመልሰን የጌታን ቃል በተናገርንበት በየከተማው ሁሉ ወንድሞችን እንጐብኛቸው፥ እንዴት እንዳሉም እንወቅ” አለው። በርናባስም ማርቆስ የተባለውን ዮሐንስን ደግሞ ከእነርሱ ጋር ይወስድ ዘንድ አሰበ፤ ጳውሎስ ግን ይህን ከእነርሱ ጋር ሊወስድ አልፈቀደም፥ ከእነርሱ ዘንድ ከጵንፍልያ ተለይቶ ነበርና፥ ወደ ሥራም ከእነርሱ ጋር አልመጣም ነበርና። ስለዚህም እርስ በርሳቸው እስኪአያዩ ድረስ መከፋፋት ሆነ፥ በርናባስም ማርቆስን ይዞ በመርከብ ወደ ቆጵሮስ ሄደ። ጳውሎስ ግን ሲላስን መረጠ፥ ወንድሞችም ለእግዚአብሔር ጸጋ አደራ ከሰጡት በኋላ ወጣ፤ አብያተ ክርስትያናትንም እያጸና በሶርያና በኪልቅያ ይዞር ነበር።

ሐዋርያት ሥራ 15:1-41 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

አንዳንድ ሰዎች ከይሁዳ ወደ አንጾኪያ ሄደው፥ “ለሙሴ በተሰጠው ሕግ መሠረት ካልተገረዛችሁ ልትድኑ አትችሉም” እያሉ አማኞችን ያስተምሩ ጀመር። ጳውሎስና በርናባስ ስለዚህ ጉዳይ ከሰዎቹ ጋር ንትርክና ክርክር አደረጉ፤ ከዚህ በኋላ ጳውሎስና በርናባስ በአንጾኪያ ካሉ ከሌሎች ጥቂት ወንድሞች ጋር ሆነው ወደ ኢየሩሳሌም እንዲሄዱና ጉዳዩን ለሐዋርያትና ለሽማግሌዎች እንዲያቀርቡ ተወሰነ። ስለዚህ እነርሱ በቤተ ክርስቲያን ተልከው ሄዱ፤ በፊንቄና በሰማርያ ሲያልፉም የአሕዛብን ወደ እግዚአብሔር መመለስ ተናገሩ፤ ይህም ዜና ክርስቲያኖችን ሁሉ አስደሰተ። ወደ ኢየሩሳሌም በደረሱ ጊዜ ቤተ ክርስቲያንና ሐዋርያት፥ ሽማግሌዎችም ተቀበሉአቸው፤ መልእክተኞቹም እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ሆኖ ያደረገውን ሁሉ አወሩላቸው። ነገር ግን ከፈሪሳውያን ወገን የሆኑ አንዳንድ አማኞች ተነሡና “አሕዛብ እንዲገረዙና የኦሪትን ሕግ እንዲጠብቁ ማድረግ ይገባል” አሉ። ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ይህን ጉዳይ ለመመርመር ተሰበሰቡ፤ ብዙ ክርክር ከተደረገም በኋላ ጴጥሮስ ተነሥቶ እንዲህ አላቸው፤ “ወንድሞች ሆይ፥ አሕዛብ በእኔ አማካይነት የወንጌልን ቃል ሰምተው እንዲያምኑ ከዚህ በፊት እግዚአብሔር እኔን ከእናንተ መካከል እንደ መረጠኝ ታውቃላችሁ። የሰውን ልብ የሚያውቅ አምላክ፥ መንፈስ ቅዱስን ለእኛ እንደ ሰጠው ዐይነት ለእነርሱም በመስጠት መሰከረላቸው። ልባቸውን በእምነት ስላነጻ በእኛና በእነርሱ መካከል ምንም ልዩነት አላደረገም። ታዲያ፥ አባቶቻችንም ሆኑ እኛ ልንሸከመው ያልቻልነውን ቀንበር በአማኞች ጫንቃ ላይ በመጫን ለምን አሁን እግዚአብሔርን ትፈታተኑታላችሁ? እኛም የምንድነው ልክ እንደ እነርሱ በጌታ በኢየሱስ ጸጋ መሆኑን እናምናለን።” በዚህ ጊዜ ጉባኤው ጸጥ ብሎ በርናባስና ጳውሎስ በእነርሱ አማካይነት እግዚአብሔር በአሕዛብ መካከል ያደረገውን ተአምርና ድንቅ ነገር ሁሉ ሲናገሩ በመገረም አዳመጣቸው። እነርሱ ተናግረው ካበቁ በኋላ፥ ያዕቆብ እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ወንድሞች ሆይ! እስቲ ስሙኝ! እግዚአብሔር አንድ በስሙ የሚጠራ ሕዝብን ከመካከላቸው ለመምረጥ ለመጀመሪያ ጊዜ አሕዛብን እንዴት እንደ ጐበኘ ስምዖን አስረድቶአል። ከዚህም አሳብ ጋር የነቢያት ቃል ይስማማል፤ ይህም እንዲህ ተብሎ የተጻፈው ነው፦ ‘ከዚህ በኋላ እመለሳለሁ፤ የፈረሰውንም የዳዊትን ቤት እሠራለሁ፤ ፍርስራሹንም ጠግኜ እንደገና አቆማለሁ። ይህንንም የማደርገው የቀሩት ሰዎችና በስሜ የተጠሩት አሕዛብ ሁሉ እኔን እግዚአብሔርን እንዲፈልጉ ነው፤ ከጥንት ጀምሮ ይህን ሁሉ ያስታወቅኹ እኔ እግዚአብሔር እንዲህ እላለሁ፤’ “ስለዚህ የእኔ አሳብ ወደ እግዚአብሔር የሚመለሱትን አሕዛብ እንዳናስቸግራቸው ነው። ይልቅስ ‘ለጣዖት በመሠዋቱ ምክንያት የረከሰ ምግብን አትብሉ፤ ከዝሙት ራቁ፤ ሳይታረድና ደሙም ሳይፈስ ታንቆ የሞተ እንስሳ ሥጋን አትብሉ፤ ደምንም አትብሉ’ ብለን እንጻፍላቸው። ከጥንቱም ጀምሮ የሙሴ ሕግ በየሰንበቱ በምኲራቦች ይነበብ ነበር፤ ቃሉም በየከተማው ይሰበካል።” ከዚህ በኋላ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ከቤተ ክርስቲያን ሰዎች ሁሉ ጋር ሆነው ከጉባኤው መካከል ጥቂት ሰዎችን መርጠው ከጳውሎስና ከበርናባስ ጋር ወደ አንጾኪያ ለመላክ ወሰኑ፤ ስለዚህ በወንድሞች መካከል በመሪነት መልካም ዝና የነበራቸውን በርሳባስ የተባለውን ይሁዳንና ሲላስን መረጡ። የተጻፈውን ደብዳቤ በእነርሱ እጅ ላኩ፤ ደብዳቤውም እንዲህ የሚል ነበር፦ “እኛ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ወንድሞቻችሁ፥ በአንጾኪያና በሶርያ፥ በኪልቅያም ለምትኖሩ ከአሕዛብ ወገን ለሆናችሁ ወንድሞቻችን ሰላምታ እናቀርባለን፤ ከእኛ መካከል አንዳንድ ሰዎች እኛ ሳናዛቸው ወደ እናንተ መጥተው በነገሩአችሁ ቃል እንዳስቸገሩአችሁና ግራ እንዳጋቡአችሁ ሰምተናል፤ ስለዚህ በአንድነት ከተሰበሰብን በኋላ መልእክተኞችን መርጠን ከተወደዱት ወንድሞቻችን ከበርናባስና ከጳውሎስ ጋር ወደ እናንተ ልንልካቸው ተስማማን። በርናባስና ጳውሎስ ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወታቸውን አሳልፈው የሰጡ ናቸው። የጻፍንላችሁን በቃልም ጭምር እንዲነግሩአችሁ ይሁዳንና ሲላስን ልከናል። ከእነዚህ ከሚከተሉት አስፈላጊ ነገሮች በስተቀር ሌላ ከባድ ሸክም እንዳንጭንባችሁ መንፈስ ቅዱስና እኛ መልካም ሆኖ አግኝተነዋል፤ ለጣዖት በመሠዋቱ ምክንያት የረከሰ ምግብ አትብሉ፤ ታንቆ የሞተ እንስሳ ሥጋን አትብሉ፤ ደምም አትብሉ፤ ከዝሙት ራቁ፤ ከእነዚህ ነገሮች ሁሉ ብትጠበቁ መልካም ታደርጋላችሁ፤ ደኅና ሁኑ።” መልእክተኞቹም ተሰናብተው ወደ አንጾኪያ ሄዱ፤ አማኞቹንም ሰብስበው ደብዳቤውን ሰጡአቸው። አማኞቹም ደብዳቤውን ባነበቡ ጊዜ በሚያጽናናው መልእክት እጅግ ደስ አላቸው። ይሁዳና ሲላስ ነቢያት ስለ ነበሩ ወንድሞችን በብዙ ቃል መክረው አጽናኑአቸው፤ አበረታቱአቸውም። ይሁዳና ሲላስ ጥቂት ቀኖች እዚያ ከቈዩ በኋላ ከአማኞች ወንድሞች ጋር ተሰነባብተው ወደ ላኩአቸው ተመልሰው ሄዱ። [ሲላስ ግን እዚያው መቅረት ፈለገ።] ጳውሎስና በርናባስም ከሌሎች ከብዙ አማኞች ጋር ሆነው የጌታን ቃል እያስተማሩና እየሰበኩ ጥቂት ቀኖች በአንጾኪያ ቈዩ። ከጥቂት ቀኖች በኋላ ጳውሎስ በርናባስን “ና እንመለስና ከዚህ በፊት የጌታን ቃል ባበሠርንባቸው ከተሞች ሁሉ ያሉትን ወንድሞች እንጐብኝ፤ እንዴት እንደ ሆኑም እንወቅ” አለው። በርናባስም ማርቆስ የተባለው ዮሐንስ ከእነርሱ ጋር አብሮአቸው እንዲሄድ ፈለገ። ጳውሎስ ግን ይህ ሰው ከእነርሱ ጋር እንዲሄድ አልፈቀደም፤ ያልፈቀደበትም ምክንያት እሱ በጵንፍልያ ከእነርሱ ተለይቶ ስለ ቀረና ወደ ሥራም ከእነርሱ ጋር ስላልሄደ ነው። በዚህ ምክንያት በጳውሎስና በበርናባስ መካከል ከፍ ያለ ክርክር ተነሣና ተለያዩ፤ ስለዚህ በርናባስ ማርቆስን ይዞ በመርከብ ወደ ቆጵሮስ ሄደ። ጳውሎስ ግን ሲላስን መረጠ፤ ወንድሞችም ጳውሎስን ለጌታ ጸጋ ዐደራ ከሰጡት በኋላ ሄደ። እርሱም አብያተ ክርስቲያንን እያበረታታ በሶርያና በኪልቅያ በኩል አለፈ።

ሐዋርያት ሥራ 15:1-41 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

አንዳንዶችም ከይሁዳ ወረዱና “እንደ ሙሴ ሥርዓት ካልተገረዛችሁ ትድኑ ዘንድ አትችሉም፤” ብለው ወንድሞችን ያስተምሩ ነበር። በእነርሱና በጳውሎስ በበርናባስም መካከል ብዙ ጥልና ክርክር በሆነ ጊዜ፥ ስለዚህ ክርክር ጳውሎና በርናባስ ከእነርሱም አንዳንዶች ሌሎች ሰዎች ወደ ሐዋርያት ወደ ሽማግሌዎችም ወደ ኢየሩሳሌም ይወጡ ዘንድ ተቆረጠ። ቤተ ክርስቲያኑም በመንገድ እየረዳቸው እነርሱ የአሕዛብን መመለስ እየተረኩ በፊንቄና በሰማርያ አለፉ፤ ወንድሞችንም ሁሉ እጅግ ደስ አሰኙአቸው። ወደ ኢየሩሳሌምም በደረሱ ጊዜ ቤተ ክርስቲያንና ሐዋርያት ሽማግሌዎችም ተቀበሉአቸው፤ እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር ያደረገውን ሁሉ አወሩ። ከፈሪሳውያን ወገን ግን ያመኑት አንዳንዶቹ ተነሥተው “ትገርዙአቸው ዘንድና የሙሴን ሕግ እንዲጠብቁ ታዙአቸው ዘንድ ይገባል፤” አሉ። ሐዋርያትና ሽማግሌዎችም ስለዚህ ነገር ለመማከር ተሰበሰቡ። ከብዙ ክርክርም በኋላ ጴጥሮስ ተነሥቶ እንዲህ አላቸው “ወንድሞች ሆይ! አሕዛብ ከአፌ የወንጌልን ቃል ሰምተው ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር በመጀመሪያው ዘመን ከእናንተ እኔን እንደ መረጠኝ እናንተ ታውቃላችሁ። ልብንም የሚያውቅ አምላክ ለእኛ ደግሞ እንደ ሰጠን መንፈስ ቅዱስን በመስጠት መሰከረላቸው፤ ልባቸውንም በእምነት ሲያነጻ በእኛና በእነርሱ መካከል አንዳች አልለየም። እንግዲህ አባቶቻችንና እኛ ልንሸከመው ያልቻልነውን ቀንበር በደቀ መዛሙርት ጫንቃ ላይ በመጫን እግዚአብሔርን አሁን ስለምን ትፈታተናላችሁ? ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ እንደ እነርሱ ደግሞ እንድን ዘንድ እናምናለን።” ሕዝቡም ሁሉ ዝም አሉ፤ በርናባስና ጳውሎስም እግዚአብሔር በእጃቸው በአሕዛብ መካከል ያደረገውን ምልክትና ድንቅ ሁሉ ሲተርኩላቸው ይሰሙ ነበር። እነርሱም ዝም ካሉ በኋላ ያዕቆብ እንዲህ ብሎ መለሰ “ወንድሞች ሆይ! ስሙኝ። እግዚአብሔር ለስሙ የሚሆንን ወገን ከአሕዛብ ይወስድ ዘንድ አስቀድሞ እንዴት እንደ ጐበኘ ስምዖን ተርኮአል። ከዚህም ጋር የነቢያት ቃል ይስማማል፤ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ “‘ከዚህ በኋላ እመለሳለሁ፤ የፈረሰውን የዳዊትን ቤት እገነባለሁ። ፍርስራሹን መልሼ አቆማለሁ፤ እንደገናም እሠራዋለሁ፤ የቀሩት ሰዎችና በስሜ የተጠሩት አሕዛብ ሁሉ ጌታን እንዲፈልጉ፥ ይላል ይህን የሚያደርግ ጌታ። ከጥንት ጀምሮ ሥራቸው ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ የታወቀ ነው።’ ስለዚህ ከአሕዛብ ወደ እግዚአብሔር የዞሩትን እንዳናስቸግራቸው፥ ነገር ግን ከጣዖት ርኩሰትና ከዝሙት ከታነቀም ከደምም ይርቁ ዘንድ እንድንጽፍላቸው እቆርጣለሁ። ሙሴስ ከቀደሙት ትውልድ ጀምሮ በሰንበት በሰንበት በምኵራቦቹ ሲያነቡ በየከተማው እርሱን የሚሰብኩ አሉት።” ያንጊዜ ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ከቤተ ክርስቲያኑ ሁሉ ጋር ከእነርሱ የተመረጡትን ሰዎች ከጳውሎስና ከበርናባስ ጋር ወደ አንጾኪያ ይልኩ ዘንድ ፈቀዱ፤ እነርሱም በወንድሞች መካከል ዋናዎች ሆነው በርስያን የተባለው ይሁዳና ሲላስ ነበሩ። እንዲህም ጽፈው በእነርሱ እጅ ላኩ “ሐዋርያትና ሽማግሌዎች ወንድሞችም በአንጾኪያና በሶርያ በኪልቅያም ለሚኖሩ ከአሕዛብ ወገን ለሆኑ ወንድሞች ሰላምታ ያቀርባሉ። ያላዘዝናቸው ሰዎች ከእኛ ወጥተው ‘ትገረዙ ዘንድና ሕግን ትጠብቁ ዘንድ ይገባችኋል፤’ ብለው ልባችሁን እያወኩ በቃል እንዳናወጡአችሁ ስለ ሰማን፥ ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ነፍሳቸውን ከሰጡት ከምንወዳቸው ከበርናባስና ከጳውሎስ ጋር የተመረጡትን ሰዎች ወደ እናንተ እንልክ ዘንድ በአንድ ልብ ሆነን ፈቀድን። ራሳቸውም ደግሞ በቃላቸው ያንኑ ይነግሩአችሁ ዘንድ ይሁዳንና ሲላስን ልከናል። ለጣዖት ከተሠዋ፥ ከደምም፥ ከታነቀም፥ ከዝሙትም ትርቁ ዘንድ ከዚህ ከሚያስፈልገው በቀር ሌላ ሸክም እንዳንጭንባችሁ እኛና መንፈስ ቅዱስ ፈቅደናልና፤ ከዚህም ሁሉ ራሳችሁን ብትጠብቁ በመልካም ትኖራላችሁ። ጤና ይስጣችሁ።” እነርሱም ተሰናብተው ወደ አንጾኪያ ወረዱ፤ ሕዝቡንም ሰብስበው ደብዳቤውን ሰጡአቸው። ባነበቡትም ጊዜ ከምክሩ የተነሣ ደስ አላቸው። ይሁዳና ሲላስም ደግሞ ነቢያት ነበሩና ወንድሞችን በብዙ ቃል መክረው አጸኑአቸው። አያሌ ቀንም ከተቀመጡ በኋላ ከወንድሞች በሰላም ተሰናብተው ወደ ሐዋርያት ሄዱ። ሲላስ ግን በዚያ ይኖር ዘንድ ፈቀደ። ጳውሎስና በርናባስም ከሌሎች ከብዙ ሰዎች ጋር ደግሞ የጌታን ቃል እያስተማሩና ወንጌልን እየሰበኩ በአንጾኪያ ይቀመጡ ነበር። ከጥቂት ቀንም በኋላ ጳውሎስ በርናባስን “ተመልሰን የጌታን ቃል በተናገርንበት በየከተማው ሁሉ ወንድሞችን እንጐብኛቸው፤ እንዴት እንዳሉም እንወቅ፤” አለው። በርናባስም ማርቆስ የተባለውን ዮሐንስን ደግሞ ከእነርሱ ጋር ይወስድ ዘንድ አሰበ፤ ጳውሎስ ግን ይህን ከእነርሱ ጋር ሊወስድ አልፈቀደም፤ ከእነርሱ ዘንድ ከጵንፍልያ ተለይቶ ነበርና፤ ወደ ሥራም ከእነርሱ ጋር አልመጣም ነበርና። ስለዚህም እርስ በርሳቸው እስኪለያዩ ድረስ መከፋፋት ሆነ፥ በርናባስም ማርቆስን ይዞ በመርከብ ወደ ቆጵሮስ ሄደ። ጳውሎስ ግን ሲላስን መረጠ፤ ወንድሞችም ለእግዚአብሔር ጸጋ አደራ ከሰጡት በኋላ ወጣ፤ አብያተ ክርስትያናትንም እያጸና በሶርያና በኪልቅያ ይዞር ነበር።