ሐዋርያት ሥራ 13:11 - Compare All Versions

ሐዋርያት ሥራ 13:11 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))

እነሆ፥ አሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በአ​ንተ ላይ ነው፤ ዕው​ርም ትሆ​ና​ለህ፤ እስከ ጊዜ​ውም ፀሐ​ይን አታ​ይም፤” ወዲ​ያ​ው​ኑም ታወረ፤ ጨለ​ማም ዋጠው፤ የሚ​መ​ራ​ውም ፈለገ።

ሐዋርያት ሥራ 13:11 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)

አሁንም የጌታ እጅ በአንተ ላይ ነው፤ ዕውር ትሆናለህ፤ ከእንግዲህ የፀሓይን ብርሃን ለአንድ አፍታ እንኳ አታይም።” ወዲያውም ጭጋግና ጨለማ በላዩ ወረደ፤ እጁን ይዞ የሚመራውንም ሰው ለመፈለግ ወዲያ ወዲህ ይል ጀመር።

ሐዋርያት ሥራ 13:11 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))

አሁንም፥ እነሆ፥ የጌታ እጅ በአንተ ላይ ናት፥ ዕውርም ትሆናለህ እስከ ጊዜውም ፀሐይን አታይም” አለው። ያን ጊዜም ጭጋግና ጨለማ ወደቀበት፥ በእጁም የሚመራውን እየዞረ ፈለገ።

ሐዋርያት ሥራ 13:11 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

አሁንም እነሆ፥ የጌታ እጅ ይመታሃል፤ ዕውርም ትሆናለህ፤ ለጥቂት ጊዜም የፀሐይን ብርሃን አታይም።” ወዲያውኑ ዐይኖቹን ጭጋግና ጨለማ ሸፈናቸው፤ እጁን ይዞ የሚመራውንም ሰው ዙሪያውን መፈለግ ጀመረ።

ሐዋርያት ሥራ 13:11 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))

አሁንም፥ እነሆ፥ የጌታ እጅ በአንተ ላይ ናት፤ ዕውርም ትሆናለህ እስከ ጊዜውም ፀሐይን አታይም፤” አለው። ያን ጊዜም ጭጋግና ጨለማ ወደቀበት፤ በእጁም የሚመራውን እየዞረ ፈለገ።