2 ቆሮንቶስ 10:2-5
2 ቆሮንቶስ 10:2-5 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ወደ እናንተ በመጣሁ ጊዜ እሠራለሁ፤ በሥጋዊ ሥርዐትም እንደምንኖር አድርገው በሚጠረጥሩን ሰዎች ላይ በድፍረት ለመናገር አስባለሁ፤ እናንተ ግን በዚህ ዓይነት ድፍረት እንድናገር እንዳታደርጉኝ እለምናችኋለሁ። በሥጋችንስ እንሄዳለን፤ ነገር ግን በእርሱው ሥርዐት የምንሄድና የምንዋጋ አይደለም። የጦር ዕቃችን ሥጋዊ አይደለምና፥ ጽኑ ምሽግን በሚያፈርስ በእግዚአብሔር ኀይል ነው እንጂ። ልብ ሁሉ ይማረክ ዘንድ ኅሊናም ለክርስቶስ ይገዛ ዘንድ በእግዚአብሔር ላይ የሚታበየውንና ከፍ ከፍ የሚለውን እናፈርሳለን።
2 ቆሮንቶስ 10:2-5 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ወደ እናንተ በምመጣበት ጊዜ፣ በዓለማዊ መንገድ እንደምንኖር አድርገው በሚቈጥሩን ሰዎች ላይ በድፍረት ለመናገር ቈርጫለሁ፤ እናንተን ግን በዚያ ዐይነት ድፍረት እንድናገር እንዳታደርጉኝ እለምናችኋለሁ። የምንኖረው በዚህ ዓለም ቢሆንም፣ የምንዋጋው በዚህ ዓለም ስልት አይደለም። ደግሞም የምንዋጋበት የጦር መሣሪያ የዚህ ዓለም መሣሪያ አይደለም፤ ይሁን እንጂ ምሽግን ለመደምሰስ የሚችል መለኮታዊ ኀይል ያለው ነው። በእግዚአብሔር ዕውቀት ላይ በትዕቢት የሚነሣውን ክርክርና ከንቱ ሐሳብ ሁሉ እናፈርሳለን፤ አእምሮንም ሁሉ እየማረክን ለክርስቶስ እንዲታዘዝ እናደርጋለን።
2 ቆሮንቶስ 10:2-5 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
በዓለማዊ ልማድ እንደምንመላለስ በሚቆጥሩን በአንዳንዶች ላይ አምኜ ልደፍር አስባለሁ፥ በዚያ እምነት ግን ከእናንተ ጋር ሆኜ እንዳልደፍር እለምንችኋለሁ። በሰው ልማድ ምንም እንኳ የምንመላለስ ብንሆን፥ እንደ ሰው ልማድ አንዋጋም፤ የጦር ዕቃችን ሥጋዊ አይደለምና፥ ምሽግን ለመስበር ግን በእግዚአብሔር ፊት ብርቱ ነው፤ የሰውንም አሳብ በእግዚአብሔርም እውቀት ላይ የሚነሣውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን ለክርስቶስም ለመታዘዝ አእምሮን ሁሉ እንማርካለን፥
2 ቆሮንቶስ 10:2-5 አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም (አማ05)
የምለምናችሁም ወደ እናንተ በምመጣበት ጊዜ በድፍረት እንድናገር እንዳታደርጉኝ ነው፤ በሥጋ አስተሳሰብ እንደምንመላለስ አድርገው በሚገምቱን በአንዳንድ ሰዎች ፊት ግን በድፍረት ለመናገር እፈልጋለሁ። ምንም እንኳ በዓለም ብንኖር የምንዋጋው ዓለማዊ ጦርነት አይደለም። የጦር መሣሪያዎቻችንም ምሽግ ለማፍረስ የሚያስችል መለኮታዊ ኀይል ያላቸው ናቸው እንጂ ዓለማዊ የጦር መሣሪያዎች አይደሉም። እግዚአብሔርን በማወቅ ላይ እንቅፋት ሆነው የሚነሡትን ክርክርና ትዕቢት እናፈርሳለን፤ የሰውን ሐሳብ ሁሉ እየማረክንም ለክርስቶስ እንዲታዘዝ እናደርጋለን።
2 ቆሮንቶስ 10:2-5 መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) (መቅካእኤ)
ስመጣ ግን በዓለማዊ ልማድ እንደምንመላለስ በሚቆጥሩን በአንዳንዶች ላይ በድፍረት ለመናገር አስባለሁ፤ እናንተን ግን በዚያ ድፍረት እንድናገር እንዳታደርጉኝ እለምናችኋለሁ። ምንም እንኳ በሥጋ የምንመላለስ ብንሆን፥ ውጊያችንን ግን እንደ ሰው ልማድ አንዋጋም፤ ምክንያቱም የጦር ዕቃችን ሥጋዊ አይደለም፤ ምሽግን ለመስበር መለኮታዊ ኃይል አለው። በእግዚአብሔር እውቀት ላይ የሚነሣውን ከፍ ያለውን ክርክርና ማንኛውም የእብሪት እንቅፋት እናፈርሳለን፤ አእምሮን ሁሉ እየማረክን ለክርስቶስ እንዲታዘዝ እናደርጋለን፤