2 ቆሮንቶስ 4:7-15

2 ቆሮንቶስ 4:7-15 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ነገር ግን ይህ እጅግ ታላቅ ኀይል ከእግዚአብሔር እንጂ ከእኛ አለመሆኑን ለማሳየት፣ ይህ የከበረ ነገር በሸክላ ዕቃ ውስጥ አለን። ከየአቅጣጫው ብንገፋም አንንኰታኰትም፤ ግራ ብንጋባም ተስፋ አንቈርጥም፤ ብንሰደድም ተጥለን አንቀርም፤ መትተው ቢጥሉንም አንጠፋም። የኢየሱስ ሕይወት በሰውነታችን እንዲገለጥ፣ የኢየሱስን ሞት ዘወትር በሰውነታችን ተሸክመን እንዞራለን። የኢየሱስ ሕይወት ሟች በሆነው ሥጋችን እንዲገለጥ፣ እኛ ሕያዋን የሆንን ሁልጊዜ ስለ ኢየሱስ ለሞት ዐልፈን እንሰጣለንና። እንግዲህ ሞት በእኛ ይሠራል፤ ሕይወት ግን በእናንተ። “አመንሁ፤ ስለዚህም ተናገርሁ” ተብሎ እንደ ተጻፈ፣ እኛም በዚያው የእምነት መንፈስ እናምናለን፤ ስለዚህም እንናገራለን፤ ምክንያቱም ጌታ ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው እኛንም ደግሞ ከኢየሱስ ጋራ አስነሥቶ ከእናንተ ጋራ በፊቱ እንደሚያቀርበን እናውቃለን። ለብዙ ሰዎች እየደረሰ ያለው ጸጋ፣ ለእግዚአብሔር ክብር በምስጋና ላይ ምስጋናን እንዲጨምር ይህ ሁሉ ለእናንተ ጥቅም ሆኗል።

2 ቆሮንቶስ 4:7-15 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ነገር ግን ከእኛ ያይ​ደለ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ገኘ ታላቅ ኀይል ይሆን ዘንድ በሸ​ክላ ዕቃ ውስጥ ይህ መዝ​ገብ አለን። በሁሉ መከ​ራን እን​ቀ​በ​ላ​ለን፤ ነገር ግን አን​ጨ​ነ​ቅም፤ እን​ና​ቃ​ለን፥ ነገር ግን ተስፋ አን​ቈ​ር​ጥም። እን​ሰ​ደ​ዳ​ለን፤ ነገር ግን አን​ጣ​ልም፤ እን​ወ​ድ​ቃ​ለን፤ ነገር ግን አን​ጠ​ፋም። የክ​ር​ስ​ቶስ ሕይ​ወቱ በዚህ በሟች ሰው​ነ​ታ​ችን ላይ ይገ​ለጥ ዘንድ፥ ዘወ​ትር የክ​ር​ስ​ቶ​ስን ሞት በሥ​ጋ​ችን እን​ሸ​ከ​ማ​ለን። በሕ​ይ​ወት የም​ን​ኖር እኛም በሟች ሰው​ነ​ታ​ችን ላይ የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ሕይ​ወቱ ይገ​ለጥ ዘንድ፥ ዘወ​ትር ስለ ኢየ​ሱስ ክስ​ር​ቶስ ብለን ተላ​ል​ፈን ለሞት እን​ሰ​ጣ​ለን። ስለ​ዚ​ህም ሞት በእኛ ላይ፥ ሕይ​ወ​ትም በእ​ና​ንተ ላይ ይሠ​ራል። አንድ የእ​ም​ነት መን​ፈስ አለን፤ መጽ​ሐፍ፥ “አመ​ንሁ፤ ስለ​ዚ​ህም ተና​ገ​ርሁ” እን​ዳለ እኛም አመን፤ ስለ​ዚ​ህም ተና​ገ​ርን። ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ያስ​ነ​ሣው እርሱ እኛ​ንም እንደ እርሱ እን​ዲ​ያ​ስ​ነ​ሣን፥ ከእ​ና​ን​ተም ጋር በፊቱ እን​ዲ​ያ​ቆ​መን እና​ው​ቃ​ለን። ጸጋው በብ​ዙ​ዎች ላይ ትት​ረ​ፈ​ረፍ ዘንድ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የክ​ብሩ ምስ​ጋና ይበዛ ዘንድ ሁሉ ስለ እና​ንተ ነውና።

2 ቆሮንቶስ 4:7-15 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

ነገር ግን ይህ እጅግ ታላቅ ኀይል ከእግዚአብሔር እንጂ ከእኛ አለመሆኑን ለማሳየት፣ ይህ የከበረ ነገር በሸክላ ዕቃ ውስጥ አለን። ከየአቅጣጫው ብንገፋም አንንኰታኰትም፤ ግራ ብንጋባም ተስፋ አንቈርጥም፤ ብንሰደድም ተጥለን አንቀርም፤ መትተው ቢጥሉንም አንጠፋም። የኢየሱስ ሕይወት በሰውነታችን እንዲገለጥ፣ የኢየሱስን ሞት ዘወትር በሰውነታችን ተሸክመን እንዞራለን። የኢየሱስ ሕይወት ሟች በሆነው ሥጋችን እንዲገለጥ፣ እኛ ሕያዋን የሆንን ሁልጊዜ ስለ ኢየሱስ ለሞት ዐልፈን እንሰጣለንና። እንግዲህ ሞት በእኛ ይሠራል፤ ሕይወት ግን በእናንተ። “አመንሁ፤ ስለዚህም ተናገርሁ” ተብሎ እንደ ተጻፈ፣ እኛም በዚያው የእምነት መንፈስ እናምናለን፤ ስለዚህም እንናገራለን፤ ምክንያቱም ጌታ ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው እኛንም ደግሞ ከኢየሱስ ጋራ አስነሥቶ ከእናንተ ጋራ በፊቱ እንደሚያቀርበን እናውቃለን። ለብዙ ሰዎች እየደረሰ ያለው ጸጋ፣ ለእግዚአብሔር ክብር በምስጋና ላይ ምስጋናን እንዲጨምር ይህ ሁሉ ለእናንተ ጥቅም ሆኗል።

2 ቆሮንቶስ 4:7-15 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)

ነገር ግን የኃይሉ ታላቅነት ከእግዚአብሔር እንጂ ከእኛ እንዳይሆን ይህ መዝገብ በሸክላ ዕቃ ውስጥ አለን፤ በሁሉ እንገፋለን እንጂ አንጨነቅም፤ እናመነታለን እንጂ ተስፋ አንቆርጥም፤ እንሰደዳለን እንጂ አንጣልም፤ እንወድቃለን እንጂ አንጠፋም፤ የኢየሱስ ሕይወት ደግሞ በሥጋችን ይገለጥ ዘንድ ሁልጊዜ የኢየሱስን መሞት በሥጋችን ተሸክመን እንዞራለን። የኢየሱስ ሕይወት ደግሞ በሚሞት ሥጋችን ይገለጥ ዘንድ እኛ ሕያዋን የሆንን ከኢየሱስ የተነሣ ዘወትር ለሞት አልፈን እንሰጣለንና። ስለዚህ ሞቱ በእኛ ሕይወቱም በእናንተ ይሠራል። ነገር ግን፦ አመንሁ ስለዚህም ተናገርሁ ተብሎ እንደ ተጻፈ ያው አንዱ የእምነት መንፈስ ስላለን፥ እኛ ደግሞ እናምናለን ስለዚህም እንናገራለን፤ ጌታን ኢየሱስን ያስነሣው እኛን ደግሞ ከኢየሱስ ጋር እንዲያስነሣን ከእናንተም ጋር እንዲያቀርበን እናውቃለንና። በብዙዎች በኩል የተትረፈረፈው ጸጋ ለእግዚአብሔር ክብር ምስጋናን ያበዛ ዘንድ፥ ሁሉ ስለ እናንተ ነውና።

2 ቆሮንቶስ 4:7-15 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)

ነገር ግን ይህ ከሁሉ የሚበልጠው ኀይል የእግዚአብሔር እንጂ የእኛ አለመሆኑ እንዲታወቅ ይህን ክቡር ነገር እንደ ሸክላ ዕቃ ሆነን ይዘነዋል። በየአቅጣጫው መከራ ይደርስብናል፤ ግን አንሸነፍም፤ ብዙ ጊዜ ግራ ይገባናል፤ ግን ተስፋ አንቈርጥም፤ ጠላቶች ያሳድዱናል፤ ግን ወዳጆች አጥተን አናውቅም፤ ተመተን እንወድቃለን፤ ግን አንሞትም፤ የኢየሱስ ሕይወት በእኛ ሰውነት እንዲገለጥ በኢየሱስ ላይ የደረሰው ሞት በእኛም ሰውነት ላይ ዘወትር ተሸክመን እንዞራለን። የኢየሱስ ሕይወት በሟች ሰውነታችን ይገለጥ ዘንድ እኛ ሕያዋኑ ስለ ኢየሱስ ሁልጊዜ ለሞት ተላልፈን እንሰጣለን። ስለዚህ እኛ መላልሰን ለሞት ስንጋለጥ እናንተ ግን ለሕይወት ትጋለጣላችሁ። ይሁን እንጂ “አመንኩ፤ ስለዚህ ተናገርኩ” ተብሎ እንደ ተጻፈው፥ እኛም ያው አንዱ የእምነት መንፈስ ስላለን እናምናለን፤ ስለዚህም እንናገራለን። ጌታ ኢየሱስን ከሞት ያስነሣ አምላክ እኛንም ከኢየሱስ ጋር እንደሚያስነሣንና ከእናንተም ጋር በፊቱ እንደሚያቀርበን እናውቃለን። ይህ ሁሉ ለእናንተ ጥቅም የሆነው ጸጋ ተትረፍርፎ ለብዙ ሰዎች በደረሰ መጠን ለእግዚአብሔር ክብር የሚሆነው ምስጋና እንዲበዛ ነው።

2 ቆሮንቶስ 4:7-15 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)

ነገር ግን ይህ ልዩ ኃይል የእግዚአብሄር መሆኑንና ከእኛ አለመመጣቱን ግልጽ ለማድረግ፥ ይህ ሀብት በሸክላ ዕቃ ውስጥ አለን፤ ከየአቅጣጫው መከራን እንቀበላለን እንጂ አንጨነቅም፤ ግራ እንጋባለን እንጂ ተስፋ አንቆርጥም፤ እንሰደዳለን እንጂ አንተውም፤ እንወድቃለን እንጂ አንጠፋም፤ የኢየሱስ ሕይወት ደግሞ በሥጋችን እንዲገለጥ፥ ሁልጊዜ የኢየሱስን መሞት በሥጋችን ተሸክመን እንዞራለን። የኢየሱስ ሕይወት ደግሞ በሚሞት ሥጋችን እንዲገለጥ፥ እኛ ሕያዋን የሆንን ስለ ኢየሱስ ስንል ዘወትር ለሞት አልፈን እንሰጣለን። ስለዚህ ሞት በእኛ፥ ሕይወት ግን በእናንተ ይሠራል። ነገር ግን “አመንሁ፤ ስለዚህም ተናገርሁ፤” ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ ያው አንዱ የእምነት መንፈስ ስላለን፥ እኛ ደግሞ እናምናለን፤ ስለዚህም እንናገራለን። ምክንያቱም ጌታን ኢየሱስን ያስነሣው እኛንም ከኢየሱስ ጋር እንደሚያስነሣንና ከእናንተም ጋር በፊቱ እንደሚያቀርበን እናውቃለን። በብዙዎች በኩል የተትረፈረፈው ጸጋ፥ ለእግዚአብሔር ክብር ምስጋናን እንዲያበዛ፥ ሁሉም ነገር ስለ እናንተ ሆኗል።

2 ቆሮንቶስ 4:7-15

2 ቆሮንቶስ 4:7-15 NASV