2 ቆሮንቶስ 5:1-8

2 ቆሮንቶስ 5:1-8 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

በም​ድር ያለው ማደ​ሪያ ቤታ​ችን ቢፈ​ር​ስም፥ በሰ​ማይ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የሰው እጅ ያል​ሠ​ራው ዘለ​ዓ​ለ​ማዊ ቤት እን​ዳ​ለን እና​ው​ቃ​ለን። ስለ እርሱ የም​ን​ደ​ክ​ም​ለ​ትን በሰ​ማይ ያለ​ውን ቤታ​ች​ንን እን​ለ​ብስ ዘንድ እር​ሱን ተስፋ እና​ደ​ር​ጋ​ለን። ከለ​በ​ስ​ነ​ውም በኋላ ዕራ​ቍ​ታ​ች​ንን የም​ን​ገኝ አይ​ደ​ለ​ንም። በዚህ ቤት ውስጥ ሳለ​ንም ከከ​ባ​ድ​ነቱ የተ​ነሣ እጅግ እና​ዝ​ና​ለን፤ ነገር ግን ሟች በሕ​ይ​ወት ይዋጥ ዘንድ ሌላ ልን​ለ​ብስ እንጂ ልን​ገ​ፈፍ አን​ወ​ድም። ለዚ​ህም ያዘ​ጋ​ጀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ እር​ሱም የመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስን ፈለማ ሰጠን። እን​ግ​ዲህ ሁል​ጊዜ እመኑ፥ ጨክ​ኑም፤ በዚህ ሥጋ ሳላ​ች​ሁም እና​ንተ እን​ግ​ዶች እንደ ሆና​ችሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ ከሥ​ጋ​ች​ሁም ተለ​ይ​ታ​ችሁ ወደ ጌታ​ችን ትሄ​ዳ​ላ​ችሁ። በእ​ም​ነት እን​ኖ​ራ​ለን፤ በማ​የ​ትም አይ​ደ​ለም። ታም​ነ​ናል፤ ይል​ቁ​ንም ከሥ​ጋ​ችን ተለ​ይ​ተን ወደ ጌታ​ችን እን​ሄ​ዳ​ለ​ንና ደስ ይለ​ናል።

2 ቆሮንቶስ 5:1-8 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ይህ እንደ ድንኳን ጊዜያዊ የሆነው ምድራዊው ሥጋችን ሲፈርስ በሰው እጅ ሳይሆን በእግዚአብሔር የታነጸ ዘለዓለማዊ መኖሪያ በሰማይ እንዳለን እናውቃለን። ሰማያዊ አካልን ለመልበስ በመናፈቅ እንጥራለን። እርሱንም ስንለብስ ራቁታችንን ሆነን አንገኝም። በዚህ እንደ ምድራዊ ድንኳን በሆነው ሥጋችን ውስጥ ስንኖር ከብደን እንቃትታለን፤ የምንቃትተውም ሞት በሕይወት እንዲለወጥ ሰማያዊውን አካል በበለጠ እንድንለብስ ነው እንጂ ከዚህ ከምድራዊ ሥጋችን ለመለየት በመፈለግ አይደለም። ለዚህም ነገር ያዘጋጀን እግዚአብሔር ነው፤ ከዚያም በላይ ለሚሰጠን ነገር ሁሉ ዋስትና እንዲሆን መንፈሱን የሰጠንም እርሱ ነው። በምድራዊ ሰውነታችን እስካለንበት ጊዜ ድረስ ከጌታ የራቅን መሆናችንን ብናውቅም እንኳ ሁልጊዜ በእርሱ እንተማመናለን። እኛ የምንኖረውም ጌታን በማመን እንጂ እርሱን በማየት አይደለም። ከዚህ እንደ መኖሪያችን ከሆነው ሥጋችን ተለይተን ከጌታ ጋር ለመሆን እንመኛለን፤ ስለዚህ በመተማመን እንኖራለን።