2 ሳሙኤል 10:12 - Compare All Versions
2 ሳሙኤል 10:12 አማ2000 (የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ))
በርታ፤ ስለ ሕዝባችንና ስለ አምላካችንም ከተሞች እንጽና፤ እግዚአብሔርም በዐይኑ ፊት ደስ ያሰኘውን መልካሙን ያድርግ።”
2 ሳሙኤል 10:12 NASV (አዲሱ መደበኛ ትርጒም)
እንግዲህ በርታ፤ ለሕዝባችንና ለአምላካችን ከተሞች በጀግንነት እንዋጋ፤ እግዚአብሔርም በፊቱ ደስ ያሠኘውን ያድርግ።”
2 ሳሙኤል 10:12 አማ54 (መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት))
አይዞህ፥ ስለ ሕዝቦችንና ስለ አምላካችንም ከተሞች እንበርታ፥ እግዚአብሔርም ደስ ያሰኘውን ያድርግ አለ።
2 ሳሙኤል 10:12 አማ05 (አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም)
እንግዲህ አይዞህ በርታ! ለሕዝባችንና ለአምላካችን ከተሞች ስንል በርትተን እንዋጋ! እንግዲህ ሁሉ ነገር እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን!”
2 ሳሙኤል 10:12 መቅካእኤ (መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ))
እንግዲህ በርታ፤ ለሕዝባችንና ለአምላካችን ከተሞች በጀግንነት እንዋጋ፤ ጌታም በፊቱ መልካም መስሎ የታየውን ያድርግ።”