2 ጴጥሮስ 2:21-22
2 ጴጥሮስ 2:21-22 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
የጽድቅን መንገድ ካወቁ በኋላ ከተሰጣቸው ቅዱስ ትእዛዝ ወደ ኋላ ከሚመለሱ ይልቅ የጽድቅን መንገድ ሳያውቁ ቀርተው ቢሆን ኖሮ በተሻላቸው ነበር። “ውሻ ወደ ትፋቱ ይመለሳል፤” እንዲሁም “እርያ ብትታጠብ በጭቃ ለመንከባለል ትመለሳለች፤” የሚለው እውነተኛ ምሳሌ ደርሶባቸዋል።
2 ጴጥሮስ 2:21-22 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ዕውቀዋት ከተሰጣቸው ከቅድስት ትእዛዝ ከሚመለሱ የጽድቅን መንገድ ባላወቋት በተሻላቸው ነበርና። “ውሻ ወደ ትፋቱ ይመለሳል፤” ደግሞ “የታጠበች እርያ በጭቃ ለመንከባለል ትመለሳለች፤” እንደሚባል እውነተኞች ምሳሌዎች ሆኖባቸዋል።
2 ጴጥሮስ 2:21-22 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
የጽድቅን መንገድ ካወቁ በኋላ ከተሰጣቸው ቅዱስ ትእዛዝ ወደ ኋላ ከሚመለሱ፣ ቀድሞውኑ የጽድቅን መንገድ ባላወቋት ይሻላቸው ነበር። “ውሻ ወደ ትፋቱ ይመለሳል” እንዲሁም “ዐሣማ ቢታጠብም ተመልሶ በጭቃ ላይ ይንከባለላል” የሚለው ምሳሌ እውን ይሆንባቸዋል።
2 ጴጥሮስ 2:21-22 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
አውቀዋት ከተሰጣቸው ከቅድስት ትእዛዝ ከሚመለሱ የጽድቅን መንገድ ባላወቋት በተሻላቸው ነበርና። ውሻ ወደ ትፋቱ ይመለሳል፥ ደግሞ፦ የታጠበች እርያ በጭቃ ለመንከባለል ትመለሳለች እንደሚባል እውነተኞች ምሳሌዎች ሆኖባቸዋል።