2 ቆሮንቶስ 5:13-19

2 ቆሮንቶስ 5:13-19 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

እኛ ሰነ​ፎች ብን​ሆ​ንም፥ ስን​ፍ​ና​ችን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ ዐዋ​ቂ​ዎች ብን​ሆ​ንም ዐዋ​ቂ​ነ​ታ​ችን ለእ​ና​ንተ ነው። የክ​ር​ስ​ቶስ ፍቅር በዚህ አሳብ እን​ድ​ን​ጸና ያስ​ገ​ድ​ደ​ናል፤ ሁሉ ፈጽ​መው ስለ ሞቱ አንዱ ስለ ሁሉ ቤዛ ሆኖ ሞቶ​አ​ልና። በሕ​ይ​ወት የሚ​ኖ​ሩ​ትም ስለ እነ​ርሱ ቤዛ ሆኖ ለሞ​ተ​ውና ለተ​ነ​ሣ​ውም እንጂ ወደ​ፊት ለራ​ሳ​ቸው የሚ​ኖሩ እን​ዳ​ይ​ሆኑ እርሱ ስለ ሁሉ ቤዛ ሆኖ ሞተ። ስለ​ዚህ ከአ​ሁን ጀምሮ በሥጋ የም​ና​ው​ቀው የለም፤ ክር​ስ​ቶ​ስ​ንም በሥጋ ብና​ው​ቀው አሁን ግን ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ የም​ና​ው​ቀው አይ​ደ​ለም። አሁ​ንም በክ​ር​ስ​ቶስ የሆ​ነው ሁሉ አዲስ ፍጥ​ረት ነው፤ የቀ​ደ​መ​ውም አለፈ፤ እነሆ ሁሉም አዲስ ሆነ። ነገር ግን ሁሉ በክ​ር​ስ​ቶስ ከራሱ ጋር ከአ​ስ​ታ​ረ​ቀን፥ የማ​ስ​ታ​ረቅ መል​እ​ክ​ት​ንም ከሰ​ጠን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ነው። ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ይቅር ብሎ በደ​ላ​ቸ​ው​ንም ሳያ​ስብ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በክ​ር​ስ​ቶስ ዓለ​ሙን ከራሱ ጋር አስ​ታ​ር​ቆ​አ​ልና፤ የዕ​ርቅ ቃሉ​ንም በእኛ ላይ አደ​ረገ፤ የይ​ቅ​ር​ታ​ው​ንም መል​እ​ክት ሰጠን።

2 ቆሮንቶስ 5:13-19 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

እብዶች ብንሆን ለእግዚአብሔር ስንል ነው፤ ባለ አእምሮዎች ብንሆንም ለእናንተ ስንል ነው። አንድ ጊዜ ክርስቶስ ለሁሉም መሞቱንና ሁሉም የእርሱ ሞት ተካፋዮች መሆናቸውን ስለ ተረዳን የክርስቶስ ፍቅር ለሥራ ያስገድደናል። በሕይወት ያሉት ሁሉ ለእነርሱ ለሞተውና ከሞትም ለተነሣው እንዲኖሩ እንጂ ከእንግዲህ ወዲህ ለራሳቸው ሲሉ እንዳይኖሩ ክርስቶስ ለሁሉም ሞተ። ከእንግዲህ ወዲህ እኛ ማንንም ሰው በሥጋዊ አመለካከት አንመለከትም፤ ከዚህ በፊት ክርስቶስንም የተመለከትነው እንደ ማንኛውም ሰው በሥጋዊ አመለካከት ከሆነ ለወደፊቱ ግን ይህን አናደርግም። ስለዚህ ማንም ሰው የክርስቶስ ወገን ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ፍጥረት አልፎአል፤ በእርሱም ስፍራ አዲስ ፍጥረት ተተክቶአል። ይህም ሁሉ የሆነው እኛን ከራሱ ጋር በክርስቶስ አማካይነት ባስታረቀንና የማስታረቅንም አገልግሎት በሰጠን በእግዚአብሔር ነው። ይህም እግዚአብሔር በክርስቶስ የዓለምን ሰዎች ሁሉ ከራሱ ጋር አስታረቀ ማለት ነው፤ በደላቸውንም አልቈጠረባቸውም፤ ለእኛም ሰውን ከጌታ ጋር የምናስታርቅበትን ቃል ሰጠን።

2 ቆሮንቶስ 5:13-19 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

አእምሮችንን የሳትን ብንሆን፥ የሳትነው ለእግዚአብሔር ነው፤ ጤነኞችም ብንሆን ለእናንተ ነው። አንዱ ስለ ሁሉ እንደ ሞተ እርግጠኞች በመሆናችን፥ የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናል፤ ይህ በመሆኑም ሁሉ ሞተዋል። በሕይወትም ያሉት፥ ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ፥ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ እርሱ ስለ ሁሉ ሞተ። ስለዚህ ከአሁን ጀምሮ ማንንም በሰብአዊ አመለካከት እንደምናየው አድርገን አንመለክትም፤ ክርስቶስንም በዚህ መልክ ተመልክተነው የነበርን ብንሆን እንኳን፥ ከእንግዲህ ወዲህ ግን በዚህ መልክ አይደለም የምናውቀው። ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል! ይህ ሁሉ የሆነው፥ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን፥ የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን ከእግዚአብሔር ነው፤ ይህ እግዚአብሔር የሰዎችን በደል ሳይቆጥርባቸው በክርስቶስ ዓለምን ከራሱ ጋር አስታርቋል፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኑሯል።

2 ቆሮንቶስ 5:13-19

2 ቆሮንቶስ 5:13-19 NASV