2 ቆሮንቶስ 11:14-15
2 ቆሮንቶስ 11:14-15 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
ይህም የሚያስደንቅ ነገር አይደለም፤ ሰይጣን እንኳ የብርሃን መልአክ ለመምሰል ራሱን ይለውጣል። ስለዚህ እነዚህ የሰይጣን አገልጋዮች የጽድቅ አገልጋዮችን ለመምሰል ራሳቸውን ቢለውጡ አያስደንቅም፤ በመጨረሻ የሥራቸውን ዋጋ ያገኛሉ።
2 ቆሮንቶስ 11:14-15 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ይህም አያስደንቅም፤ ሰይጣን ራሱ ተለውጦ እንደ ብርሃን መልአክ ይመስላልና። መልእክተኞቹም የጽድቅ መላእክትን ቢመስሉ፥ ይህ ታላቅ ነገር አይደለም፤ ፍጻሜያቸው ግን እንደ ሥራቸው ነው።
2 ቆሮንቶስ 11:14-15 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ይህም የሚያስደንቅ ነገር አይደለም፤ ምክንያቱም ሰይጣን ራሱ የብርሃን መልአክ ለመምሰል ራሱን ይለዋውጣል። እንግዲህ የርሱ አገልጋዮች፣ የጽድቅ አገልጋዮች ለመምሰል ራሳቸውን ቢለውጡ የሚያስገርም አይደለም፤ ፍጻሜአቸውም እንደ ሥራቸው ይሆናል።
2 ቆሮንቶስ 11:14-15 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ይህም ድንቅ አይደለም፤ ሰይጣን ራሱ የብርሃንን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለውጣልና። እንግዲህ አገልጋዮቹ ደግሞ የጽድቅን አገልጋዮች እንዲመስሉ ራሳቸውን ቢለውጡ ታላቅ ነገር አይደለም፤ ፍጻሜአቸውም እንደ ሥራቸው ይሆናል።