2 ቆሮንቶስ 5:17-19
2 ቆሮንቶስ 5:17-19 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
አሁንም በክርስቶስ የሆነው ሁሉ አዲስ ፍጥረት ነው፤ የቀደመውም አለፈ፤ እነሆ ሁሉም አዲስ ሆነ። ነገር ግን ሁሉ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ከአስታረቀን፥ የማስታረቅ መልእክትንም ከሰጠን ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው። ኀጢአታቸውን ይቅር ብሎ በደላቸውንም ሳያስብ እግዚአብሔር በክርስቶስ ዓለሙን ከራሱ ጋር አስታርቆአልና፤ የዕርቅ ቃሉንም በእኛ ላይ አደረገ፤ የይቅርታውንም መልእክት ሰጠን።
2 ቆሮንቶስ 5:17-19 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር ዐልፏል፤ እነሆ፤ አዲስ ሆኗል። ይህ ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፤ እርሱ በክርስቶስ አማካይነት ከራሱ ጋራ አስታረቀን፤ የማስታረቅንም አገልግሎት ሰጠን፤ እግዚአብሔር በክርስቶስ ዓለምን ከራሱ ጋራ ሲያስታርቅ የሰዎችን በደል አይቈጥርባቸውም ነበር፤ ለእኛም ደግሞ የማስታረቅ ቃል ሰጠን።
2 ቆሮንቶስ 5:17-19 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል። ነገር ግን የሆነው ሁሉ፥ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን፥ ከእግዚአብሔር ነው፤ እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ።
2 ቆሮንቶስ 5:17-19 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ስለዚህ ማንም ሰው የክርስቶስ ወገን ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ፍጥረት አልፎአል፤ በእርሱም ስፍራ አዲስ ፍጥረት ተተክቶአል። ይህም ሁሉ የሆነው እኛን ከራሱ ጋር በክርስቶስ አማካይነት ባስታረቀንና የማስታረቅንም አገልግሎት በሰጠን በእግዚአብሔር ነው። ይህም እግዚአብሔር በክርስቶስ የዓለምን ሰዎች ሁሉ ከራሱ ጋር አስታረቀ ማለት ነው፤ በደላቸውንም አልቈጠረባቸውም፤ ለእኛም ሰውን ከጌታ ጋር የምናስታርቅበትን ቃል ሰጠን።