2 ቆሮንቶስ 5:5-7
2 ቆሮንቶስ 5:5-7 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ለዚህም ያዘጋጀን እግዚአብሔር ነው፤ እርሱም የመንፈስ ቅዱስን ፈለማ ሰጠን። እንግዲህ ሁልጊዜ እመኑ፥ ጨክኑም፤ በዚህ ሥጋ ሳላችሁም እናንተ እንግዶች እንደ ሆናችሁ ታውቃላችሁ፤ ከሥጋችሁም ተለይታችሁ ወደ ጌታችን ትሄዳላችሁ። በእምነት እንኖራለን፤ በማየትም አይደለም።
2 ቆሮንቶስ 5:5-7 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ለዚህ ዐላማ ያዘጋጀን እግዚአብሔር ነው፤ ሊመጣ ላለው ዋስትና እንዲሆነን መንፈሱን መያዣ አድርጎ የሰጠንም እርሱ ነው። ስለዚህ ሁልጊዜ በመታመን እንኖራለን፤ በሥጋ እስካለን ድረስ ከጌታ ርቀን እንደምንገኝ እናውቃለን፤ ምክንያቱም የምንኖረው በእምነት እንጂ በማየት አይደለም።
2 ቆሮንቶስ 5:5-7 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ነገር ግን ለዚሁ የሠራን እግዚአብሔር ነው እርሱም የመንፈሱን መያዣ ሰጠን። እንግዲህ ሁልጊዜ ታምነን በእምነት እንጂ በማየት አንመላለስምና በሥጋ ስናድር ከጌታ ተለይተን በስደት እንዳለን የምናውቅ ከሆንን፥