2 ነገሥት 6:18
2 ነገሥት 6:18 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ሶርያውያንም ወደ እርሱ በወረዱ ጊዜ ኤልሳዕ “እግዚአብሔር ሆይ! እነዚህ ሰዎች እንዲታወሩ አድርግ!” ብሎ ጸለየ፤ እግዚአብሔርም የኤልሳዕን ጸሎት በመስማት፥ ዐይኖቻቸው እንዲታወሩ አደረገ።
2 ነገሥት 6:18 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ወደ እርሱም በወረዱ ጊዜ ኤልሳዕ፥ “አቤቱ፥ እነዚህን ሰዎች አሳውራቸው” ብሎ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። ኤልሳዕም እንደ ተናገረው ቃል አሳወራቸው።
2 ነገሥት 6:18 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ሶርያውያንም ወርደው ወደ እርሱ ሲመጡ ኤልሳዕ፣ “ይህን ሕዝብ ዕውር አድርገው” ብሎ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። ስለዚህ ኤልሳዕ በጠየቀው መሠረት እግዚአብሔር ዕውር አደረጋቸው።
2 ነገሥት 6:18 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ወደ እርሱም በወረዱ ጊዜ ኤልሳዕ “ይህን ሕዝብ ዕውር ታደርገው ዘንድ እለምንሃለሁ፤” ብሎ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። ኤልሳዕም እንደ ተናገረው ቃል ዕውር አደረጋቸው።