2 ነገሥት 2:14
2 ነገሥት 2:14 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
በራሱ ላይ ያረፈችውን የኤልያስን መጠምጠሚያ ወስዶ ውኃውን መታባት፦ ውኃው ግን አልተከፈለም፤ እርሱም፥ “የኤልያስ አምላክ እግዚአብሔር ወዴት ነው? እንዴትስ ነው?” አለ። ከዚህም በኋላ ውኃውን በመታ ጊዜ ወዲህና ወዲያ ተከፈለ፤ ኤልሳዕም ተሻገረ።
2 ነገሥት 2:14 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ከኤልያስ፣ የወደቀውንም ካባ ይዞ ውሃውን መታና፣ “የኤልያስ አምላክ እግዚአብሔር ወዴት ነው?” አለ። ውሃውን ሲመታውም ውሃው በግራና በቀኝ ተከፈለ፤ ኤልሳዕም ተሻገረ።
2 ነገሥት 2:14 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ከኤልያስም የወደቀውን መጎናጸፊያ ወስዶ ውሃውን መታና፥ “የኤልያስ አምላክ እግዚአብሔር ወዴት ነው?” አለ፤ ውሃውንም በመታ ጊዜ ወዲህና ወዲያ ተከፈለ፤ ኤልሳዕም ተሻገረ።