ሐዋርያት ሥራ 13:2-3 - Compare All Versions

ሐዋርያት ሥራ 13:2-3 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ ሲሠሩ፥ ሲጾ​ሙም መን​ፈስ ቅዱስ፥ “በር​ና​ባ​ስ​ንና ሳው​ልን እኔ ለፈ​ለ​ግ​ኋ​ቸው ሥራ ለዩ​ልኝ” አላ​ቸው። ያን​ጊ​ዜም ከጾ​ሙና ከጸ​ለዩ፥ እጃ​ቸ​ው​ንም በራ​ሳ​ቸው ላይ ከጫ​ኑ​ባ​ቸው በኋላ ላኩ​አ​ቸው።

ሐዋርያት ሥራ 13:2-3 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

እነዚህም ጌታን እያመለኩና እየጾሙ ሳሉ፣ መንፈስ ቅዱስ፣ “በርናባስንና ሳውልን እኔ ለጠራኋቸው ሥራ ለዩልኝ” አለ። እነርሱም ከጾሙና ከጸለዩ በኋላ እጃቸውን ጭነው አሰናበቷቸው።

ሐዋርያት ሥራ 13:2-3 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

እነዚህም ጌታን ሲያመልኩና ሲጦሙ መንፈስ ቅዱስ፦ “በርናባስንና ሳውልን ለጠራኋቸው ሥራ ለዩልኝ” አለ። በዚያን ጊዜም ከጦሙ ከጸለዩም እጃቸውንም ከጫኑ በኋላ አሰናበቱአቸው።

ሐዋርያት ሥራ 13:2-3 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

እነርሱ ጌታን ሲያገለግሉና ሲጾሙ ሳሉ መንፈስ ቅዱስ “እኔ ለመረጥኳቸው ሥራ በርናባስንና ሳውልን ለዩልኝ!” አለ። እነርሱም ጾመውና ጸልየው እጆቻቸውን ከጫኑባቸው በኋላ ላኳቸው።

ሐዋርያት ሥራ 13:2-3 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

እነዚህም ጌታን ሲያመልኩና ሲጦሙ መንፈስ ቅዱስ “በርናባስንና ሳውልን ለጠራኋቸው ሥራ ለዩልኝ፤” አለ። በዚያን ጊዜም ከጦሙ ከጸለዩም እጃቸውንም ከጫኑ በኋላ አሰናበቱአቸው።